ህገ መንግሥታዊ እሴቶች ለኢትዮጵያ ሥነ ጽሁፍና መገናኛ ብዙኃን

 

ዮናስ ገረመው

ስድስተኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ህገ መንግሥታችን ለብዝሃነታችን ለአንድነታችንና ለህዳሴያችን በሚል መሪ ቃል በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መቀሌ ከተማ ተከብሯል፡፡

ህገ መንግሥቱን የመተርጐም ሥልጣን የተሰጠውና የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መገለጫ የሆነው የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ልክ እንደቀደመው ሁሉ የበዓሉ መዳረሻ አካባቢ ወይም በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚከናወነው ክብረ በዓል ቀደም ብሎ ዕለቱን በተለያዩ አካባቢዎች በተለያዩ ዝግጅቶች እንዲከበር ያስተባብራል፤ ተሳትፎም ያደርጋል፡፡

ዘንድሮም በዓሉን ማክበር የጀመረው ህዳር 15 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም በብሔራዊ ትያትር ነው፡፡ ምክር ቤቱ ህዳር 15 እና 16 ለሁለት ቀናት የሚቆይ ኮንፈረንስ ያዘጋጀው ህገ መንግሥታዊ መርሆዎችን እና እሴቶችን ፋይዳውንና ተግዳሮቱን ሌሎችም መሰል ህገ መንግሥታዊ ድሎችንና አጋጣሚዎችን የተመለከተ ውይይት ከመገናኛ ብዙኃን፣ ከኪነ ጥበብና ሥነ ጥበብ ባለሙያዎች ጋር በማድረግ ነው፡፡

በዚሁ መሠረት በርካታ የመገናኛ ብዙኃን፣ የሥነ ጥበብና ኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በዕለቱ ታድመው ነበር፡፡ ህገ መንግስቱ ከየሙያውና ባለሙያው አንጻር ያለውን ፋይዳ፣ የአጠቃቀምና የመጠቀም እንዲሁም በዘርፉ ተዋናዮች ዘንድ ያለውን ግንዛቤ በተመለከተ የጥናት ወረቀቶች ቀርበው ውይይት ተደርጐባቸዋል፡፡

የዛሬው መጣጥፌ የትኩረት አቅጣጫም በተለይ ህገ መንግስታችን ለኢትዮጵያ ሥነ ፅሁፍና መገናኛ ብዙኃን የሰጠውን ዋስትናና የዘርፉ ሙያተኞች አጠቃቀምና ህገ መንግሥታዊ ግንዛቤን የተመለከተ  ነው።

በደራሲ ዳንኤል  ወርቁ  የቀረበው ጥናት የኢትዮጵያ ሥነ ጽሁፍን ወቅታዊ ሁኔታ ከኢፌዴሪ ህገ መንግሥት አኳያ  ይቃኛል፡፡

የጥናት ወረቀቱ ከኢትዮጵያ ሥነ ጽሁፍ አጀማመርና ከኢትዮጵያ ሥነ ጽሁፍ ታሪክ በመነሳት በዘመኑ የነበሩትን ነገሥታትና ሥርዓተ መንግስት ከኢትዮጵያ ሥነ ጽሁፍ እድገትና ሥነ ጽሁፍን ከማህበራዊ ዕድገት አንፃር የቃኘ ነው፡፡

በተለይም በደርግ ሥርዓት የነበረውን የሳንሱር ሕግና ተዛማጅ ጉዳዮች በስፋት ዳሷል። በነገሥታቱም ዘመን ሆነ በደርጉ ሥርዓት ጥበብን የሚያበረረታ ሥርዓት እንዳልነበረና ይልቁንም ጥበብ ለገዥዎች ውዳሴና ጥበብ ለአብዮት እንደነበር በሰፊው ያትታል፡፡

አጀንዳዬ ህገ መንግሥታችን ለሥነ ጽሑፋችን እና መገናኛ ብዙኃን ያለውን ፋይዳ የተመለከተ በመሆኑ የጥናት አቅራቢውን ያለፉ ዘመናት ዳሰሳ እዚህ ጋር ማንሳት ተገቢ ስለማይሆን ወደ ዘመናችንና አሁን ወዳለንበት ወቅት በመመለስ የኢትዮጵያን ሥነ ጽሁፍ ወቅታዊ ሁኔታ ወደተመለከተው ጉዳይ አመራለሁ፡፡

ከደርግ መውደቅ ማግስት ጀምሮ ሳንሱር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያ ደራሲያን ጫንቃ ላይ ስለመነሣቱ የሚከራከር ያለ አይመስለኝም፡፡ የሳንሱር መነሳትም ብቻ አይደለም ህገ መንግሥታችን ለሚጽፉትም ሆነ ለሚናገሩቱ በአንቀጽ 29፣ አንቀጽ 41 እና 51 እንዲሁም 91 ዋስትና ሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህም የተነሣ ይመስላል የመፃፍና የመናገር ነፃነትን በተመለከተ  ህገ መንግሥታችን ከብዙ የአፍሪካም ሆነ ሌላው ዓለም   የተሻለ እንደሆነ ብዙዎቹ የፖለቲካና የህግ ምሁራን የሚናገሩት፡፡

