ታዋቂው ሳይንቲስት ስቴፈን ሃውኪን ለወደፊቱ የሚፈጠሩ ቴክኖሎጂዎች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ካልተደረገ የሰው ልጅን ህልውና ሊፈታተኑ እንደሚችሉ አስጠነቀቀ ።
ታላቁ የፊዚክስ ባለሙያ ከዚህ ቀደም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የላቀ እውቀት ለወደፊቱ የሰው ልጅን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል እየሆነ እንደሚመጣ መናገሩ የሚታወስ ሲሆን ለእያንዳንዱ ነገር ምክንያታዊ በመሆን በዓለም ላይ ትልቅ አደጋ ሊሆን የሚችለውን የባይሎጂካልና የኒኩሌር ጦርነት ስጋትን ማስቀረት ይቻላል ብለዋል ።
ቴክኖሎጂ በተራቀቀና በተሻሻለ ጊዜ የዓለም ህልውና የሚፈታታን በመሆኑ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላትና መንግሥታት በአመክንዮ የማመን ዕድሉን በማጎልበት የዓለምን ስጋት በቁጥጥር ሥር ማዋል ይገባቸዋል ብለዋል ።
ፕሮፌሰር ስቲቨን ሃውኪን ለጋርዲያን እንደገለጸው ዓለማችን ከምንም ጊዜ በላይ ብዙ የሚያሳስቧት ችግሮች ያጋጠሟት በመሆኑ የሰው ልጅ በአንድነት በመሆን ችግሮችን በመጋፈጥ በጋራ መሥራት ይገባዋል ብሏል ።
የዓለማችን ፈተኛ ከሆኑት መካከል የአየር ንብረት ለውጥ ፣ የምግብ ምርት ፣ የህዝብ ብዛት ፣ የተለያዩ ፍጥረታት መጥፋት ፣ የወረርሽኝ በሽታዎችና የውቅያኖስ በአሲድ መሞላት የዓለም ትልቅ ስጋት መሆናቸውን ሃውኪን አብራርቷል ።
በአሁኑ ወቅት የሰው ልጅ ሊኖርበት የሚችለው አንድ ፕላኔት መሬት ብቻ በመሆኗ የምንኖርባትን ፕላኔት ከውድመት ለመከላከል ሁሉም በጋራ መሥራት እንደሚጠበቅበት ሃውኪን አስረድቷል ።
የዓለም እውቁ የፊዚክስ ባለሙያ ሃውኪን በቅርቡ ሮቦት የሰው ልጅን ቢና ሮቦት እንዲተካው መደረጉ አለም ለሰው ልጆች ትልቅ ስጋት የሚደቅን መሆኑን ተናግሯል ። ( ምንጭ: ዴይሊሜል )