የመጀመሪያው የወባ ክትባት በኬንያ ስራ ላይ ዋለ

ፍቱን እንደሆነ የተነገረለት  የወባ ክትባት ለመጀመሪያ በዛሬው ዕለት በኬንያ ስራ ላይ መዋሉ ተገልጿል፡፡

ክትባቱ በአፍሪካ አህጉር ደረጃ በጋና፣ ማላዊ እና ኬንያ ስራ ላይ እንደዋለም ነው የተገለፀው ፡፡

ክትባቱ በተጠቀሱት ሶስት ሀገራት እድሜያቸው ከሁለት ዓመት በታች ለሆነ 300 ሺህ ህፃናት በየዓመቱ  ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዓመት በወባ ምክንያት ለህልፈት ከሚዳረጉ 400 ሺህ ሰዎች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙ ህፃናት ናቸው፡፡

ክትባቱ ውጤታማ መሆኑን የገለፀው የዓለም የጤና ድርጅት ከክትባቱ  ጎን ለጎን የአጎበር ስርጭትና መድሃኒት የመርጨት ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስቧል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