የ8 ዓመቷ ሜክሲኳዊት የፀሐይ ኃይልን የሚጠቀም የውሃ ማሞቂያ በመሥራት የኒዩክሊየር ሳይንስ ሽልማትን ተቀዳጀች

ሜክሲኳዊቷ የ8 ዓመት ታዳጊ የፀሐይ ኃይልን የሚጠቀም የውሃ ማሞቂያ በመሥራት የኒዩክሊየር ሳይንስ ሽልማትን መቀዳጀት ችላለች፡፡

በሜክሲኮዋ ቺፓስ ነዋሪ የሆነችው እና  ዞችት ጓዳሉፔ  የተሰኘችው ታዳጊ በአካባቢዋ የሚገኙ ማህበረሰቦች ውሃ ለማሞቅ ደንን መመንጠራቸው ይህን የፈጠራ ውጤት ለመስገኘት ደፋ ቀና እንድትል እንዳደረጋት ትናገራለች፡፡

ካልቸራ ኮለክቲቫ የተሰኘው የዜና ምንጭ እንዳስታወቀው ታዳጊዋ ሽልማቱን ናሽናል ኦቶኖመስ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሜክሲኮ ከተሰኘው አንጋፋ የሜክሲኮ ዩኒቨርሲቲ ነው የተበረከተላት፡፡

የታዳጊዋ የፈጠራ ግኝት በድጋሚ ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጎ ዳግም መሰራት የሚችል መሆኑ ይበልጥ አድናቆት እንዲቸራት አድርጓል፡፡

በፀሐይ ኃይል የሚሠራው ይህ የውሃ ማሞቂያ ለአካባቢ ጥበቃ እና በመላው ዓለም  በማገዶ ላይ ጥገኛ ለሆኑ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች ከፍተኛ እገዛ ይኖረዋል ተብሏል፡፡

የታዳጊዋ ቤተሰብ የፈጠራው ቀዳሚ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል ያለው የዘ ሳይንስ ኒውስ ሪፖርተር ዘገባ ታዳጊዋን ከመሰሉ የፈጠራ አቅም ካላቸው  የእድሜ እኩዮቿ ጋር መጪው ጊዜ ብሩህ  እንዲሆን አስችሏል ብሏል፡፡

http://www.thescinewsreporter.com/2019/08/8-year-old-mexican-girl-wins-nuclear.html