በቀጣይ ጊዜያት የሮቦት ቴክኖሎጂ ሰዎችን ሊተካ እንደሚችል አንድ ጥናት አመላከተ

በቀጣይ ጊዜያት የሮቦት ቴክኖሎጂ ሰዎችን ሊተካ እንደሚችል አንድ ጥናት አመላከተ፡፡

በጥናቱ መሠረት ሮቦቶች ሰውን የሚተኩ ማሽኖች ብቻ ሳይሆኑ አብሮ የሚሰሩ የስራ አጋር እንደሚሆኑ ነው ጥናቱ ያመላከተው፡፡

የሮቦት ቴክኖሎጂ የሰዉ ልጆችን በመተካት የተለያዩ ተግባራትን ሲከዉኑ ማየት ዛሬ ላይ ብዙም አስደናቂ አይደለም፡፡

ሮቦቶች ከከባዱ የውትድርና ስራ ጀምሮ በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ዉስጥ የሰዉ ልጆች የሚሰሯቸዉን መደበኛ ስራዎች መከወን መቻላቸዉ በርካታ ሰዎች ስራችንን ልንቀማ ነዉ የሚል ስጋት ዉስጥ እንዲገቡ እንዳደረጋቸው ይገለፃል፡፡

በጥናቱ ከተካተቱት ሰራተኞች መካከል የቴክኖሎጂ መዘመንና የሮቦቶች መምጣት ስራችንን ይሻማል ያሉት 9 በመቶዎቹ ብቻ ሲሆኑ 4 በመቶዎቹ ያክል ደግሞ የቴክኖሎጂዉ መዘመን በስራቸዉ ላይ ሊያመጣ የሚችለዉን ተፅእኖ እንደማይረዱት ተናግረዋል።

አለም አቀፉ የሮቦት ፌዴሬሽን ያወጣዉ ሳይንሳዊ ግምት እንዳመላከተዉ ከሆነ እስከ ቀጣዩ የፈረንጆቹ 2020 ድረስ 3 ሚሊዮን ያህል ሮቦቶች በተላያዩ የአለም ክፍል በፋብሪካዎች ዉስጥ ስራ ላይ ይዉላሉ ተብሏል።

በሰዉ ኃይል ዙሪያ በተደረገ ጥናት መሰረትም በቀጣዩ 2020 የፈረንጆቹ አመት 84 በመቶ የሚሆኑት ተቋማት የሰዉ ሃይላቸዉን ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አሰራርን እንዲለምዱ ለማድረግ ያሰቡ ሲሆን ይህም 2011 የፈረንጆቹ አመት 21 በመቶ ከነበረዉ አሃዝ ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ይሆናል ተብሏል።

በማኑፋክቸሪንግና ማምረቻ ዘርፎች የተሰማሩ ሮቦቶች ከፍተኛ ጉልበት የሚጠይቁትን የእለት ተዕለት ስራዎች በተሳካ ሁኔታ ማከናወን በመጀመራቸዉ ከዚህ በኋላ አብዛኞቹ የማምረቻ ተቋማት ከጉልበት ሰራዎች ይልቅ የተግባቦት ብቃት በሚጠይቁት የኮሚዩኒኬሽን፣ የአመራርና ሌሎች ተመሳሳይ ስራዎች ላይ ብቻ ሰራተኞች ይቀጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡  (ምንጭ፡ቲ አር ቲ)