ጥናት አቅራቢውም ቢሆኑ ለዚህ ጥናት ሲሉ ጉዳዩን በተመለከተ ያደረጉት ዳሠሣ የኢትዮጵያ ህገ መንግሥት ከአብዛኞቹ አገሮች ህገ መንግሥታት የተሻለ እንደሆነ የሚጠቁም እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ግን ይላሉ ጥናት አቅራቢው በመሠረቱ የህጎች ሁሉ የበላይ የሆነው ህገ መንግሥታችን ሁሉም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች አምነውና ፈቅደው ሲያፀድቁ ለህሊናቸውና መንፈሣቸው እርካታ ብቻ ብለው ሳይሆን ለአንዳች ልማታዊ ፋይዳና ሥጋዊ ለውጥ ነው፡፡

በዚሁ መሠረት ሥነ ጽሁፍም ጥበብ ለጥበብነቷ ከሚል ዘወርዋራ መንገድ ወጥታ ጥበብ ለዓላማ፣ ጥበብ ለልማትና ለውጥ ወደሚለው ትክክለኛ መርሆና ቀጥተኛ መንገድ መግባት ይገባታልና የኢትዮጵያ ሥነ ጽሁፍ ያለፉት 2ዐ ዓመታት ጉዞም መቃኘት ያለበት ከዚሁ አንፃር ነው የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል፡፡

ይህንንም ሲሉ ህገ መንግሥታችን ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓታችን ግንባታ፤ ህገ መንግሥታችን ለልማትና ሌሎችም ጉዳዮች ያለውን አትኩሮትና ያለበትን ተጨባጭ ሁኔታ መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ለዚህ ድምዳሜያቸው ሌላም ማሣያ አቅርበዋል፡፡ የጀርመንን ከድህነት ወደ ሃብት የተደረገ ጉዞና ለስኬቱም የሥነ ጽሁፍን ኃይልና የደራሲያኑን ብሔራዊ ስሜት የተመለከተ ነው  እንደማሣያነት የቀረበው፡፡

የጀርመን ሥነ ጽሁፍን ኃያልነትና ለጀርመናውያኑ ያበረከተውን አስተዋጽኦ የተመለከተው ጉዳይ ለእኛም አገር ደራሲያን ጥሩ ተሞክሮ ስለሚሆን እዚህ ጋር ከብዙ በጥቂቱ ጠቅሶ ማለፍ  ጠቃሚ ነው፡፡

ሃይንሪሽ ቦል  ይባላል ደራሲው፡፡ ይህ ደራሲ በወቅቱ የነበረውን የጀርመን የኢኮኖሚ ሁኔታ “የዛን ጊዜ ዳቦ” በሚለው ረጅም ልቦለድ ጀርመን በወቅቱ ደርሶባት የነበረውን የድህነት ጥልቀትና በዚያም ሳቢያ የተከተለውን የሞራል ዝቅጠት አሳይቷል፡፡ ነገር ግን የጀርመንን የድህነት ጥልቀት እንዲያሳይ የተሳለው ገፀ ባህሪ በነበረው ሁኔታ ተሸንፎ

አልቀረም፡፡ ይልቁንም ኑሮውን ለማሸነፍ የሚያደርገውን ተጋድሎ ሃይንሪሽ ቦል በ“የዛን ጊዜ ዳቦ” ማሳየቱን ተከታዩን ምልልስ (dialoge) ከመጽሃፉ በመውሰድ ለታዳሚያኑ አቅርበዋል፡፡

ገጸ ባህሪው ወይም ባለታሪኩ ሚስቱ በሣንባ ነቀርሣ ሆስፒታል ውስጥ ሞታ አስከሬንዋን እንዲረከብ ተጠርቶ የመጣ ነው፡፡ ይህ ሰው እንደመጣ ያደረገው ሚስቱ ተኝታበት የነበረውን አልጋ መፈተሽ ነው፡፡ ሃይንሪሽ እንዲህ አስቀምጦታል፡፡ እንደገባ “ያመጣሁት የታሸገ ሥጋ የት አለ?” ሲል አምባረቀበት፡፡ “ትናንት ማታ ነበር ያመጣሁላት በአራት ሰዓት፣ እና የሞተችው ማታ ከሆነ ሥጋውን ልትበላ ጊዜ አልነበራትም ማለት ነው፡፡ ሥጋውን እፈልገዋለሁ፣ ካላገኘሁት ግን ይህን ቦታ ግልብጥብጡን ነው የማወጣው፡፡” ተረኛዋ ነርስ ፊትዋ በድንጋጤ ቲማቲም መሰለ፣ እሷም መልሳ መጮህ ጀመረች፣ ከሁኔታዋ እንደተረዳሁት ሥጋውን ሳትሰርቀው አትቀርም፡፡ “ይህ እንግዲህ እንደ

