በከተማ አስተዳደሩ በኤች አይቪ ኤድስ ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ግምገማ እየተካሄደ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤች አይቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ጽህፈት ቤት ከአስሩ ክፍለ ከተሞችና ከመቶ አስራ ሰባት ወረዳዎች ባለድርሻ አካላት ጋር በአመቱ የተሰሩ የእቀድ ስራዎችና አፈፀፀማቸውን በተመለከተ ግምገማ እያደረገ ነው፡፡

የጽህፈት ቤቱ ሀላፊ ወ/ሮ ብርዛፍ ገብሩ በተለይ ለዋልታ እንደገለጹት፣ በዓመቱ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን በመጥቀስ በተለያዩ የቅንጅት መጓዳል ያልተሰሩና ቢሰሩም የሚቀሩ ስራዎች እንዳሉ አስረድተዋል፡፡

በኤች አይ ቪ ኤድስ ዙሪያ እየተረሳ የመጣውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

የባህሪ ተግባቦትና የሴተኛ አዳሪዎች ገቢ ማስገኛ ፕሮግራሞች ላይ  ሰፊ ስራዎች ቢሰሩም  በተለይ  የተለዋዋጭነት ባህሪ ስላለውና በሴተኛ አዳሪዎች ላይ ገቢ ሁኔታን የማመዛዘን ችግር ስላለ የሚፈለገውን ያህል ለውጥ ማምጣት አልተቻለም ነው ያሉት ኃላፊዋ፡፡

ለኤች አይቪ ተጋላጭ የሆኑ የህበረተሰብ ክፍሎችና  አካባቢዎች ላይ የተለያዩ ስልጠናዎች ተሰጥቷልም ብለዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም በደማቸው ውስጥ  ኤች አይ ቪ ኤድስ ያለባቸው ሰዎች አድሎና መገለል ይደርስብናል ብለው በመፍራት ወደቀድሞ አስተሳሰብ መመለስ መጀሩ እንደ ትልቅ ፈተና መሆኑን ወይዘሮ ብርዛፍ አክለው አብራረተዋል፡፡

በከተማው ውስጥ የሚገኙ 532 የሚሆኑ ተቋማት የኤች አይቪን ጉዳይ በመስሪያቤቶቻቸው አካተው እየሰሩ መሆናቸውን የጠቀሱት ሃላፊዋ፤ በከተማው ወደፊት ለውጥ ሊመጣ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

በየተቋማቱ ወላጅ አጥ የሆኑ ህፃናት እንክብካቤና በሰራተኞቻቸው ላይ የሚሰጡት ስልጠናዎች  አበረታች እንደሆነም የፅህፈት ቤቱ ሀላፊዋ ወ/ሮ ብርዛፍ ገበሩ ጠቁመዋል፡፡