ፌስቡክ ሀሰተኛ መረጃ መለየት የሚያስችል ፕሮግራም በኢትዮጵያ መጀመሩን ገለፀ

 የፌስቡክ ኩባንያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ10 የአፍሪካ ሀገራት ሀሰተኛ መረጃዎችን መቀነስ የሚያስችለውን የሶስተኛ ወገን የትክክለኛነት ማረጋገጫ ፕሮግራም (Third-Party Fact-Checking Program) መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ኩባንያው ፕሮግራሙን ካስጀመረባቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን ጨምሮ ዛምቢያ፣ ሶማሊያ፣ ቡሪኪና ፋሶ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኮትዲቯር፣ ጊኔ ኮናክሪ እና ጋና ይገኙበታል፡፡

ሶስተኛ ወገን የመረጃ ትክክለኛነት ማረጋገጫ ፕሮግራም ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመግታት የሚያስችል እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በዚህም የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በማህበራዊ ሚዲያው ጥራት ያለው መረጃ የሚያገኙበትን አሰራር የሚያሻሽል እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ (ምንጭ፡-ፌስቡክ)