ጥናት አቅራቢው ማብራሪያ የወቅቱን የጀርመን የድህነት ጥልቀትና የሞራል ዝቅጠት ለማሳየት ደራሲው የተጠቀመበት ሥልት ነው፡፡

የገጸ ባህሪውን የአልሸነፍ ባይነትና ኑሮውን ለማሸነፍ ያደረገውን ተጋድሎ በተመለከተ ጥናት አቅራቢው ከ“የዚያን ጊዜ ዳቦ” በመውሰድ ተከታዩን ምልልስ አቅርቧል፡፡

“በቀን 12 ሰዓት እሠራለሁ፣ ይህ እሁድንም ጨምሮ ነው … እጅግ ከመድከሜ የተነሣ እሁድ ቤተክርስቲያን ገብቼ ወንበሬ ላይ ዘፍ እንዳልኩ እንቅልፍ ይዞኝ እልም ይላል፤ የምነቃው ዲያቆኑ ለቁርባን ደወሉን ሲደውል ነው፡፡”

በአጠቃላይ በዚያ አስከፊ ጊዜ የጀርመን ፀሃፊዎች እጅግ ወሣኝ ኃላፊነት ነበረባቸው፡፡ ህዝባቸውን አዲስ መንገድ የማመላከት፣ ድህነትን የሚያሸንፍበትን መንገድ የመምራት፣ እና ያሉበትን ሁኔታ የማሣየት ኃላፊነት፡፡ ይህንንም ኃላፊነት በብቃት ተወጥተዋል።

በሥነ ጽሁፋቸው ለህዝባቸው አዲስ መንገድ አመላክተዋል፣ ሥነ ጽሁፋቸው ህዝባቸው ከድህነት ጋር ለነበረው ዘመቻ የመሪነት ሚናን በመውሰድ ተዋግቶ አዋግቷል፡፡ የድሉን ዋዜማና ድሉንም ያበሰረው ይኸው ሥነ ጽሁፋቸው ነው፡፡ የተገኘው ውጤትና ስኬት እንዲጠበቅና ወደ ኋላ እንዳይመለስ ይልቁንም ሁሌም የወደፊት ልዕልና እንዲኖረው የጀርመን ደራሲያንና ሥነ ጽሁፋቸው ዛሬም የራሱን አሻራ ጥሎ እያለፈ የቅብብሎሹን ጉዞ እንደቀጠለ ነው፡፡

እዚህ ጋር ነው እንግዲህ የሳንሱር ዘመን እንደምክንያት እንዳይሆን ላይመለስ ከተቀለበሰ በኋላና ይልቁንም ለሥነ ጽሁፋችንና ፀሃፍቱ በአንቀጽ 29፣41፣51 እና 91 ህገ መንግሥታዊ ዋስትና ከተሰጠ በኋላ ያለነው የቱ ጋር ነው? የሚለው ጥያቄ የሚመጣው፡-

ውይይቱም ሆነ የጥናት ወረቀቱ ማራኪና ቀልብን የገዛ ነው፡፡ እኔም መጻፌን እቀጥላለሁ፤ እዚህች ጋር አንድ ነገር ታወሰኝ ”የብሄሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች  ቀን በዓል ፋይዳዎች” በሚል ርዕስ ከሰሞኑ አንድ ጽሁፍ ለንባብ አብቅቼ ነበር፡፡

በዚህ ጽሁፌ ላይ የብሄሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አንዳንዶች እንደሚሉት ከድግስና ጭፍራም የዘለለ ብሔራዊ ፋይዳ እንዳለው የተለዩ አብነቶችን እና መገለጫዎችን በማስላት ፋይዳውን ለማሣየት የሞከርኩበት መጣጥፍ ነበር፡፡

ከዚህ ቀደም የነበሩትን የአምስት ዓመታት የብሄሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አከባበር ከነመሪ ቃሎቹና ፋይዳው ሳነሣ በዓሉ በየዓመቱ የራሱን እድገት እያሳየና ጠቃሚ ነገሮችን በማካተት እየተከበረ ስለመምጣቱና ውጤቱንም ለማሳየት ሞክሬያለሁ፡፡

