ከ15 አመት በታች የሆኑ ህፃናት ለከፍተኛ የጥርስ ህመም ተጋላጭ መሆናቸዉ ተገለፀ

እድሜያቸው ከ15 አመት በታች የሆኑ ህፃናት ላይ እየታየ ያለው የጥርስ ህመም ችግር ከፍተኛ እንደሆነ ጥናት አመለከተ።

ጥናቱን ያካሄዱት የጥርስ ስፕሻሊስቷ ዶክተር የሽመቤት አለሙ በኢትዮጵያ የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መጥቷል በተከይ በመዲናዋ አዲስ አበባ በርካታ የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች በየጊዜው ይከፈታሉ ይህ የሚያሳየው ደግሞ የጥርስ ህመም ችግሩ እየተበራከተ በመምጣቱ ቅድመ መከላከል ላይ መስራት አለበት ሲሉም ይገልፃሉ።

ዶክተር የሽመቤት አጠናሁት ባሉት ጥናት መሰረት በሀገራችን እየተከሰተ ያለው የጥርስ ህመም ችግር አሳሳቢነቱ ከፍተኛ መሆኑን ይናገራሉ በተለይ ጥናቱ መሰረት ባደረገባቸው እድሙያቸው ከ15 አመት በታች ያሉ ህፃናት ላይ ውጤቱ ከፍተኛ ነው ሲሉም ይገልፃሉ።

የአኗኗር ዘይቢያችን መቀየርና በአመጋገባችን ላይ ጥንቃቄ አለማድረጋችን ለዚህ ችግር መከሰት ዋነኛ ምክንያት መሆኑን የሚጠቅሱት ባለሙያዋ ችግሩ በዚህ ሳያበቃ አሁን ላይ ሀገሪቱን እያሳሰቧት ላሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በተለይ ለኩላሊት ህመም እንደሚዳርግም ተናግረዋል።

በከፍተኛ ደረጃ የጥርስ ህክምና መስጫ ተቋማት እንዳሉ የጠቀሱት ባለሙያዋ የመንግስት ፖሊሲ ቅድመ መከላከል ላይ መሰረት ያደረገ እንደ መሆኑ መጠን ህመሙን ለማከም ከመስራት ይልቅ ቅድመ መከላከል ላይ ከፍተኛ ትኩረት መሰጠት ይኖርበታል ብለዋል። 

ከሀገሪቱ ህዝብ ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት እድሜያቸው ከ15 አመት በታች ያሉ ህፃናት እንደመሆናቸው መጠን በትምህርት ቤቶች ከፍተኛ የግንዛቤ ፈጠራ መሰራት አለበት ለዚህ ደግሞ የጤናና የትምህርት አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ተነግሯል።