“ኢትዮጵያ ኢኖቬት” የቴክኖሎጂ ሳምንት ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ይጀመራል

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር “ኢትዮጵያ ኢኖቬት” በሚል ርዕስ አገር አቀፍ የቴክኖሎጂ ሳምንት ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሊኒየም አዳራሽ ያዘጋጃል፡፡ 
ከግንቦት 29/2011 እስከ ሰኔ 05/2011 ዓ.ም በሚካሄደው ሁነት ላይ ታላላቅ ዓለም አቀፍና አገር አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።
የአይሲቲ ኤክስፓ፣ የስታርት አፕ ውድድር፣ የሳይንሰ፣ ኢኖቬሺን እና ቴክኖሎጂ ሽልማትና እውቅና እንዲሁም የዲጂታል አፍሪካ ጉባኤ ዐበይት ይዘቶች ናቸው። 
በአይሲቲ ኤክስፖው የመረጃ ቴክኖሎጂ ውጤቶችና ባለሞያዎች ከጎብኝዎች ጋር ይገናኛሉ። 
የዚህን ዓይነተ ልዩ የቴክኖሎጂ ሳምንት ክዋኔዎች ከመክፈቻው እስከ ማጠናቀቂያው ድረስ በሚሊኒየም አዳራሽና ተያያዥ ፕሮግራሞች በሚከናወኑበት ዕለት ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ መሆኑን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