በስድስተኛው የብሄሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ደግሞ ከአምስቱም ዓመታት የተለዩ አዳዲስ ነገሮችን ጨምሮ ስለመምጣቱና የበዓሉ ፋይዳ ከፍ እያለ መሄዱን እዚህ ጋር ለማስታወስ ያስገደደኝና ወደ ኋላ የመለሰኝ የብሄሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልና ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ስለ ሥነ ጽሁፍና መሰል የጥበብ ውጤቶች በሰጠው ዋስትና ልክ ያገኘውን ምላሽ በተመለከተ የሚፈትሽ መድረክ የበዓሉ አካል በማድረግ ማዘጋጀት ተገቢና ወቅቱን የጠበቀ አጀንዳ መሆኑ  ነው። ንግባእኬ ሀበ ጥንተ ነገር (ወደ ቀደመው ነገራችን እንመለስ) ሥነ ጽሁፋችንና ፀሃፍቱ ከተሰጣቸው ህገ መንግሥታዊ ዋስትናና የህግ ማዕቀፍ አንፃር የቱ ጋር ናቸው? ስል የጀርመናውያኑን ደራሲያንና ሥነ ጽሁፍ ማጣቀሻ ወዳደረኩበት አጀንዳ ልመለስ፡-

ጀርመኖቹ በሥነ ጽሁፋቸው ለህዝባቸው አዳዲስ መንገዶችን ጠቁመዋል፤ ድህነትን ማሸነፍ እንደሚቻል በጥበብ ሥራቸው  አሳይተዋል፡፡ የህዝባቸውን ስሜት በሚስሉት ገፀ ባህርያት ገዝተዋል፡፡ እናም ጀርመንና ራሳቸውን ለውጠዋል፡፡ እነሱና ቀጣዩ ትውልድም የሥነ ጽሁፋቸው ውጤት ተጠቃሚ በመሆኑ እሴቶቹን ጠብቆ እየተጓዘ ነው፡፡  አሁንም ጥያቄው እኛስ? የሚል ነው፡፡

ሥነ ጽሁፍ ሌላውንም የጥበብ ዘርፍ ጨምሮ ለአንድ ኅብረተሰብ ግንባር ቀደም የድህነት ማስወገጃ መንገድ ጠቋሚ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የፈጠራ ሥራ ዛሬን ብቻ ሳይሆን መጪውንም ጊዜ አመላካች በመሆኑ አንባቢ በጥቅሉ ኅብረተሰቡ ራሱን ከገጸ ባህሪያቱ ጋር እንዲያመሳስል፣ ራሱን እንዲፈልግ እና ምኞቱንም ለማሳካት እንዲነሳሳ አቅጣጫ ያሳያል፡፡

በጥናቱ ወረቀት ላይ እንደተገለጸው “ሥነ ጽሁፍም ሆነ ማንኛውም የጥበብ ሥራ ዋና ቅመሙ ውበትና ረቂቅነት ነው፡፡ ዘወትር የምናየውን፣ የምንሰማውን፣ የምናውቀውን የሚመስለንን ነገር በልዩ ቋንቋ ከሸኖ አዋዝቶ ማቅረብ ነው፡፡ አንድን በጥሩ ሁኔታ የተፃፈ መጽሀፍ ስናነብ ራሳችንን እስከመጠራጠር የምንዳርሰው እና ለመለወጥ የምንነሳሳው ለዚህ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት መጻህፍት ስናነብ የወደፊት ህልማችንን እና ምኞታችንን ለማሳካት እንነሳለን፡፡ ራሳችን ውስጥ ያልነበረውን ራሳችንን እናገኛለን፡፡”

ሆኖም ሳንሱር ምክንያት ሆኖ የቆየበት የሥነ ጽሁፋችን የጨለማ ዘመን በብርሃን ቢተካምና ህገ መንግሥታዊ ዋስትና ቢሰጠው ሥነ ጽሁፋችን ዛሬም ድረስ ቀደም ተብሎ እንደተገለጸው የጀርመን ደራሲያን ሥራዎች ዓይነት ወገብን አስታጥቀው ወደተግባር የሚመወስዱ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡

አብዛኛቹ የጥበብ ሥራዎች ተመሳሳይ የሃዘን እንጉርጉሮዎች፣ ችግርን ማለፍ እንዴት እንደሚቻል የሚያሳይ ሳይሆን፤ ኅብረተሰቡን ለአሸናፊነት የሚያነሳሱ ሳይሆን አብረውት የሚያለቅሱና አብረውት የሚቆዝሙ በመሆናቸው የፈየዱት ፋይዳ እምብዛም ነው ብሎ ለመናገር ያስደፍራል፡፡

