የ”መሬት ወረራ” እንቶፈንቶ ሲገለጥ

 

ለግብርና ልማት ሊውል የሚችል ሰፋፊ መሬት ያላቸው የአፍሪካ፣ የላቲን አሜሪካ፣ ኤዥያና ምስራቅ አውሮፖ ሀገራት የተፈጠረውን ምቹ አለማዊ ሁኔታ ተጠቅመው መሬታቸውን ለማልማት የሚያደርጉትን ጥረትና በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ለበርካታ ዓመታት ኢንቨስትመንት በተጠማው የግብርና መስክ ኢንቨስት ለማድረግ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ተከትሎ በርካታ አስተያየቶች እየተንፀባረቁ ይገኛሉ፡፡ በሰፋፊ የእርሻ ኢንቨስትመንት ረገድ እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተ በእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ማስፋፋት ከመፈረጅ ጫፍ የወጣ አቋም ጀምሮ በአካባቢ ማህበረሰብ መብትና በአካባቢ ጥበቃ ስም በርካታ አስተያየቶችና አቋሞች በዓለም የመገናኛ ብዙሀን፣ የሰብዓዊ መብት ጠበቃ ነን በሚሉና የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪ ነን ባዮች በየዕለቱ የሚደመጡ መሆን ከጀመረ ውሎ አድሯል፡፡

በጽንፈኛ የኒዩ-ሊበራሎች አዝማችነት ከላይ በተጠቀሱት አካላት የሚሰነዘሩ ትችቶች ጠቅለል ተደርገው ሲታዩ የሚያተኩሩባቸው ጭብጦች የሚያጠነጥኑት በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ የመጀመሪያው መሬት ለውጭ ባለሀብቶች እየተሸጠ የመሬት ወረራና የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ እየተስፋፋ ነው የሚል ነው፡፡ ሁለተኛው ሀገሮች  ለውጭ ባለሀብቶች መሬት በተለያየ የስምምነት አግባብ ሲያስተላልፉ በተለይ ደግሞ እነኝህ ሀገሮች ብዙዎቹ የምግብ ዋስትናቸው ያልተረጋገጠ ስለሆነ ብሄራዊ የምግብ ዋስትና እንዳይረጋገጥ እያደረገ ነው የሚል ነው፡፡ ይህን ጉዳይ አንዳንዴም በሚያሳፍር ሁኔታ ከድርቅ ችግር ጋር ሲያያይዙትም ይስተዋላል፡፡ በሦስተኛ ደረጃ የሚያስተጋቡት ጉዳይ መሬት ለባለሀብቶች የሚተላለፈው የአካባቢው አርሶ አደርና አርብቶ አደር እንዲፈናቀል በማድረግ  ነው የሚል ነው፡፡ በመጨረሻ የሚያነሱት መሬት ለሰፋፊ እርሻ እንዲውል ሲደረግ በአካባቢው ስነ-ምህዳር ላይ ጉዳት በሚያስከትል አግባብ ነው የሚል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡  ለእነኝህ ትችቶች ትኩረት መስጠታችንና ይዘታቸውን ፈትሾ ማጋለጥ የመምረጣችን ምክንያት ትችቶቹ ሀገራችን በምታካሂደው የሰፋፊ እርሻ ልማት ላይ ተነጣጥረው የሚሰነዘሩበት ሁኔታም ስላለ ነው፡፡ ትችቶቹ ተወስደው ሲመረመሩ ከላይ ቀለም ተቀባብተው የሰሚን ጆሮ እንዲስቡ ተደርገው አሳቢና ተቆርቋሪ በመምሰል የሚሰነዘሩ፣ ገለጥለጥ ተደርገው ሲታዩ እውነታን ያልያዙ፣ በይዘታቸውም ልማታዊ ያልሆኑ ይልቁንም ልማትን የሚያደናቅፉ መሰናክሎች የታጨቁባቸው ሆነው ይገኛሉ፡፡ ይህንኑ ለመረዳት ዘርዘር አድርጎ ማየቱ ጠቃሚ ነው፡፡

በቅድሚያ የሰፋፊ እርሻ ልማት የሚመሠረትበትን መነሻ ከፖሊሲና ስትራቴጂዎቻችን ጋር በማስተሳሰር እንዲሁም ለሰፋፊ እርሻ ማስፋፋት አቅጣጫ በአሁኑ ጊዜ ትኩረት ሰጥተን የምንረባረው ለምንድነው? የሚሉትን በማየት ጀምረን፣ በልማቱ ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶችን አንድ በአንድ ማጋለጡን አስከትለን  አብረን እንዝለቅ፡፡

