በአንድነት ፓርክ ውስጥ የድንገተኛ ህክምና መስጫ ማዕከል ተቋቋመ

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በታላቁ ቤተመንግስት ቅጥር ግቢ በተሰራው የአንድነት ፓርክ ውስጥ የድንገተኛ ህክምና ማዕከል አቋቋመ።

የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን እንደገለጹት፤ መስከረም 30 ቀን 2012 ዓ.ም ለህዝብ ክፍት በሚሆነውና በታላቁ ቤተመንግስት በተሰራው የአንድነት ፓርክ ውስጥ የድንገተኛ ጊዜ የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ ማዕከል ተቋቁሟል።

ይህ የህክምና ማዕከል የተቋቋመውም በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አማካኝነት መሆኑንም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል በአለምአቀፍ ደረጃ የአዕምሮ ጤና ቀን በመከበር ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ አመት የጤና ሚኒስቴር ትኩረት ሰጥቷቸው ከሚሰራቸው ስራዎች መሀከል የአዕምሮ ጤና ዋነኛው ሲሆን፤ በሚቀጥለው ሳምንት በሚካሄደው 21ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ የግምገማ መርሀ ግብር ላይ ከባለሙያዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በስፋት ውይይት እንደሚካሄድና ቀጣይ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ ይጠበቃል፡፡

በተመሳሳይ የአዕምሮ ጤና ኢንስቲትዩት በዚህ አመት ተከፍቶ ወደ ስራ ለማስገባት እንቅስቃስ መጀመሩን የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን በይፋ ማህበራዊ ገፃቸው አስፍረዋል፡፡