በኢትዮጵያውያን የተነደፉ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ወደ ገበያ የሚገቡበትን መንገድ ለማመቻቸት ያለመ ወርክሾፕ ተዘጋጀ

በኢትዮጵያውያን የተነደፉ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ወደ ገበያ የሚገቡበትን መንገድ ለማመቻቸት ያለመ ወርክ ሾፕ ተዘጋጅቷል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በቻይና ቁጥር አንድ የቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ከሆነው ቺንጉሃ የኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የተነደፈ (designed in Ethiopia) ፕሮጀክት ወደ ፊት ለማራመድ እና ፕሮቶታይፖችን በማውጣት ወደ ገበያ ገብተው ጥቅም ላይ የሚውሉበትን መንገድ ለማመቻቸት ከዩኒቨርስቲው ከመጡት ልኡካን ጋር ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ወርክሾፕ አዘጋጅቷል።

ከዚህም በተጨማሪ በወርክሾፑ በቻይና ሸንዘን ኢኮሲስተም ውስጥ ያሉ በኢትዮጵያ ለተነደፈ ፕሮጀክት ድጋፍ የሚያደርጉ እድሎችን ለፈጠራ ባለሙያዎች ያስተዋውቃል ተብሏል።

በጋራ የሚሰሩበት ሁኔታዎች ላይም ውይይት እንደሚያደርጉም ተገልጿል። 

ሽንዘን በኤሌክሮኒክስና ሀርድ ዌር ዲዛይን አሸናፊ ለነበሩ በኢትዮጵያ የተነደፈ አሸናፊዎች የኤሌክሮኒክ ኪት እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው የቁሳቁሶችን ስጦታ አበርክቷል። (ምንጭ፡-የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር)