ሁዋዌ ቴክኖሎጂስ በራሱ ባለሙያዎች የተሠራ ሆንግ ሜንግ የተሰኘ አንድሮይድን የሚተካ አዲስ መተግበሪያ ያለው ስማርት ስልክ ሙከራ አደረገ።
አዲሱ ስማርት ስልክ በተያዘው 2019 የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ላይ ለገበያ ሊቀርብ ይችላል ሲል ግሎባል ታይምስ የተሰኘው የሀገሪቱ መንግሥት ሚዲያ ዘግቧል።
የአሜሪካ መንግሥት ቻይና የጎግል አንድሮይድ መተግበሪያ እንዳትጠቀም ማዕቀብ መጣሉን ተከትሎ፣ ሆንግ ሜንግ መተግበሪያ ላይ የተመሠረተው ስማርት ስልክ ይፋ መሆን ለሁዋዌ ትልቅ እምርታ ነው ተብሏል።
አዲሱ ስማርት ስልክ 288 የአሜሪካ ዶላር ያወጣል ተብሏል፡፡ ይህም በገበያ ላይ ከሚገኙት ስማርት ስልኮች አንጻር ዋጋው አነስተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡ (ምንጭ፡-ሮይተርስ)