አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የኤሌክትሪክንና የፀሃይ ሃይልን በቅንጅት የሚጠቀም የዶሮ እንቁላል መፈልፈያ ኢንኩቤተር ሰራ

የኤሌክትሪክንም ሆነ  የፀሃይ  ሃይልን በቅንጅት መጠቀም የሚችል የዶሮ እንቁላል መፈልፈያ ኢንኩቤተር አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ሰርቷል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የመካኒካል እና ፕሮዳክሽን ትምህርት ክፍል የተሰራው የእንቁላል መፈልፈያ የውጭ ምንዛሬን የሚያድን ነው ተብሏል፡

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከውጭ የምታስገባው ኢንኩቤተር  በፀሃይ አልያም በኤሌክትሪክ ሃይል ብቻ የሚሰራ ነበር፡፡

አምሳለ ቅርፁን ይፋ ያደረገው ኢንኩቤትር ግን ሁለቱንም የሃይል አማራጮችን በአንድ ጊዜ መጠቀም የሚችል ነው፡፡

ኢንኩቤተሩ በኤሌክትክ ሃይል እየሰራ መብራት ቢቋረጥ  ቴክኖሎጂው ያለምንም የሙቀት መቆራረጥ የፀሃይ ሀይልን መጠቀም  የሚችል ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በዝቅተኛ ወጭ ከመሰራቱም ባለፈ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬን የሚያድን ነው፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ  ቴክኖሎጂውን በገንዘብ ለመደገፍ የባለቤትነት መብት ለማውጣትና ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