የሰው ልጅ አዕምሮን ከኮምፒውተር ሲሰተም ጋር የሚያገናኝ ቴክኖሎጂን የሚያመርት ኩባንያ ማቋቋሙን የቴሴላ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢሎን ሙስክ አስታወቀ ።
ዎል ስትሪት ጆርናል ከሙስክ የተላከለትን የቲዊተር መልዕክት ጠቅሶ እንደዘገበው አዲሱ ኩባንያ ኒውራል ሌስ የተባለ በሰው ልጅ አዕምሮ ውስጥ የሚተከል ቴክኖሎጂን ለማምረት የተቋቋመ ነው ።
ኩባንያው የሚያመርተው የኤሌክትሮድ ቅንጣት የሰው ልጅ የማስታወስ አቅምን የሚያሳድግ ሲሆን የሰው ልጅን ሠው ሰራሽ የማሰብ አቅምን በእጅጉ የሚያሳደግ ቴክኒካዊ ዘዴ ነው ።
ጆርናሉ በዘገባው በዓለም የአዕምሮና የኮምፒውተር ሳይንስ ተመራማሪዎች ከኩባንያው ጋር ለመሥራት ከወዲሁ እየተመዘገቡ መሆኑን ተያያዞ ተገልጿል ።
በዘርፉ ዕውቅ ተመራማሪዎች እንደሚገልጹት ለወደፊቱ የሰው ልጅ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ሃሳብን ወደ ራሱ አዕምሮ ማስገባትና ወደ ሌላም እንዲተላላፍ የሚያደርጉ ሁኔታዎች ይፈጠራሉ የሚል ግምት እንዳላቸው ተናግረዋል ።
ሚስተር ሙስክ እንደገለጹት ኩባንያው በሚቀጥለው ሳምንት መቋቋሙን ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግና ዝርዝር ሁኔታዎችን ግልጽ እንደሚሆኑ አስረድተዋል ።
ሚስተር ሙስክ በዋና ሥራ አስፈጻሚነት የሚመሩት ቴሴላ የተባለ ኩባንያ የመኪና ኤሌክትሪክ ሲስተሞችን በመሥራት የሚታወቅ ሲሆን በቀረብ ዓመታት በጠፈር ምርምር የሚያደርግ ስፔስ ኤክስ የተባለ ኩባንያ በመቋቋም አዲስ የጠፈር ትራንስፖርት ፕሮጀክትን በማከናወን ላይ ይገኛሉ ።
ሚስተር ሙስክ አሁን የጀመሩት የሰው አዕምሮና የኮምፒውተር ሲስተም የሚያገናኝ ኩባንያ መቼ ውጤታማ እንደሚሆን ለመወሰን ከባድና አደጋዎችም እንዳሉት ሊታወቅ ይገባል ተብሏል ። ( ምንጭ ቢቢሲ)