የሌሎቹ አገሮችን ተሞክሮ ስናይ አሜሪካንን ጨምሮ ምዕራባውያንም ሆኑ ምሥራቃውያን መንግሥታት የሥነ ጽሁፍን አስፈላጊነት በመረዳት በየትኛውም ዘመን እና ወቅት ትልቅ ቦታ ሰጥተውት እናገኛለን፡፡ ህዝባቸው ውስጥ ሥር እንዲሰዱ የሚፈልጓቸውን ነገሮች በሙሉ በተለይም የህገ መንግሥታቸውን እሴቶች ከህፃናት መጻሕፍት ጀምሮ በተለያየ ደረጃ እንዲደርሱ ለማድረግ የተጠቀሙት ሥነ ጽሁፍን እንደሆነ የተለያዩ የጥናት ውጤቶች ያሳያሉ፡፡

በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ጥናት ያቀረቡት ደራሲ ዳንኤል ወርቁም በጥናት ወረቀታቸው ላይ እንዳመለከቱት የአገራችን ደራሲያንና አርቲስቶች ህገ መንግሥቱን ማወቅ የውዴታ ግዴታ መሆኑን በቅጡ ያልተገነዘቡ በመሆናቸው ህዝቡም እንደሌላው የህይወት ገጠመኙ ስለ ህግ ወይም ህገ መንግሥቱ ማወቅ የሚመኘው ሲከስ ወይም ሲከሰስ ብቻ  ነው፡፡

ይህ ደግሞ ዛሬም ድረስ በፅሁፎቻቸው ውስጥ በሚንፀባረቁት የተለመዱና በዘልማድ ያገኟቸው ሃሳቦች ይንፀባረቃል፡፡ ለምሳሌ እንኳ ብንወስድ በአንቀጽ 35 የተገለጸውን የሴቶች መብትና በአንቀጽ 39 የተረጋገጠውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መብት በመዘንጋት ሴት ገፀ ባህርያት በመጻፍት

ውስጥ የሚወከሉበት መንገድ ከቀድሞውና ህገ መንግሥት በሌለበት ዘመን እንደነበሩት የአባቶቻችን ጽሁፎች በቀጥታ የተቀዱ እስኪመስለን ድረስ ተመሳሳይነት ያላቸው ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡

ብዝሃነትን ከማንፀባረቅ አንፃር የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ወደተቃኙበትና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ቤት መምህር በሆኑት ተሻገር ሽፈራው ወደቀረበው ጥናታዊ ወረቀት ደግሞ እንሂድ፡፡

የዴሞክራሲ ግንባታ በምጣኔ ሀብት፣ በፖለቲካና በባህል መስክ ከዝቅተኛ የማኅበረሰብ ደረጃ እስከ ከፍተኛው ድረስ የህዝብ ተሳትፎን እንደሚጠይቅ፣ ህዝብም ከምክንያታዊ ውሳኔና ምርጫ ላይ መድረስ የሚችለው ሰፊና ዓይነተ ብዙ መረጃ ሲኖረው እንደሆነ፣ የመረጃ አማራጮችን በሥፋት የማቅረብና ነፃ አስተሳሰብ እንዲጐለብት ማድረግም ህገ መንግስታዊ እሴቶችን የማበልፀግ አንድ አካል ተደርጐ ሊወሰድ እንደሚችልና ዜጐች ለዴሞክራሲያዊ ባህል መዳበር ድርሻ ሊያበረክቱ የሚችሉት ስለ ህገ መንግሥቱ ያላቸው ግንዛቤ ሲዳብር፣ የዜግነት መብትና ግዴታቸውን ሲያውቁ በመሆኑ የመገናኛ ብዙኃን የማስተማሪያና የመወያያ መድረክ የመፍጠር ድርሻ በምንም ሊተካ እንደማይችል በማስመርና አጽንኦት በመስጠት የሚጀምረው የጥናት አቅራቢው ማብራሪያ ሲቀጥል፦ ትኩረት ያሻቸዋል ያሏቸውን ሶስት መሠረታዊ ነጥቦች ያስቀምጣሉ፡፡

ብዝሃነታችንን ከመገናኛ ብዙኃን አንፃር ለመቃኘት የመጀመሪያውና መታየት የሚገባው መሠረታዊ ነጥብ ሃሣብን በነፃነት የመግለጽ ባህል በሌለበት መገለልና ጭቆና ሰፍኖ በቆየበት፣ ድህነትና ኋላ ቀርነት የማኅበረሰቡ መገለጫ በሆነበት ሁኔታ ውስጥ ለኖረ ህዝብ የሚሰሩ መገናኛ ብዙኃን ተልዕኳቸው የሚለካው አወንታዊ ለውጥ ከማምጣት አንፃር  ነው፡፡

ለተኛው ደግሞ በተለይ አገር አቀፍ ርጭትና የዜና ሽፋን እንዳላቸው የሚያምኑ መገናኛ ብዙኃን የብዙ ብሔሮች፣ ብሄረሰቦችና ባህሎችን እውነታ ከማንፀበረቅ አንፃር ራሳቸውን መፈተሽ እንደሚገባቸውና ብዝሃነት በኢትዮጵያ ህገ መንግት ውስጥ