የገጠር ልማት ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና ስልቶች በተተነተኑበት ሰነዳችን እንደተገለፀው በገጠር ልማትን ከማረጋገጥ አኳያ ልንከተላቸው የሚገቡን አቅጣጫዎች አስቀድመው ተመልሰዋል፡፡ ሰነዱ ግልጽ አቅጣጫ ካስቀመጠባቸው ጉዳዮች አንዱ በህገ-መንግስቱ ላይ የሰፈረውን የመሬት ይዞታ ፖሊሲ ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡ በህገ-መንግስቱ መሬት የህዝብ ንብረት ሆኖ በመንግስት እንደሚተዳደር ተደንግጓል፡፡ በዚህ ላይ በመመስረት ያልታረሰ ሰፊ መሬት ባለባቸው ምዕራባዊ ቆላማ የአገራችን አካባቢዎች የጉልበትን ምርታማነት የሚያሳድግ የቴክኖሎጂ አማራጭ በመጠቀም ሰፋፊ እርሻዎችን በግል ባለሀብቶች ተሳትፎ ማስፋፋት እንደሚገባ፣ ይህን በማድረግ ረገድም የሀገር ውስጥ ባለሀብቶችን መደገፍና ተሳትፏቸውን ማጎልበት ትኩረት የሚሰጠው ቀዳሚ ተግባር መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ሀገራችን የካፒታል እጥረት ያለባት በመሆኑ የውጭ ኢንቨስተሮችን ወደ ግብርና መሳብ እንደሚያስፈለግ በማያሻማ ሁኔታ ተመላክቷል፡፡ እዚህ ላይ ይህን ማንሳት ያስፈለገው የፖሊሲውን ይዘት ለመተንተን ተፈለጎ ሳይሆን የሰፋፊ እርሻ ልማት ዕቅዳችን ዛሬ በድንገት ያነሳነው አጀንዳ ሳይሆን ቀድሞውንም በገጠር ልማት ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና ስልቶች ተመልሶ ያደረ ጉዳይ መሆኑን ለማስረገጥ ነው፡፡

ከግሉ ባለሀብት የግብርና ልማት ተሳትፎ ጋር ተያይዞ የሰፋፊ እርሻ ልማት አቅጣጫችን ቀደም ብሎ የሚታወቅና ግልጽነት የተያዘበት ጉዳይ ነው ተብሎ ሊወሰድ ይችላል፡፡  ነገር ግን የሰፋፊ እርሻ ልማት አቅጣጫችንን ለመፈፀም ይህን ጊዜ ለምን መረጥን የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ አቅጣጫውን ብናስቀምጥም አቅጣጫውን ለመፈፀም መሟላት ያለባቸው ገና አቅጣጫው ሲቀመጥ ጀምሮ የተዘረዘሩ ሁኔታዎች መኖራቸውን ነው፡፡ ያልታረሰ ሊለማ የሚችል ሰፊ መሬት ያለባቸው አካባቢዎች ከመሠረተ ልማት ርቀው የሚገኙ በመሆናቸው መሬቶቹን ለማልማት ሰፊ የመሠረተ ልማት ግንባታ ሥራ ይጠይቃል፡፡ አካባቢዎቹ ሰው በብዛት ያልሰፈረባቸው በመሆናቸው ለሰፋፊ እርሻ ልማት የሚያስፈለገውን መጠነኛ የጉልበት ፍላጎት ማሟላት የሚቻልበት ሁኔታ ዝቅተኛ ነበር፡፡ ከነኚህ እውነታዎች በተጨማሪ ሀገራችን የካፒታል እጥረት ያለባት በመሆኑ ሰፋፊ እርሻ ለማስፋፋት የሚያስፈልገውን ካፒታል በበቂ ማቅረብ የማይቻልበት ሁኔታ ነው የነበረው፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ለሰፋፊ እርሻ ልማት ተፈላጊነት ያላቸው ሁኔታዎች በበቂ ደረጃ ሳይሟሉ የቆዩ በመሆኑ ምክንያት ግልጽ አቅጣጫ በተቀመጠበትና አቅጣጫውንም ለመተግበር ቁርጠኝነት ባልተጓደለበት ሁኔታ የሰፋፊ እርሻዎች ልማት ግን ትርጉም ባለው ደረጃ ሳይካሄድ ቆይቷል፡፡ አሁን ይህ ሁኔታ በብዙ መልኩ ተቀይሯል፡፡ መንግስት ባለፉት ዓመታት ባከናወናቸው ሰፋፊ የመሰረተ ልማት ሥራዎች ሰፊ ሊለማ የሚችል መሬት ያለባቸው አካባቢዎች የመሠረተ ልማት አገልግሎቶች ማግኘት ጀምረዋል፡፡ በቀጣይ የዕቅዱ መርሃግብር ዘመንም የበለጠ ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሁኔታ ተመቻችቷል፡፡ በመሆኑም አንዱ ተፈላጊ ሁኔታ መሟላት ጀምሯል፡፡ ብዙ ርቀትም ሄዷል ለማለት ይቻላል፡፡

የጉልበት አቅርቦትን በሚመለከት ምንም እንኳ ሰፋፊ እርሻ በዋነኛነት ሜካናይዜሽን የሚጠቀም ቢሆንም መጠነኛ ጉልበት የሚፈልግ በመሆኑ የእርሻ መሣሪያዎችን ለማንቀሳቀስ የሚያስችል ክህሎት ያላቸው ወጣቶች ልማቱ ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች መልምሎ በማሰልጠን ለማሟላት ታቅዶ እየተሰራ ስለሆነ፣ የጉልበት አቅርቦት ችግርንም ከክልሎች ጋር በመቀናጀት ለማቃለል አቅጣጫ ተቀምጦ ሥራ ስለተጀመረ ለሰፋፊ እርሻ ልማት መስፋፋት ማነቆ የማይሆንበት አጠቃላይ ሁኔታ መፍጠር ተችሏል፡፡ የካፒታል እጥረቱን በሚመለከት የአገር ውስጥ ባለሀብቱና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አቅማቸው በፈቀደ መጠን በእርሻ ኢንቨስትመንት እንዲሳተፉ በመደገፍ አበረታች ጅምር ው-ቖት መታየት የጀመረ በመሆኑ፣ በተለይ ደግሞ አለማዊ ሁኔታው ለግብርና ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ በመፍጠሩና በርካታ የውጭ ባለሀብቶች በግብርና ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት ማሳየት በተግባርም ኢንቨስት ማድረግ ላይ በመሆናቸው ችግሩ መቃለል ጀምሯል፡፡ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ የውጭ ኢንቨስትመንት በግብርና ዘርፍ መሳብ የሚቻልበት ወቅት በመሆኑና ይኸውም ወደፊት ተጠናክሮ የሚቀጥል እንጂ ባጭር ጊዜ ይለወጣል ተብሎ ስለማይገመት ለሰፋፊ እርሻ ልማት ሌላው ተፈላጊ ሁኔታ ከሞላ ጎደል ተሟልቷል ሊባል ይችላል፡፡ አሁን ባለንበት ዘመን ለአቅጣጫው መፈፀም የተመቻቸ ሁኔታ በመኖሩ ይህንኑ በመጠቀምና የግል ባለሀብቱ የግብርና ልማት ተሳትፎ እንዲጎለብት በማድረግ በሂደት አንድ ጠንካራ የግብርና ዕድገት ምንጭ ሆኖ እንዲወጣ ማስቻል ለግብርና ለራሱና ለአጠቃላይ ኢኮኖሚ ዕድገትም የሚበጅ መሆኑ ነው የሰፋፊ እርሻ ልማትን ወቅታዊና ተፈላጊ ያደረገው፡፡

በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዳችን እንደ አንድ የግብርና ልማት አቅጣጫ የተቀመጠውና  በዚህ ወቅትም በትኩረት ገቢራዊ የሚደረገው የሰፋፊ እርሻ ልማት መነሻ ሁኔታውና እውነታው ከላይ የተገለፀው ሆኖ ሳለ ነው እንግዲህ የጽንፈኛ ኒዩ-ሊበራል አፈቀላ-ቖዎች የመሬት ወረራ (ለቷነደ ገረቷበበዥነገ) በኢትዮጰያ እየተፈፀመ ነው በማለት የቁራ ጩኸት የሚጮሁት፣ የአዞ እምባ የሚያነቡት፣ በአለም አቀፍ ደረጃ በተዘረጋ የመሬት ወረራ ወጥመድ ውስጥ እንደወደቅን አድርገው ሊያሳምኑ ላይ ታች የሚሉት፡፡

እነኝህ ኃይሎች የአዞ እንባቸው ተዓማኒነት እንዲኖረው ለማድረግ የሚጠቀሟቸው አጀንዳዎች ሁሉንም ሰው በቀላሉ ይነካሉ፣ ስሜት ይኮረኩራሉ፣ ቢያንስ ከንፈር ያስመጥጣሉ የሚሏቸውን ነው፡፡ የሚያራምዷቸው አቋሞችና የሚሰነዝሯቸው ትችቶች ምን ያህል ፀረ-ልማት እንደሆኑ አጀንዳዎቻቸውን አንድ በአንድ እያነሳን ከእኛ ተጨባጭ ሁኔታና መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር አዛምደን እንመልክት፡-

አዛኝ ቅቤ አንጓች እንዲሉ አንዱና የመጀመሪያው የሚያስተጋቡት ጉዳይ መሬት ለውጭ ባለሀብቶች እየተሸጠ የመሬት ወረራና የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ እየተስፋፋ ነው የሚል እንደሆነ መግቢያችን ላይ ተገልጿል፡፡ ይህን ጩኸት የሚያሰሙ አካላት ትላንት ምን ሲሉን እንደነበረ ጉዳዩን በሚዛኑ ለማየት ያግዛል እናስታውሳችሁ፡፡ መሠረታዊ እምነታቸው የግል ባለቤትነትን እንደጣኦት ማምለክ መሆኑን ልብ እንበል፡፡ በዚህ አቋማቸው ላይ ተመስርተው መሬት ሊሸጥ ሊለወጥ ይገባዋል በማለት ውርጅብኝ ሲያዘንቡብን የነበሩ ናቸው፡፡ መሬት ለልማት ካለው ፋይዳ አንፃር ሳይሆን ከጭፍን ርዕዮተ-ዓለማዊ አቋም የሚነሳ አስተሳሰብ ያላቸው በመሆኑ መሬት የሕዝብና የመንግሰት ሆኖ በጊዜ በተገደበ የሊዝ ስርዓት ልማታዊ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውል የዘረጋነውን ሥርዓት ለሰፋፊ እርሻ ልማት እንቅፋት ነው፣ ዘላቂ የግል ባለሃብት መሳብ አያስችላችሁም፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የግብርና እድገት የታነቀው መሬት መሸጥ መለወጥ ስለማይቻል ነው ሲሉን የነበሩ ኃይሎች ናቸው፡፡ ኢህአዴግ በመቃብሬ ላይ ካልሆነ በቀር መሬት አይሸጥም አይለወጥም ብሏል በሚል የነዚህን ኃይሎች ሃሳብ ሳያላምጡ የሚወጡት የሀገራችን ተቃዋሚዎች ሳይቀር በምርጫ ዘመቻዎች አፍ ሞልተው ሲኮንኑን የነበረው የነዚህን ኃይሎች እምነት በማስተጋባት ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ እነዚህ ኃይሎች መሬት ተሸጠ፣ ተቸበቸበ ብለው ሲያስተጋቡና ከራሳቸው መሠረታዊ ዕምነት ጋር ተመልሰው ሲላተሙ ሲያስተውሉ፣ እነኝህ አካላት የያዛቸው አባዜ ያረፈችበትን ቀለም እንደምትላበሰው እስስት ተለዋዋጭነታቸውን ያስረግጥ ካልሆነ ከመሠረታዊ አቋማቸውና እምነታቸው መለወጣቸውን አያሳይም ማለት ይቻላል፡፡ ተለዋዋጭነቱ ግን ሽፋን እንጂ ይዘቱ ላይ አለመሆኑን ልብ እንበል፡፡መሠረታዊ እምነታቸው የራሳቸው ጥቅም ነው፡፡ ከተጠቀሙ መልካም ነው፡፡ ለዝንተዓለም ገብተው በዝብዘው የያዙት አለም ከነሱ ውጭ የተለየ ቀለም ወይም ገፅታ ያለው ሌላ አካል  መጠቀም ሲጀምር ግን እንደ ተርብ መናደፍ ይጀምራሉ፡፡

