የአሜሪካው ሶፍትዌር ኩባንያ በኢትዮጵያ ማዕከሉን የመክፈት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

ተቀማጭነቱ ካሊፎርኒያ ውስጥ ያደረገው ኢ ኦ ኤን ሪአሊቲ የተባለው የሶፍትዌር አምራች ኩባንያ በኢትዮጵያ ውስጥ ማዕከሉን የመክፈት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ፡፡

የኢ ኦ ኤን ኩባንያ መስራች ዳን ለጀርስካር ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ ኩባንያው በኢትዮጵያ ማዕከሉን የመክፈት ፍላጎት መኖሩን ተናግረዋል፡፡

ፕሮፌሰር ሂሩት በበኩላቸው የቴክኖሎጂውን አስፈላጊነትና ወቅታዊነትን በመገንዘብ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከኩባንያው ጋር በትብብር እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

(ምንጭ፡-የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር)