በጃፓን የካርበን አየር ተመጋቢ ተአምረኛ ህንጻ ተሰራ

ብዙዎችን ያስገረመው ህንጻ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ነውም ተብሎለታል፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ የሚመጣውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚችል ተአምረኛው ህንፃ በጃፓን ተገንብቷል፡፡

ህንፃው ታኦዡይንዩዋን ይባላል፤ ካርቦን ተመጋቢው ህንፃ ረቂቅ ችሎታ ባላቸው የስነ-ህንፃ ባለሙያዎች በፈረንጆች መስከረም 2017 ተሰርቶ እንደተጠናቀቀም ተነግሯል፡፡  በዓለማችን ከሚገኙ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች በአካባቢ ጥበቃው ወደር የለሽ ይሆናል ተብሎለታል፡፡

"ታኦዡይንዩዋን" የተባው ይህ ህንጻ በየወለሉ አራት ነጥብ አምስት ድግሪ እንደሚሽከረከርም ነው የተሰማው፡፡

ህንጻው የብዝሃ ሕይወትን ለመጠበቅ አልሞ ነው የተገነባው፡፡

ይህ ህንጻ በዙሪያው እና በውስጡ 23 ሺህ ዛፎች ያሉት ሲሆን ፤በዓመት ዓለምን የሚበክል 130 ቶን የካርቦንዳይኦክሳይድ ልቀትን መጥጦ ያቀራል ነው የተባለው፡፡

የስነህንጻ ባለሙያው ቪንሴንት ኮልባውት እንደሚሉት ራዕያቸው ከተሞችን የአረንጓዴ ልማት እና የስርዓተ ምህዳር ደህንነት መገለጫ እንዲሆኑ መስራት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

"ታኦዡይንዩዋን" ህንጻ የራሱ የመተንፈሻ አካላት ያሉት ሲሆን የአረንጓዴ ዘላቂ ልማትን ለመጠበቅ እና የመሬት መንቀጥቀጥን ለመከላከል የሚስችሉ ቴክኖሎጂዎች የተገጠሙለት እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

ተፈጥሯዊ እፅዋቶችን ጨምሮ ሌሎች የካርቦንዳይኦክሳይድን የሚመገቡ የህንጻ ክፍሎች የሚኖሩት ሲሆን፤ ሰሪዎችንም የፈተናቸው የግንባታው ክፍል ይህ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የፀሃይብርሃን፣ የእንፋሎት ሃይል እና የነፋስ ሃይል የሚቋቋሙ ቴክኖሎጂዎችን የተላበሰነው ፡፡

የህንጻውም ድረገቢም 6 ሺህ 60 ስኩዌር ሜትር በሚሸፍኑ እፅዋት የተሸፈነ ነው ፡፡