አንቀጽ ተሻጋሪ ጭብጥ በመሆኑ የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎችም ይህንን ጭብጥ ከማበልፀግ አንፃር የሚኖራቸው ድርሻ የህገ መንግቱን እሴቶች የማጎልበት ድርሻ ማዕከላዊ አካል መሆኑን መገንዘብ

አስፈላጊ እንደሆነ የሚያመለክት ነጥብ ነው። ይህ ጉዳይ በሌላ መልኩ ሲታይ ለልዩ ልዩ አስተሳሰቦች፣ ፖለቲካዊ ዝንባሌዎች፣ ባህሎች፣ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ ፍላጎቶችና ልዩ  የኅብረተሰብ ገጽታዎች ሚዛናዊና ፍትሃዊ ሽፋን መስጠትን ከሚመለከተው የጋዜጠኝነት ሙያዊ መርህ ጋር የተያያዘም እንደሆነ መገናኛ ብዙኃን ሊያጤኑት የሚገባው ነጥብ ነው።

ከጥናቱ ጋር የተያያዘውና ሶስተኛው መሰረታዊ ነጥብ:- ኢትዮጵያ የብዙ ብሄሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች አገር እንደመሆኗ ልዩ ልዩ ቋንቋዎቸ የሚነገሩባት የበርካታ ባህሎች ወጎች፣ ልማዶች እምነቶችና አስተሳሰቦች ባለቤት እንደመሆኗ መጠን ብዝሃነት ፖለቲካዊ እውነትን የሚያንፀባርቅ ጽንሰ ሃሳብ እንደሆነ በመረዳት በኢትዮጵያ የሚገኙ መገናኛ ብዙኃንም ይህን ፖለቲካዊ እውነታ በማንፀባረቅ በኩል የሚገኙትበትን ደረጃ መመዘን እንደዋነኛ የመገናኛ ብዙኃን ጥናት ዘርፍ ሊታይ የሚችል መሆኑን የሚገልፀው ፅንሰ ሃሳብ ነው።

አገር ሁሉም ዜጎች በጋራ መግባባት የሚፈጥሯት የፖለቲካ ማኅበረሰብ መሆኗን በማወቅ በአገራችን ህዝቦች ውስጥ የሚታየውን ብዝሃነት እንደ እሴት የሚመለከት ህገ መንግት ባለቤት መሆናችን አንድ ነገር ሲሆን የህገ መንግታችን የተለየ ባህሪና መሰረታዊው ስሜት ደግሞ የግለሰቦችና የህዝቦች መሰረታዊ ነፃነቶችና መብቶች መከበር፣ ያለምንም ጾታዊ ኃይማኖታዊና ባህላዊ አድልዎ በእኩልነት ለመኖር የሚያስችል መሆኑን ነው።

ልዩነትን መቀበልና ማክበር፣ የጋራ መግባባትና ስምምነት በጋራ ለመኖር መነሻ መሆኑን ማመን ህገ መንግታችን የሰለጠነ ማኅበረሰብ ለማፍራት የሚያስችል መርሆዎችን ማካተቱን የሚጠቁምና ብዝሃነትም ከእነዚህ አንኳር ህገ መንግታዊ እሴቶች አንዱ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።

ከእነዚህ መሰረታዊ የብዝሃነት ጭብጦች አንፃር በመገናኛ ብዙኃን የብዝሃነት ጥናት ውስጥ ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች መኖራቸውን ጥናት አቅራቢው እንዲህ ይገልጻሉ፡፡

|ጋዜጦች፣ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ምን ያህል ብዝሃነት ይታይባቸዋል? ምን ያህል ብዝሃነትን ያንፀባርቃሉ´ ሲሉ የጥያቄዎቹን መነሻ ምክንያቶች ያብራራሉ– ጥያቄዎቹ ወሳኝ የመገናኛ ብዙኃን ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ናቸው። የፍትህ፣ የእኩልነትና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች ናቸው ይላሉ። ልዩ ልዩ

የምርምር ተቋማትም መገናኛ ብዙኃንን ከብዝሃነት አንፃር እንደሚያጠኑ ለማሳየት አሜሪካንን እንደ አብነት አስቀምጠዋል።

በአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ውስጥ ሴቶች ምን ያህል ስፍራ እንደተሰጣቸው፣ የጥቁር አሜሪካውያን ድርሻ ምን ያህል እንደሆነ፣ ይህን ወይም ያን የኅብረተሰብ ክፍል የሚወክሉ ዜጎች ተገቢውን ስፍራ ስለመያዛቸውና እያንዳንዱ የኅብረተሰብ ክፍል በአግባቡና ፍትሃዊ በሆነ መልክ በመገናኛ ብዙኃን ውጤቶች ውስጥ የተገለፀ መሆኑን ማረጋገጥ የልዩ ልዩ ጥናቶች ትኩረት እንደሆነ አፅንኦት በመስጠት አብራርተዋል።