ከዚህ የምንገነዘበው ኒዩ-ሊበራሊዝም ለርዕዮተ-ዓለሙ ያላደረን፣ ለርዕዮተ-ዓለሙ መሪና አጋፋሪዎች ጥቅም ቅድሚያ ያልሰጠን ከራሱ መሠረታዊ አቋም ጋር የሚጋጭም ቢሆን ተለዋዋጭ አቋም እየያዘና ታርጋ እየለጠፈ  ባይሳካለትም እንኳ ያፈነገጡ የመሰሉትን ልክ ለማስገባት የሚተጋ መሆኑን ነው፡፡

እስኪ ደግሞ ከመሬት ተወረረ ልፈፋ ጋር የተያያዙ አንዳንድ መረጃዎችን በማንሳት እንመልከት፡፡ እንደሚታወቀው በሀገራችን ሊለማ ይችላል ተብሎ የሚገመተው መሬት ስፋት 73 ሚሊዮን ሄክታር ይጠጋል፡፡ ከዚህ ውስጥ እስካሁን በዋነኛነት በአነስተኛ አርሶ አደሩ በጣም በጥቂቱ ደግሞ በሀገር ውስጥ ባለሀብቱ የለማው መሬት ከ 15 ሚሊዮን ሄክታር አይበልጥም፡፡ ይህ እንግዲህ የሚያሳየን ሊለማ የሚችል ነገር ግን ገና መልማት ያልጀመረ ወደ 58 ሚሊዮን ሄክታር የሚጠጋ መሬት ሀገሪቱ ያላት መሆኑን ነው፡፡ ከዚህ ሊለማ ሲችል ያልለማ መሬት ውስጥ ለጊዜው ወደ 3 ሚሊዮን ሄክታር የሚጠጋ መሬት ለይቶ እንዲለማ ማመቻቸትና ከዚህ ውስጥ ደግሞ ወደ 378ሺ ሄክታር መሬት እንዲለማ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ባለሃብቶች ማስተላለፍ በምን ስሌት ነው የመሬት ወረራ የሚያስብል ድምዳሜ ላይ የሚደረሰው? ለሚለው ጥያቄ የመሬት ተወረረ ወሬ ነጋሪዎች መልስ የላቸውም፡፡ በተለይ ደግሞ 250,000 ሄክታር መሬት በመንግስት አማካኝነት የሸንኮራ አገዳ ልማት የሚካሄድበት የስኳር ኢንዱስትሪውን መስፋፋት የሚመግብ መሆኑን እያወቁ ጭምር ማደናገሩን ሥራዬ ብለው የተያያዙት የዘመናት ፈላጭ ቆራጭነት ህልማቸው ከእጃቸው ሲያመልጥ እየታያቸው በመሆኑ ካልሆነ ምን ሊሆን ይችላል? መቼም ይሉት አያጡምና ኢትዮጵያ የራሷን መሬት ራሷ እየወረረች ነው ብለው ያስገርሙን ይሆናል፡፡

በመሬትና ምርቱ የመጠቀም መብት የተረጋገጠለት አርሶና አርብቶ አደር በመንግስት በሚደረግለት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ታግዞ ምርትና ምርታማነቱን ለማሳደግ፣ ገቢውንና ኑሮውን ለማሻሻል የሚያደርገው ጥረት በምንም መልኩ ሳይደናቀፍ ከአርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ይዞታ ውጭ የሆነ መሬት መንግስት በሚቆጣጠረውና በዘረጋው የአገርን ጥቅም በሚያስጠብቅ ስርዓት አማካኝነት እንዲለማና ተጨማሪ የግብርና ልማት ዕድገት ምንጭ ሆኖ ሀገርንም ህዝብንም እንዲጠቅም መደረጉ ምኑ ላይ ነው ወረራ የሚያስብለው? ለዚህም መልስ የላቸውም፡፡ በተለይ በትንንሹ እና የተበጣጠሰ መሬት ላይ የተመሰረተ አርሶ አደር ይዛችሁ ማደግ አትችሉም፣ ስለዚህ ካልተሸጠና ካልተለወጠ ሰፋፊ እርሻ ሊኖራችሁ አይችልም፣ የውጭ ኢንቨስትመንት መሳብ አትችሉም በሚል ሰበብ እጃችን ለመጠምዘዝ ሲሞክሩ የነበሩ፣ መሬት መሸጥ መለወጥ ሳያስፈልግም አርሶ አደር ማፈናቀል ሳይጠይቀን ሰፋፊ አርሻ አርሶ አደር ባልሰፈረባቸው የሀገራችን አካባቢዎች ማልማት ይቻላል፡፡ በርካታ አርሶ አደር አፈናቅሎ ሰፋፊ እርሻ በውጭ ኢንቨስተር ለማልማት መሞከር የልማት ሳይሆን የጥፋት አቅጣጫ ነው እያልን ስንሞግታቸው የነበሩ ኃይሎች ናቸውና፡፡

