የውሃ መያዣ ፕላስቲክ ዕቃዎች የዓለም የመጠጥ ውሃን እየበከሉ ናቸው-የዓለም ጤና ድርጅት

የዓለም ጤና ድርጅት የውሃ መያዣ ፕላስቲክ እቃዎች ምክንያት በሰው ጤና ላይ የሚከሰተውን ችግር አስመልክቶ ሪፖርት አቅርቧል፡፡

በተለይ የውሃ መያዣ ፕላስቲክ እቃዎች ጥቃቅን የሆኑ በካይ ነገሮችን እንደሚይዙ ነው የተገለጸው፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ባደረገው ጥናት መሰረት ችግሩ የምንጠጣውን ውሃ፣ የምንመገበውን ምግብ እና የምንተነፍሰው አየር እንደሚበክል ማወቅ ተችሏል፡፡

በዚህም ማይክሮፕላስቲክ እቃዎች ፀረመድሃኒት የሚቋቋሙ በሽታ አምጪ ባክቴሪያዎችን እንደሚሸከሙም በጥናቱ ቀርቧል፡፡

በተለይ እነኚህ ማይክሮፕላስቲክ እቃዎች የሚያደርሱት ብክለት በሰዎች ላይ የጤና ችግር ማሳደር ከጀመሩ ውለው ማደራቸው ነው በጥናቱ የተመላከተው፡፡

ጥናቱ በዋናነት በዚህ መልኩ የሚመጣን ብክለት ለመከላከል የሚያስችል ስራ ለማከናወን የሚያግዝ መሆኑን የዘርፉ አጥኚዎች ገልጸዋል፡፡ (ምንጭ፡-ሮይተርስ)