የጤና ሚኒስቴር የተቋሙን አዲሱን መለያ አርማና መሪ ቃል አስተዋወቀ

የጤና ሚኒስቴር የተቋቋመበትን ዓላማና ግብ ለህብረተሰቡ በቀላሉ ለማድረስ ይቻለው ዘንድ አዲስ መለያ ዓርማና መሪ ቃል በማዘጋጀት በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ይፋ አድርጓል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ የተቋሙን መለያ አርማና መሪ ቃል በተዋወቀበት ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ንግግር የተዘጋጀው አዲሱ መለያ አርማና መሪ ቃል የጤና ሚንስቴር ራዕይና ተልዕኮ መሰረት በማድረግ ህብረተሰቡን በርህራሄ ፣በቅንነት፣ በብቃት፣ በመተባበርና በቁርጠኝነት ላይ በመመስረት ለማገልገል ያለውን ተነሳሽነት የሚያሳይ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

ሚኒስትር ዴታዋ አያይዘውም የአዲሱ መለያ አርማና መሪ ቃል በዋነኛነት የጤና ሚኒስቴር ራዕይና ተልዕኮ የሆነውን ጤናማ እና አምራች ብቁ ዜጋን ማፍራት ተልዕኮን በብቃት ለመወጣት እንደሚያግዝ አብራርተዋል፡፡

በማስታወቂያ ፕሮግራሙ ላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመለያ አርማ ለውጥ የተቋሙን እሳቤዎች ማለትም ማህበረሰብን፤ መተባበርን፤ ርህራሄን፤ ቁርጠኝነትንና ብቃትን የሚያመላክቱ እንደሆነ ማብራሪያ ተሰጥቷል ፡፡