ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ገለጸ

ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ገለጸ።

አመታዊው የአፍሪካ አካታች የኢኖቬሽን ስብሰባ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ የተካሄደ ሲሆን፣ በመድረኩ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኑስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከተለያዩ የአለም ሀገራት የተውጣቱ ባለ ድርሻዎች ተካፍለዋል።

ከመላው አፍሪካ የተውጣጡና ለ1ሚሊየን ዶላር ሽልማት የሚወዳደሩ ለዙሩ የደረሱ 8 ጀማሪ ቴክኖሎጂስቶች ስራዎቻቸውን በመድረኩ አቅርበዋል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታው ጀማል በከር ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን አብራርተዋል።

መንግስት የቴክኖሎጂው ዘርፍ የስራ እድል እንዲፈጥር፣ የግል የቴክኖሎጂ ካምፓኒዎች እንዲጠናከሩና የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡና ለወጣቶች የስራ እድል እንዲፈጥሩም እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

መድረኩን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የኬኒያው የቴሌኮም ካምፓኒና "ኤም አይ ቲ" በጋራ ነው ያዘጋጁት፡፡

በመድረኩ የፓናል ውይይቶችና የተለያዩ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት መደረጉን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