በመላው ዓለም በስፋት በጥቅም ላይ የዋሉ የአንድሮይድ ስልኮች በሚስጥር የሰው ልጆችን የግል ህይወት የተመለከቱ መረጃዎችን ያለፈቃድ የማስተላላፍ ክፍተት እንዳለባቸው አንድ ጥናት ጠቆመ ።
የአንድሮይድ ስልክ ተጠቃሚ የሆነ አንድ ግለሰብ ምንም ሳያውቅ የትቦታ እንደሚገኝ ፣ የሚያደርገውን የስልክ ልውውጡን በተመለከተና ሌሎች የግል ሚስጥሮቹን ለማወቅ በሚያስችል ሁኔታ በሌላ ግለሰብ መረጃዎቹ ሊበረበርበት እንደሚችል ጥናቱ አሳይቷል ።
በአንድሮይድ ስልክ ላይ የተጫኑ አፕሊኬሽኖች ፣ ድምጾችናሌሎች መጠቀሚያ ሶፍትዌሮች ሚስጥሮች አደጋ ላይ እንዲወድቁ ሁነታዎችን የሚፈጥሩ መሆናቸው ተገልጿል ።
ከአንድ መቶ በላይ በሚሆኑ የጎግል አፕሊኬሽኖች ላይ በተካሄደው ጥናት እንደታወቀው የስልክ ተጠቃሚዎች አፕሊኬሽኖችን አውርደው በሚጠቀሙበት ወቅት ከተጠቃሚው ፍቃድ ውጪ መረጃዎችን የመውሰድ ሁነታ ይታይባቸዋል ።
እንደ ማልዌር የመሳሰሉ አፕሊኬሽኖች ከአንዱ ስል ወደሌላው በሚላኩበት ጊዜ የተቀባዩን ቁልፍ መረጃዎች በመበርበር ለሚፈለገው ዓለማ ማዋል እንደሚቻል ጥናቱ አመልክቷል ።
በጎልግል ጥቅም ላይ ከወዋሉት 100ሺ የሚሆኑ ታዋቂ አፕሊኬሽኖች ውስጥ የጥናት ቡድኑ እንዳረጋገጠው 23ሺ 495 መረጃዎችን መበርበር የሚያስችሉ ጥንድ አፕሌኬሽኖች መሆናቸው ተጠቁሟል ።
አፕሊኬሽኖቹን የተኛውም ተጠቃሚ ካወረደ በኋላ የግል መረጃ ያለምንም ፈቃድ የግል መረጃን ለመበርበር ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራሉ ።
የጥናቱ ተንታኞች እንደሚናገሩት በአንድሮይድ ስልኮች ላይ የሚጫኑት አፕሊኬሽኖች እርስ በራሳቸው የሚናበቡና መረጃም የሚነግዱ መሆኑ ጥናቱ በጉልህ አሳይቷል ።