የፌዴራል ሰራዊቱን የሬድዮ መገናኛ ስርዓት ያዘምናል የተባለለት የድጅታል ቴክኖሎጂ ይፋ ሆነ

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የፌዴራል ሰራዊቱን የሬድዮ መገናኛ ስርዓትት ያዘምናል የተባለለትን የድጅታል ቴክኖሎጂ ይፋ አደረገ፡፡

ይህ ቴክኖሎጂ ከዚህ ቀደም ይስተዋል የነበረውን የመቆራረጥ ችግር እና ሚስጥር የመጠበቅ ችግር ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙ የፌዴራል ፓሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻዉ ጣሰዉ እንደተናገሩት፤ ቴክኖሎጂዉ የሬድዮ መገናኛ ሰርዓቱን ያዘምናል እንዲሁም በሬድዮ ዘርፍ ከፍተኛ የተገናኛ የተባለለት ነዉ፡፡

መቶሮላ ሶልሽን ካምፓኒ ዋና ሀላፊ የሆኑት ሚስተር ያቫን ሃናን በበኩላቸው፤ ቴክኖሎጂውን እንደ አሜሪካ እና አዉሮፓ የመሳሰሉ የሰለጠኑ ሀገሮች የሚጠቀሙበት መሆኑን ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያዊን ቴክኖሎጂውን በመቀላቀላቸዉ እንኳን ደስ አላቹ የሚል መልእክት አሰተላልፏል፡፡

ይህ ቴክኖሎጂ ለድንገተኛ አደጋ  አገልግሎት የሚዉሉ  የእሳት አደጋ ሰርቢሶችን ሊጠቀሙበት እንደሚችሉም አንስተዋል፡፡

የቴክኖሎጂዉን አጠቃቀም ለ16 የሬድዮ ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች ለ አንድ ወር ያህል በመቶሮላ ሶልሽን አማካኝነት ሰልጠና ወስደዋል፡፡