የደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተመረቀ

የደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተመርቋል፡፡

የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ከ270 በላይ አልጋዎችን የያዘ የእናቶችና ህፃናት ህክምና ማዕከል ሲሆን በምስራቅ አማራ ላሉ ሆስፒታሎች አገልግሎት ይሰጣል፡፡

የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ በቀን 120 ሲሊንደር ማምረት የሚችል የሜዲካል ኦክስጂን ማምረቻ፣ የሲቲ ስካን መሳሪያ እና ዘመናዊ የመድኅኒት መጋዘን ያካተተ ነው:: 
በተጨማሪም በሆስፒታሉ ውስጥ የአደጋና የድንገተኛ ህክምና መስጫ ማዕከል እና የዲያግኖስቲክስ እና አይሲቲ ማዕከል ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ፕሮግራም ተካሂዷል::

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንን ተገኝተዋል፡፡

/የጤና ሚኒስቴር/