በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ አህጉራዊ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ንቅናቄ በጥቅምት ወር በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለጸ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአይቢኤ ኢትዮጲያና ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ አህጉራዊ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ንቅናቄ ‹‹አፍሪካ ኢኖቬሽን ሳምንት›› በሚል ርዕስ ከጥቅምት 17 እስከ ጥቅምት 22/2012 ድረስ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

ስለሆነም ችግር ፈቺ፤ ሀብት ፈጣሪና ወደ ምርትና አገልግሎት ሊቀየር የሚችል የፈጠራ ስራ ያላቸሁ አካላት በዚህ አህጉራዊ መድረክ ላይ ሀገራቸውን ወክለው እንዲወዳደሩና የፈጠራ ውጤቶቻቸሁን ለውጭና ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች፣ ለቬንቸር ካፒታል ተቋማት እና ለሌሎች የፋይናስ ምንጮች በማስተዋወቅ ወደ ምርትና አገልግሎት እንድቀላቀሉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

 
በዚህም ትኩረት የሚሰጣቸው ዘርፎች የተጠቆሙ ሲሆን፣ ዘመናዊ ከተሞች እና አዳዲስ የመኖሪያ ቴክኖሎጂዎች፣ ዲጂታላይዜሽን፣ የኢንተርኔት ንግድ ስርዓት፣ የግብርና፣ የጤናና የህክምና ቴክኖሎጂ፣ መስተንግዶና ቱሪዝም፣ የማምረቻና እና የማዕድን ኢንደስትሪ ዘርፎች መወዳደር እንደሚቻል ተገልጿል፡፡

ስራዎቻቸውን በኢኖቬሽን ሳምንቱ ማስተዋወቅ የሚፈልጉ አመልካቾች የፈጠራ ስራ ፕሮፖዛላቸውን በ Registration@africainnovationweek.com በተሰኘው የኢሜይል አድራሻ ላይ በመላክ መመዝገብ እንደሚቻል ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