የመድኃኒት አቅርቦትን ወደ 90% ከፍ ማድረግ መቻሉ ተገለጸ

በጤና ተቋማት ላይ ያለው የመድኃኒት አቅርቦት ከ59 በመቶ ወደ 90 በመቶ ከፍ ማድረግ መቻሉም ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ሰንሰለት በመድኃኒት አቅርቦት ላይ ያተኮረው 3ኛው ዓመታዊ የውይይት መድረክ በጎንደር ከተማ ተካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲው እየሰራቸው ካሉ ስራዎች መሀከል ለመድኃኒትና ለህክምና መሳሪያዎች የማእቀፍ ግዥ ማስጀመር አንዱ ሲሆን በዚህም በየአመቱ የሚወጣ የጨረታ ቁጥር ከ110 ወደ 45 የተቀነሰ ሲሆን ለጨረታ የሚወስደውን አማካኝ ጊዜ ከአንድ አመት ወደ 6 ወር ማውረድ ተችሏል::

በተጨማሪም ከመድኃኒትና ከህክምና መሳሪያዎች ማእቀፍ ግዥ 3.8 ቢሊዮን ብር ማትረፍ መቻሉም ታውቋል፡፡

51 አይነት የካንሰር መድኃኒት ግዥ እና አቅርቦት በማድረግ ላይ ይገኛል::

እነዚህንና ሌሎች ለውጦች በማስቀጠል አሁንም በየጤና ተቋማት የመድኃኒት አቅርቦት ለማሻሻል እና በቴክኖሎጂ የተጠናከረ የአቅርቦት ሰንሰለትን ለመፍጠር በይበልጥ ይሰራል ተብሏል::