የሚተላለፈው መሬት ላይ የሚለሙ የሰብል ዓይነቶች ከሀገራችን ፍላጎት አኳያ ቅደም ተከተል ወጥቶላቸው (ማለትም ጥጥ፣ ሸንኮራ አገዳ ልማት፣ ፓልም ዛፍ፣ የጎማ ዛፍ) በነኝህ ላይ ኢንቨስት ሊያደርግ የሚችል ባለሀብት ላይ በማተኮርና ከውጭ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንትና ቴክኖሎጂ በመሳብ የግብርና ምርት በግብዓትነት ለሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች ጥሬ ዕቃ በበቂ እንዲቀርብና የግብርና ኢንዱስትሪ ሽግግር እንዲሳካ በማድረግ ረገድ  የሰፋፊ እርሻ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት በሚያደርግ አግባብ እየተካሄደ ያለው የማልማት ሥራ በመሬት ሀብታችን ላይ ተመስርቶ የሚካሄድ መዋቅራዊ ለውጥ የሚያመጣ ልማትን እንጂ በጭራሽ የመሬት ወረራን አያመላክትም፡፡

ሌላ አንድ ተጨማሪ መረጃ እናክል፡፡ እስካሁን በፌደራል መንግስት አማካኝነት በሊዝ የተላለፈው 378ጯዐዐዐ ሄክታር መሬት ለ26 የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች የተላለፈ ነው፡፡ ከሀያ ስድስቱ ባለሀብቶች አስሩ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አምስቱ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ የውጭ ባሀብቶች ቁጥር አስራ አንድ ነው፡፡ በድምሩ ተወስዶ ሲታይ መሬት ለማልማት የተላለፉላቸው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቁጥር አስራ አምስት ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህ የሚያረጋግጠው የሰፋፊ እርሻ ልማታችን አቅም ላላቸውና በግብርና መስክ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት ለሚያሳዩ ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች ቅድሚያ የሚሰጥ፣ በኢትዮጵያውያን የካፒታል አቅም ውስኑነት ምክንያት ሊለማ ሲገባው  ሳይለማ የሚቀር የተዘጋጀ መሬት እንዳይኖር፣ ይልቁንም የካፒታል እጥረቱ ሰፊ ስለሆነም ይህንኑ ክፍተት የሚሞላ የውጭ ኢንቨስትመንት ደግሞ በዛው መጠን ወደ ሀገራችን እንዲፈስ ለማድረግ በሚያስችል መልኩ የተቀየሰና እየተተገበረም ያለ በመሆኑ የመሬት ተወረረ አሉባልታ መሠረት ቢስ መሆኑን ነው፡፡

በሚያሳፍር ሁኔታ ከድርቅ ችግር ጋር ለማያያዝ የሚሞከረውና ሌላኛው የመሬት ተወረረ ነጠላ ዜማ ይዘት በሰፋፊ እርሻ ልማት ላይ የሚካሄድ የውጭ ኢንቨስትመንት የአስተናጋጅ አገሮችን የምግብ ዋስትና መረጋገጥ ጥረት እየጎዳ ነው፤ እንዲያውም በኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ከተከሰተው ድርቅ ጋር ተያይዞ በአርብቶ አደሩና በልግ አብቃይ አካባቢዎች የተከሰተውን ድርቅ ከሰፋፊ እርሻ መስፋፋት ጋርም ይያያዛል የሚለው ነው፡፡ ልብ ይበሉ፡፡ በኢትዮጵያ በ2ዐዐ3 የተከሰተው ድርቅ በአርብቶ አደሩ አካባቢ በተለይም በሶማሌ ክልልና በቦረናና ጉጂ አካባቢዎች በአካባቢው በአመት ሁለት ጊዜ ለአጫጭር ጊዜ በመደበኛነት የሚዘንብ ዝናብ በተከታታይ ሳይዘንብ በመቅረቱ እንዲሁም ደግሞ በልግ አብቃይ በሆኑ የኦሮሚያና ደቡብ አካባቢዎች የበልግ ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት የተከሰተ ነው፡፡ መሬት ለውጭ ባለሀብቶች የተላለፈባቸው ቦታዎች የሚገኙት ደግሞ በዋነኛነት በጋምቤላና በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ነው፡፡ በዚህ ላይ ገና መሬት መተላለፍ ጀመረ እንጂ የተላለፈው መሬት በሙሉ በአንድ ዓመት ሊለማ አይችልም፡፡ ሰፋፊ እርሻ ማልማት የካፒታል አቅም፣ የመሳሪያ ሞቢላይዜሽንና ደረጃ በደረጃ አቅዶ ማልማትን የሚጠይቅ ሥራ ነው፡፡ በመሆኑም የልማቱ ስፋትና ልማቱ የሚካሄድበት ቦታ ተወስዶ ሲመዘን የሰፋፊ እርሻ ልማት ጅምር እንቅስቃሴና የድርቁ መንስኤ የቀኝና የግራ ዓይን ማለት ናቸው ምክንያቱም አይተያዩም አይገናኙምና፡፡