የብዝሃነትን ጥያቄ በተለያየ መልክ ለማየት የሞከሩት ጥናት አቅራቢው ከእኛ አገር ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማያያዝ ማክዌል የተባለ የዘርፉን ተመራማሪ ዋቢ በማድረግ ብዝሃነት ከተደራሽነት አንፃር የሚኖረውን እንደምታ ሰፊና መሰረታዊ መሆኑን አፅንኦት በመስጠት አስቀምጠውታል። ምክንያቱም መገናኛ ብዙኃን የማኅበረሰቡን የብዝሃነት ገፅታ በሁሉም መልኩ የሚያንፀባርቁ ቢሆኑም እንኳ ለኅብረተሰቡ ተዳራሽ መሆን ካልቻሉ ተልዕኳቸው ግቡን ሊመታ አይችልም፡፡ የመገናኛ ብዙኃን ተዳራሽነት ጥያቄ ለሁሉም የብረተሰብ ክፍሎች የጋራ ችግር ባለመሆኑ ማኅበረሰቡን በተጠቃሚዎችና በተገለሉ ወገኖች ለሁለት በመክፈል ኢ ፍትሃዊ ሁኔታ እንደሚፈጥር ያብራራሉ፡፡

ማኅበረሰቡ ከምጣኔ ሀብት አንፃር ሃብታምና ደሃ ተብሎ እንደሚከፈለው ሁሉ ይህ የተግባቦት ኢ ፍትሃዊነት ማኅበረሰቡን ተናጋሪና አድማጭ፣ ህይወትን ተርጓሚና የህይወት ትርጉም ተቀባይ፣ ባለድምጽና ድምጽ አልባ በሚባሉ ሁለት ወገኖች እንደሚከፍል፣ አሳታፊ ዴሞክራሲን እንደሚያዳክምና ህገ መንግታዊ እሴቶች እንዳይዳብሩ እንቅፋት እንደሚፈጥር ማሳያ በማቅረብ የጽንሰ ሃሳቡን ትክክለኛነት በማረጋገጥ ይደመድማሉ።

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለልጣንን መረጃና በራሳቸው የተዘጋጁ መጠይቆችን መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅትና፣ ሬዲዮ ፋና፣ አዲስ ዘመን፣ ሪፖርተርና ሰንደቅ ጋዜጣዎችን ከውጫዊና ውስጣዊ ገጽታቸው አንፃር ከብዝሃነት ጋር አያይዘው እንዳጠኑ የሚገልፁት ጥናት አቅራቢው ከህገ መንግሥታዊ መርሆዎችና እሴቶች አንፃር ተከታዩ መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል።

የአብዛኞቹ ዜናዎች ምንጮች መንግታዊና መንግታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ባለልጣናት፣ ከፍተኛ ባለሙያዎችና ባለሀብቶች ናቸው፡፡ ለልዩ ልዩ የፖለቲካ የምጣኔ ሀብትና የማህበራዊ ጉዳዮች ባለድርሻ የሆኑ ነገር ግን በሙያም ሆነ በልጣን ስማቸው የሚቀድም ቅጽል የሌላቸው ዜጎች በዜና ዘገባዎች ውስጥ ድርሻቸው ያነሰ መሆኑን፣ የዋናዎቹ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ዜና ዘገባዎች አዲስ አበባ ተኮር መሆናቸውንና በዚህም የአገሪቱ ዋነኛ እውነታ የሆነው ብዝሃነት በዜና ይዘቶች ውስጥ ያለው ፍራ ዝቅተኛ እንደሆነ ይህም ቢያንስ አሳታፊና ዴሞክራሲያዊ የመገናኛ ብዙኃን ስርዓት ለመፍጠር ቁርጠኝነት እንዳላቸው የሚገልጹት የመንግት የዜና ተቋማት ሊሰሯቸው የሚገቡ በርካታ ስራዎች መኖራቸውን የሚያመለክት እንደሆነ ብዝሃነትን ከውጫዊ የመገናኛ ብዙኃን ገጽታ አኳያ የደረሱበት መደምደሚያ ነው፡፡

