በአገር አቀፍ ደረጃ የድንገተኛ አገልግሎት መስጫ ማዕከል እየተገነባ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ

በአገር አቀፍ ደረጃ የድንገተኛ አገልግሎት መስጫ ማዕከል እየተገነባ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

በ72 ኛው አለም አቀፍ የጤና ጉባኤ ጎን ለጎን በኢትዮጵያና እስዋቲኒ አዘጋጅነት በድንገተኛ የጤና አገልግሎት ላይ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

በውይይት መድረኩ ለይ የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን ድንገተኛ የጤና አገልግሎትና ፈጣን ምላሽን አስመልክቶ የኢትዮጵያን ተሞክሮ አቅርበዋል፡፡

ዶክተር አሚር ባቀረቡት ድሑፋቸው በኢትዮጵያ የድንገተኛ ጤና አገልግሎት ከጤና ኬላ ጀምሮ በሁሉም የጤና ተቋማት የሚሰጥ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአገር አቀፍ ደረጃ የድንገተኛ አገልግሎት መስጫ ማዕከል (Trauma Center) እየተገነባ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል በኢትዮጵያና ኢኳዶር ለጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች እውቅና ለመስጠት የቀረበውን ረቂቅ ሃሳብ የአለም ጤና ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