የ..መሬት ወረራ፡ ያልተቀናጀ ኦርኬስትራ ጆሮ በጣሽ ቅንብር የሚደመጥበት ሌላው ጉዳይ የምግብ ዋስትና መታጣት ያስከትላል በሚል የሚገለፀው ነው፡፡ ይህንን ጉዳይ ለመረዳት ፖሊሲዎቻችንን፣ ስትራቴጂዎቻችንና ስልቶቻችንን እንዲሁም ከዚህ የሚቀዱትን ዕቅዶቻችንን መለስ ብሎ ማየት ይጠይቃል፡፡ እንደሚታወቀው የግብርና ልማታችን በዋነኛነት የሚመሠረተው በአነስተኛ አርሶ አደር ልማት ላይ ነው፡፡ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዳችንም ላይ በያዝናቸው አምስት ዓመታትም የአነስተኛ አርሶ አደርና አርብቶ አደር ግብርና እንደ እስካሁኑ ሁሉ ዋነኛው የግብርና ዕድገት ምንጭ ሆኖ እንደሚቀጥል በግልጽ ተመላክቷል፡፡ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ጉዳይ በዋነኛነት የሚወሰነውም በዚሁ የግብርና ዕድገት ዋነኛ ምንጭ በሆነው በአነስተኛ አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ግብርና ስኬት ነው፡፡ እርግጥ የሰፋፊ እርሻ ልማት በደጋፊነት የግብርና ልማትን ለማረጋገጥ የሚያግዝ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ የምግብ ዋስትና መታጣት ችግርን ለመቅረፍ እንደ ደጋፊ አቅም ሆኖ የሚያገለግል እንጂ በግልባጩ ለምግብ ዋስትና መታጣት ችግር መንስኤ የሚሆንበት ምክንያት የለም፡፡ ባጠቃላይ የምግብ ዋስትናችንን የማረጋገጥ አጀንዳ የሚወሰነው በመሠረታዊነት በአነስተኛ አርሶ አደሩ ግብርና ው-ቖት ላይ በመሆኑና የሰፋፊ እርሻ መስፋፋት ደግሞ ለዚህ ው-ቖት ደጋፊ እንጂ በምንም አይነት አደናቃፊ ሚና የሌለው ስለሆነ በዚህ ረገድ የሚነሳው ትችትም ውሃ የሚቋጥር ሆኖ አይታይም፡፡ እስከአሁን ባየናቸው ጉዳዮች ላይ ተመስርተን የምንረዳው በኢትዮጵያ የመሬት ወረራ እየተካሄደ ነው የሚለው የዓለም አቀፍና ለእነርሱ ያደሩ፣ ሳያላምጡ የሚውጡና እንደገደል ማሚቱ የሚያስተጋቡ አንዳንድ የሀገር ውስጥ ተቃዋሚዎችና ሚዲያዎች ጩኸት ከተንሻፈፈ አመለካከታቸውና እምነታቸው የሚፈልቅ እንጂ ይህ ነው የሚባል ሊደመጥ የሚችል ይዘት የሌለው መሆኑን ነው፡፡

ነገር ግን ትችቶቻቸውና ስም የማጥፋት ዘመቻቸው በተነሱት ጉዳዮች ላይ ብቻ ተወስነው የሚቀሩ ባለመሆናቸው የያዙትን ዘመቻ በይበልጥ ለመረዳት ቀሪ አንድ ሁለት ትችቶቻቸውን መፈተሽና ባዶነታቸውን ማሳየት ይጠቅማልና ይህንኑ ወደ መመልከት እንለፍ፡፡

ተደጋግሞ እንደተገለፀው ለሰፋፊ እርሻ ልማት የሚውል መሬት ያለን ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ በተዘረጋው ምዕራባዊ ቆላማ የአገራችን ክፍል ነው፡፡ ይህ አካባቢ ደግሞ በውል እንደሚታወቀው በጣም ጥቂት ህዝብ የሰፈረበትና ለእርሻ ሥራ ተስማሚ የሆነ ሰፊ ያልለማ መሬት ያለበት ነው፡፡ ይህን እምቅ አቅም ነው እንግዲህ ወደ ልማት ደረጃ በደረጃ በማምጣት በቀጣይ እያደገ የሚሄድ የግብርና ዕድገት ምንጭ ለማድረግ የሰፋፊ እርሻ ልማት አቅጣጫ የተቀየሰውና የተግባር እንቅስቃሴውም የተጀመረው፡፡ ለአቅጣጫው ተግባራዊነት ሰፋፊ መሬት ሲለይና ሲጠና በቅድሚያ የሚታየው መሬቱ ከአካባቢው ህብረተሰብ ይዞታ ውጭና ነፃ መሬት መሆኑ ነው፡፡ እስካሁን የተለዩ መሬቶች ነፃና ሰፋሪ የሌለባቸው መሆኑ ተረጋግጦ የተለዩና መሬቱ ወደ ልማት ሲገባም የአካባቢው አርሶ አደር ሳይፈናቀል ከሁሉ አስቀድሞም ለአካባቢው ህብረተሰብ በቂ የሚያለማው መሬት እንዲኖረው አሁን  ላለው የቤተሰብ ሃላፊ አባወራ/እማወራ ብቻ ሳይሆን ወደፊት ለማስፋፋት የሚያስፈልገውንም ታሳቢ በማድረግ መሬት የሚለይበት አግባብ ነው እየተተገበረ ያለው፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ በሰፋፊ እርሻ መስፋፋት ምክንያት አርሶ አደሩ እየተፈናቀለ ነው የሚለው በሬ ወለደ ጩኸት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚሉትንም ተቀብለው የሚያስተጋቡትንም ትዝብት ላይ የሚጥል ከመሆን የዘለለ አይደለም፡፡

