በድሬዳዋ በችኩንጉኒያ በሽታ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 29 ሺህ መድረሱን የከተማው ጤና ቢሮ አስታወቀ

ከነሃሴ ወር ጀምሮ በድሬዳዋ በተከሰተው የችኩንጉኒያ በሽታ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 29 ሺህ መድረሱን የከተማው ጤና ቢሮ አስታወቀ።

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን በድሬዳዋ የበሽታውን ስርጭትና እየተደረገ ያለውን የመከላከል ስራ ተመልክተዋል።

የበሽታውን ስርጭት ለመግታት እየተደረገ ያለው ርብርብ ጥሩ ቢሆንም ህብረተሰቡ ለትንኝ መራቢያ ምቹ የሆኑ ዉሃ ያቆሩ ጉድጓዶችን እና ቁሳቁሶችን በማስወገድ ረገድ አሁንም ሰፊ የግንዛቤ ስራ መሰራት እንዳለበት ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ለችኩንጉኒያ በሽታ መከላኪያ የሚሆን የኬሚካል እና የበሽታው ማሰታገሻ መድሃኒቶች እየተሰራጩ ቢሆንም እጥረት መኖሩን ታካሚዎች ጠቁመዋል።

በከተማው እስካሁን 29 ሺህ ሰዎች በበሽታው የተያዙ ሲሆን፣ የሞተ ያለመኖሩን ማረጋገጥ ተችሏል::