አሜሪካ በስምንት የመካከለኛው ምስራቅና የሰሜን አፍሪካ አገራት ጋር በምታደርገው በረራዎች ላይ የኤሌክትሮኒክስና እቃዎች እንዳይጓዙ የሚያደርግ እገዳን ልትጥል መሆኑ ተገለጸ ።
የአሜሪካ መንግሥት ምንጭ ለቢቢሲ እንደገለጸ በአሜሪካ ከ10 የአውሮፕላን ማረፊያዎች ዘጠኙ እገዳው የመቆጣጣር ኃላፊነት ይኖርባቸዋል ።
በእገዳው ከስምንት አገራት ላብቶፖች ፣ ታብሌቶች፣ ካሜራዎች ፣ ዲቪዲና ኤሌክትሮኒክ ማጫወቻዎች እንዳይገቡ እንደሚከለከሉ ተገልጿል ።
የአሜሪካ የአገር ውስጥ ደህንነት በጉዳዩ ላይ ያወጣው መረጃ ባይኖርም በሚቀጥለው ማክሰኞ መግለጫ እንደሚሠጥ ይጠበቃል ።
ባለቤትነቱ የዱባይ የሆነ የመንገደኞች አውሮፕላን ከሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በተነሳ በደቂቃዎች ጊዜ ውስጥ የፈነዳ ሲሆን በአደጋው ላይ ምርመራ ያደረጉ ሲሆን አደጋው የተከሰተው አንድ ላብቶፕ በያዘ ግለሰብ መሆኑ ተረጋግጧል ።
አውሮፕላኑን የሚያበረው ፓይለት ሁኔታውን በመገንዘብ አውሮፕላኑ መልሶ እንዲያርፍ በማድረጉ አውሮፕላኑን እንዳይወድም አስተዋጽኦ አድርጓል ።
አልሻባብ የቦንብ ፍንዳታውን በማቀድ በኩል ኃላፊነቱን የወሰደ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን አሜሪካውያን በምድራቸው እንደዚህ አይነት ጥቃት ሊቃጣ ይችላል የሚለው የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊዎችን እያሳሰበ ይገኛል ።
እግዳው በተመለከተ የአሜሪካ የሥራ ኃላፊዎች ዝርዝር ጉዳዮን ከማሳወቅ እስካሁን ተቆጥበዋል ።
የአሜሪካ መንግሥት በበረራ ወቅት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን የሚከለክለውን ህግ ሲያወጣ የአሜሪካ ተጓዦች ድህንነታቸው ለመጠበቅ እንደሆነ ሊያምኑ ይገባል ተብሏል ።
እገዳው የሚመለከታቸው በስምንት አገራት የሚገኙ 10 የአውሮፕላን ማረፊያ ኤርፖርቶች ሲሆኑ
1ኛ የአማን ጆርዳን የአውሮፕላን ማረፊያ ንግስት አሊያ አለም አቀፍ ማረፊያ
2ኛ የካይሮ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ
3ኛ የአታቱርክ የአውሮፕላን ማረፊያ
4ኛ የጅዳው ንጉስ አብዱላዚዝ ዓለም አቀፍ ማረፊያ
5ኛ የንጉስ ካህሊድ የሪያድ ማረፊያ
6ኛ የኩዌት ዓለም አቀፍ ማረፊያ
7ኛ ሞሐመድ 5ኛ የሞሮኮ ማረፊያ
8ኛ የሃማድ ዱሃ ማረፊያ
9ኛ የዱባይ ዓለም አቀፍ ማረፊያ
10ኛ የአቡ ዳቢ ዓለም አቀፍ ማረፊያ መሆናቸውን አሶሺትድ ፕሬስ ዘግቧል ።
በበረራ የእገዳው የኤሌክትሪኒክስ እቃዎችን እንጂ ተንቀሳቃሽ ስልኮችንና የህክምና መገልገያ የኤሌክትሪኒክስ እቃዎችን የማይጨምር መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን የጆርዳን የዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከአሁኑ ወደ ሰሜን አሜሪካ ለሚደረጉ በረራዎች አገዳውን ተግባራዊ ለማድረግ እተረንቀሰቀሰ መሆኑን ሲአን ኤን ኤን ዘግቧል ። ( ምንጭ : ቢቢሲ)