ደቡብ እና ሰሜን ኮሪያ ድንበር ላይ የ5ጂ ኔትወርክ መንደር ተከፈተ

ደቡብ እና ሰሜን ኮሪያ በሚዋሰኑበት ከጦር እንቅስቃሴ ነፃ ቀጠና ክልል ውስጥ የ5ጂ ኔትወርክ መንደር ተከፍቷል፡፡

በቀጠናው የ5ጂ መንደር መቋቋሙ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያለውን የኒዩክሌር ፍጥጫ ለማርገብ ፍንጭ የሚሰጥ ነውም ተብሏል።

በዓለም ላይ የሚገኙ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ኩባንያዎች ባለ 5ጂ ቴክኖሎጂ ለማስፋፋት ውድድር ላይ በሚገኙበት በዚህ ወቅት የደቡብ ኮሪያዋ መንደር ይህንን ዕድል በማግኘት የመጀመሪያዋ ሆናለች።

መንደሯን ልዩ የሚያደርጋት ደግሞ ሰሜን እና ደቡብ ኮሪያን በሚለያቸው ከጦር እንቅስቃሴ ነፃ ቀጠና ክልል ውስጥ የምትገኝ መሆኗ ነው ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።