በከተማዋ ከ320 ሺህ በላይ ሰዎች የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል

በአዲስ አበባ ከ320 ሺህ በላይ ሰዎች የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል::

የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎትን ለማጠናከር እና የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ።

የአገልግሎት አሰጣጡን በተሻለ ደረጃ ለማሳደግ በተዘጋጀ ሀገራዊ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ረቂቅ አዋጅ ላይ ዛሬ ውይይት ተካሂዷል።

በአዲስ አበባ ከሁለት አመት በፊት የተተገበረው የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት እያደገ መምጣቱን የአዲስ አበባ ጤና መድህን ጽ/ቤት ስራ አሰኪያጅ አቶ ብርሃኑ አይካ ተናግረዋል።

እስካሁንም ከ320ሺህ በላይ ሰዎችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ መቻሉን ስራ አስኪያጁ አብራርተዋል።

በቀጣይም አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ጉልህ ሚና እንዳለው አቶ ብርሃኑ አክለዋል።

ረቂቅ አዋጁን በተመለከተ በቀረበ ማብራሪያ ላይም የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል።