አፕል በድምፅ የሚታዘዝ የድምፅ ማዳመጫ ይፋ አደረገ

አፕል ኩባንያ ተጠቃሚዎች በድመፅ ማዘዝ የሚችሉት ገመድ አልባ ድምፅ ማዳመጫ ወይንም ኢርፎን ይፋ አደረገ፡፡

ይህም ተጠቃሚዎች ምንም አይነት ነገር ሳይጫኑ  ሃይ ሲሪ የሚል ድምፅ በማሰማት ብቻ የድምፅ ማዳመጫውን ማዘዝ እንደሚችሉ ነው የተነገረው፡፡

ከዚህ ባለፈ ኤርፖድስ የተባለው ገመድ አልባ ድምፅ ማዳመጫ ተጠቃሚዎች ባትሪ ካለቀባቸው እንዲያስተካክሉ ተጨማሪ ሰዓትን በቅድሚያ እንደሚሰጥ ነው የተነገረው፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት የሰጡ ባለሙያዎች  ኤርፖድስ የተሰኘው የድምፅ ማዳመጫ በእጅጉ እየዘመነ መምጣቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

ይህ አዲሱ ድምፅ ማዳመጫ 159 የአሜሪካ ዶላር የሚያወጣ ሲሆን ገመድ አልባ ቻርጀርን የሚያካትት ከሆነ ተጨማሪ 40 ዶላር ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

(ምንጭ፡-ቢቢሲ)