በመሬት አስተዳደር ህጎቻችን በግልጽ እንደተደነገገው መሬት ለህዝብና የላቀ ጥቅም ለሚያስገኝ ልማት ተፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በይዞታው ላይ ላለው ዜጋ በመሬቱ ላይ ላፈሰሰው ሀብት ካሣ ተከፍሎት መሬቱ ለላቀ ልማትና ለህዝብ ጥቅም እንዲውል ማድረግ ይቻላል፡፡ ለሰፋፊ እርሻ  መሬት ከማዘጋጀት አኳያ ይህን ማድረግ የሚያስገድድ ሁኔታ ስለሌለ (በአካባቢው በቂና ሰው ያልሰፈረበት መሬት ያለ በመሆኑ) አልተፈፀመም እንጂ ቢፈፀምም እንኳ ከህግ-ውጭና ያለአግባብ የተፈፀመ ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም፡፡

የመጨረሻው የትችት ናዳ የሚወርድበት አጀንዳ የሰፋፊ እርሻ መስፋፋት በተፈጥሮ ሀብት ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው፣ ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታም መሬት ለውጭ ባለሀብት እየተሰጠ ነው የሚለው ነው፡፡ ለዘላቂ የግብርና ልማት የተፈጥሮ ሀብት ልማት ቀዳሚና ተፈላጊ መሆኑን በስትራቴጂዎች፣ ስልቶችና ዕቅዶች በግልጽ በማስቀመጥ ይህንኑ ወደ ተግባር ለመቀየር በሚሊዮኖች የሚቆጠር አርሶ አደር በተደራጀና በተቀናጀ መንገድ አንቀሳቅሶ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ሥራ  ው-..ት በሚያመጣ አግባብ የሚሰራ፣ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ችግኝ አዘጋጅቶ በመትከል የደን ሽፋን ለማሳደግ ጥረት በማድረግ ላይ ያለ፣ በየአመቱ በብዙ መቶ ሺዎች ሄክታር መሬት ከሰው እና እንስሳት ንክኪ ነፃ ሆነው እንዲጠበቁና መልሰው እንዲያገግሙ በማድረግ ላይ የሚገኝ፣ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አነስተኛ የውሃ ማስረጊያና ማሰባሰቢያ ስትራክቸሮች በመስራት ስነ-ምህዳሩን ለመጠበቅ ተግቶ የሚሰራ ሀገርና መንግስት እንዴት ሆኖ ነው ኃላፊነት በጎደለው መንገድ የተፈጥሮ ሀብት መመናመን እያስከተለ ነው ተብሎ ሊወቀስ የሚችለው? በለፀግን የሚሉ ሀገራት እንኳ ቁርጠኝነት ያጡበትን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ራዕይ አንግቦ ለተግባራዊነቱ ዝግጅትና ተጨባጭ እንቅስቃሴ በማድረግ ዋንኛው የልማታችን የሃይል ምንጭ ከታዳሽ የሀይል ምንጮች  (ከውሃ፣ ከነፋስ፣ ከባዮ-ፊውል) እንዲሆን የልማት አቅሞችን የሚያረባርብና ው-ቖት በማምጣት ላይ ያለ፣ ከወዲሁ ራዕዩን ማሳካት የሚችል መሆኑን የሚያመለክቱ ው-ቖቶችም እያስመዘገበ ያለ ሀገርና መንግስት በአካባቢ ጥበቃ ሥራ ሊወደስ ካልሆነ ሊወቀስ አይችልም፡፡

ለሰፋፊ እርሻ መሬት ሲለይ በመጀመሪያ ከሚታዩ ጉዳዮች አንዱ መሬቱ ከፓርኮችና ጥብቅ ደኖች ነፃ መሆኑ ነው፡፡ እስካሁን የተለየው መሬትም በተቻለ መጠን የሳቫናሳርና ቁጥቋጦ ያለበት ቦታ እንዲሆን ነው የተደረገው፣ ወደፊትም የሚደረገው ይኸው ነው፡፡ የሚለሙ የሰብል ዓይነቶች ቅደም ተከተል ሲቀመጥ የተለዩት የቋሚ ተክሎች የጎማ ዛፍ፣ የፖልም ዛፍና የመሳሰሉት እዛው ሳሉ ለአካባቢ ስነ-ምህዳር አዎንታዊ አስተዋጽኦ ያላቸውም ናቸው፡፡ በመሬት መለየት፣ በሚለሙ ሰብሎች ቅደም ተከተል ማስቀመጥ ረገድ የሚደረገው ጥንቃቄ እንደተጠበቀ ሆኖ መሬቱ ለልማት ሲተላለፍ የመሬት ሊዝ ውሉ ላይ ለአፈር ለምነት እንክብካቤና ለዛፍ ጥበቃ ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች የሚገልፁ አንቀጾች እንዲካተቱም ተደርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለእያንዳንዱ እርሻ የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ሰነድ ተዘጋጅቶ ይገመገማል፡፡  በፀደቀው ሰነድ አማካኝነትም በሚመለከተው የአካባቢ ጥበቃ አካል ወይም እርሱ በወከለው ተቋም አማካኝነት እንዲካሄድ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ይህ ሁሉ ጥንቃቄ የሚደረገው ራሱ ልማቱም ዘላቂነት እንዲኖረው ለማድረግ፣ በአካባቢ ሙቀት ለውጥ ምክንያት የሚከተል ተጽዕኖን ለመቀነስና ለመቋቋም ታስቦ ነው፡፡

