ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቻይና እርዳታ ለማምጠቅ በዝግጅት ላይ ያለችውን የኢትዮጵያ ሳተላይት ጎበኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቻይና እርዳታ በሚቀጥለው አመት ለማምጠቅ በዝግጅት ላይ ያለችውን የኢትዮጵያ ሳተላይት ጎበኙ፡፡

በኢትዮጵያ የሕዋ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት ሥር ሳተላይትን በማደራጀት በቻይና መንግሥት እርዳታ ወደ ጠፈር በሚቀጥለዉ አመት መጨረሻ ለማምጠቅ በዝግጅት ላይ መሆኗ ተገልጿል።

ሳተላይቷ ለግብርና ዕቅድ፣ ለድርቅ ቅድመ ጥንቃቄና ለደን አስተዳደር፣ የአየር ንብረት ሁኔታን ለመተንበይ እንደምታገለግል ነው የተገለጸው፡፡

(ምንጭ፡-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)