ከተፈቀደው በላይ ድምፅ የሚያወጡ መኪኖችን የሚቆጣጠር የድምፅ መቆጣጠሪያ ራዳር በስራ ላይ ሊውል ነው

ከተፈቀደው በላይ ድምፅ የሚያወጡ መኪኖችን የሚቆጣጠር ከዓለማችን የመጀመሪያው የድምፅ መቆጣጠሪያ ራዳር በፈረንሳይ ስራ ላይ ሊውል ነው፡፡

በፓሪስ አንዲት መንደር በዓለማችን የመጀመሪያውን የድምፅ ብክለት መቆጣጠሪያ ራዳር በመትከል ከፍተኛ ድምፅ የሚያወጡ መኪኖችን ለመቅጣት ማሰቧ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

በዓለም ላይ እስካሁን ለመኪኖች ተግባር ላይ እየዋለ ያለው ከተፈቀደው የፍጥነት መጠን በላይ የሚጓዙ መኪኖችን አደብ የሚያስይዝ የፍጥነት መቆጣጠሪያ ራዳር በመትከል ነበር፡፡

ቪሌኔውቭ ሌሮይ የተባለችው የፓሪስ መንደር ግን፤ የድምፅ ብክለት ለኗሪዎች ከባድ ሆኗል በሚል አዲስ የተባለውን የድምጽ ብክለት መቆጣጠሪያ ራዳር በመትከል ችግሩን ለመቋቋም አዲስ ዜዴ ይዛ ብቅ ብላለች፡፡

ለድምፅ መቆጣጠሪያነት የተተከለሉ መሳሪያዎች የሚያጓራ ድምፅ የሚያወጡ ተሽከርካሪዎችን ለይተው በማውጣት በቀጥታ የቅጣት ትኬት የመላክ አቅም እንደሚኖራቸውም ተመልክቷል፡፡

አራት የመናገሪያ ማይኮችን የያዙት እያንዳንዱ አዲሱ የፈጠራ ውጤት በየአስር ሰኮንዱ ከየመኪኖቹ የሚወጡ ድምጾችን በመሰብሰብ ከየትኛው መኪና እንደሆነ በማገናዘብ የቅጣት ውሳኔውን ያሳልፋል፡፡

በዚህም መኪኖች የሞተራቸውን ይዘት እንዲፈትሹና የአነዳዳቸውን ሁኔታ ለነዋሪዎች በተመቸ እንዲሆን የሚያስችል የፈጠራ አካል ህግ ነውም ተብሏል፡፡

ይሁንጂ ይህን አሰራር የሚፈቅድ የፈረንሳይ ህግ ባለመኖሩ የህግ መንግስት ማሻሻያ እስከማድረግ የሚጠይቅ መሆኑ ጉዳዩን ቀልብ ሳቢ አድርጎታል፡፡

በመሆኑም ጉዳዩ በመንግስት እውቅና አግኝቶ ረቂቅ እስከመዘጋጀት ደርሷልም ተብሏል፡፡

በዚህም ረቂቅ ህጉ አካባቢያዊ መንግስታት በድምፅ መቆጣጠሪያ ራዳሩ ድምፅ መቅረፅና ከተፈቀደው መጠን በላይ ድምፅ የሚያወጡ መኪኖችን የመቅጣት እድል ይፈጥርላቸዋል ተብሏል፡፡

በሙከራ ደረጃ እስከ 50 የሚደርሱ የድምፅ መቆጣጠሪያ ራዳር የተተከሉ ሲሆን ለሁለት ዓመት ያህል ህጉ ይፋ እስከሚሆንም ጭምር ወደ ተግባር ሳይገባ በሙከራ ደረጃ ይቆያል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ (ምንጭ፡-ሮይተርስ)