ይህ ሁሉ ዙሪያ መለስ ጥረት በሚደረግበት በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር የዓለም ሙቀት መጨመር የሚያስከትለውን ተጽእኖ ለመቋቋም፣ ምንም እንኳ ከአሁን በፊትም ለሙቀቱ መጨመር ያለን አስተዋጽኦ ወደ ምንም የተጠጋ ቢሆንም ቅሉ ወደፊትም የካርቦን ልቀት በድምሩ ዜሮ እንዲሆን ሀገራችን ራዕይ ሰንቃ ለዚሁ ስኬት እየሰራች ባለችበት፣ ው-ቖትም እየተመዘገበ በመጣበትና ይህም በገሀድ የሚታይ እውነታ በሆነበት ሁኔታ የሰፋፊ እርሻ ልማትን ኃላፊነት በጎደለው መልኩ በአካባቢ ላይ ጉዳት እንዲያደርስ በሚያደርግ አግባብ እየተፈፀም ነው የሚለው የስም ማጥፋት ዘመቻ ኢትዮጵያን አይመለከታትምና ከላይዋ ላይ ወረድ በሉ እንላለን፡፡

ጠቅለል ተደርጎ ሲታይ ለግብርና ልማታችንና ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ለሚደረገዉ ሽግግር በሂደት አስተዋጽኦው እየጎለበተ የሚሄደውን የሰፋፊ እርሻ ልማት ማስፋፋት ሥራ ለልማታችን በሚበጅ መልኩ ተልመንና አቅደን እየመራነውና እየተገበርነው ያለ በመሆኑ ይህን እምቅ አቅማችንን እንዴትና መቼ እንደምን እንደምን-ቀምበት ከማንም የውጭ ሀይል መመሪያ አያስፈልገንም፡፡ ማናቸውም የውጭ ሀይሎችና የሀገር ውስጥ ተላላኪዎቻቸዉ ልናለማው የሚገባንንና ከድህነት መላቀቂያ አቅማችንን እንዳናለማ ሊያደርጉ አይቻላቸውም፡፡ የመሬት ሀብታችንን፣ ለማልማት ከማንም ፈቃድ አያስፈለገንምና፡፡ የመሬት ሀብታችንን የማልማት ጉዳይ በዋነኛነት የሚመሠረተው በፖሊሲዎቻችን ስትራቴጂዎቻችንና ስልቶቻችን እንዲሁም መሬታችንን ለማስተዳደር ባወጣናቸው ህጎች ላይ ነው፡፡ በነዚህ ህጎች ላይ ተመስርተን የሀገራችን ጥቅም በሚያስጠብቅ፣ ልማታችንን በሚያፋጥንና ልናመጣ ያቀድነውን መዋቅራዊ ለውጥ በሚያሳካ መልኩ በተመቻቸው ዕድል ተጠቅሞ ኢንቨስት ለማድረግ ለሚፈልግ ሁሉ ምቹ ሁኔታ ፈጥረን አብረን እንሰራለን፡፡ ፍላጎታችን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በመሳብ ያለብንን የካፒታል እጥረት በማቃለል ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ብሎም መዋቅራዊ ለውጥ የሚያመጣ ልማት ማረጋገጥ ነው፡፡ ኢንቨስተሩ ከምስራቅ ሆነ ከምዕራብ ነጭ ሆነ ጥቁር መመዘኛችን ባስቀመጥነው ስርዓት መሠረት የሚሰራ መሆኑ ነው፡፡ በዚህ መሠረታዊ መርህ ላይ በመመስረት በሚካሄድ እንቅስቃሴ የሚያኮርፍ ካለ በራሱ ርዕዮተ-ዓለማዊ አመለካከትና በፍትሀዊ ተጠቃሚነት ከልብ ያለማመን ምክንያት የሚመጣ ፀረ-ልማት አቋም እንጂ ሀገራችን ሰፋፊ የእርሻ ልማት ለማካሄድ የነደፈችው አቅጣጫ ው-ቖት አይደለምና የመሬት ተወረረ ለፋፊዎቹና የገደል ማሚቴዎቻቸው የእንቶፈንቶ ጩኸታቸውን ይጮሀሉ ፍትሓዊ የህዝብ ተጠቃሚነትን ያነገበው ልማታዊ ግመል ግን ጉዞውን ቀጥሏል ብለን በጀመርነው ትግል እንቀጥል፡፡