ከመገናኛ ብዙኃን ውስጣዊ ገጽታ አንፃር ብዝሃነትን ሲፈትሹ የደረሱበትን ደግሞ በሁለት መልኩ አስፍረዋል። አገር አቀፍ ስርጭት ባላቸው መገናኛ ብዙኃን የአማርኛ ዜና ክፍሎች ውስጥ ከሚሰሩት ጋዜጠኞች መካከል ከ75 በመቶ በላይ የሚሆኑት የአማራ ብሄር አባላት ናቸው፡፡  ባለሙያዎቹ ከተገኙባቸው ብሄረሰቦች አንፃር ስብጥሩ የአገሪቱን የብዝሃነት እውነታ የማያንፀባርቅ እንደሆነ የሚያመላክተው የጥናት ውጤት የመጀመሪያው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በእነዚሁ አገር አቀፍ ስርጭት ባላቸው የመገናኛ ብዙኃን የአማርኛ የዜና ክፍሎች ውስጥ ከሚሰሩት ባለሙያዎች ከ85 በመቶ በላይ መሆናቸው ከኃይማኖት አንፃር በመገናኛ ብዙኃኑ ውስጥ ያለው እውነታ የአገሪቱን ገጽታ የማይወክል መሆኑ ነው።

ከዚህ ጥናታዊ ውጤት መረዳት የሚቻለው መገናኛ ብዙኃን የሚገኙበትን ማኅበረሰብ የብዝሃነት ገጽታ የማንፀባረቅ ህገ መንግታዊ ግዴታ ያለባቸው እንደሆነ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የተወሰኑ አመለካከቶችና ፍላጎቶች ብቻ በሌሎች ላይ ገነው የሚወጡበት እድል ሰፊ እንደሆነና በዚህም መግባባትና ፍትሃዊ የሆነ የተግባቦት ርዓት የሚዳከም መሆኑን ነው።

የመገናኛ ብዙኃን ብዝሃነትን ማንፀባረቅ የዴሞክራሲ እሴቶች እንዲዳብሩና የአስተሳሰብ ፅንፈኝነት በሚዛናዊ አተያይ የሚተካበትን መንገድ ይፈጥራል። በዚህ ብቻ ሳይወሰን የተወሰኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ባህላዊና ፖለቲካዊ እሴቶች በሌሎች ላይ የሚጫኑበትን እድል በማስቀረት ሁሉም

የኅብረተሰብ ክፍሎች የየራሳቸውን ቋንቋ፣ ባህልና አስተሳሰብ እንዲያዳብሩም በር ይከፍታል። እነዚህ መነሻዎች ደግሞ የመገናኛ ብዙሃን የብዝሃነት ጽንሰ ሃሳብ ፖለቲካዊ እንድምታዎችን ይጠቁማሉ። ብዝሃነት በማኅበረሰብና በመገናኛ ብዙኃን አምድ ውስጥ ከዜጎች መብቶች መከበርና የዴሞክራሲ እሴቶች መጠበቅ ጋር ቁርኝት ያለው መሆኑም በዋናነት ሊጤንና ሊሰመርበት የሚገባው ጉዳይ ነው።

ሥነ ጽሁፋችንን ከህገ መንግታችን ስሜቶች አንፃር ወደተመለከተው ውይይት ማጠቃለያ ስመለስ– ህገ መንግታችን ለኪነ ጥበብ ለነ ጽሁፍና ለፈጠራ ባለሙያዎች ያጎናፀፈው መብት ርዓታዊ ብቻ ሳይሆን ለጥበባዊ ራም አጋዥ እንደሆነ ማረጋገጥ ይቻላል። ታዲያ የአገራችን የነ ጽሁፍ ባለሙያዎች ይህን ህገ መንግታዊ ዕድገት በኅብረተሰቡ ውስጥ እንደምን እንደሚሰሩበት ቢያስተውሉ፣ ቢጠይቁ ወይም ቢመለከቱ ለነ ጽሁፋዊ ራቸው መነሻ የሆነ የላቀ ጥበባዊ ሃሳብ እንደሚያገኙ ምን ያጠራጥር ይሆን? ለምን ቢሉ የማንኛውም የነ ጽሁፍ ማጠንጠኛውና የሂሳዊ እውነታ ማንፀባረቂያ መስታወቱ የኅብረተሰቡ ርዓት በዓይነቱ እና በየእለት ህይወቱ እንዴት እየተንፀባረቀ ነው የሚለው ዐቢይ ጉዳይ ስለሆነ ብዬ ነው።

በርግጥ ደራሲያን የምንፈልጋቸውን እና መንገድ የሚያሳዩንን ጠንካራ ራዎች እንዲሰሩ መንግት በተለያዩ መልኮች ህገ መንግታዊ ዋስትና ከመስጠት የሚመነጩ ድጋፎችን ማድረግ ይጠበቅበታል። ለምሳሌ ስልጠናዎችን ማዘጋጀት ሊሆን ይችላል፣ የታተሙ መፃህፍት ወደ ህዝቡ የሚደርስበትን ሁኔታ በማመቻቸትም ሊሆን ይችላል፣ ውድድሮችን አዘጋጅቶ ማበረታቻ በመስጠትም የሚገለጽ ድጋፍ ሊሆን ይችላል፡፡ ብቻ ሁሉም ዓይነት ድጋፎች መንግነ ጽሁፍን የማሳደግ ግዴታ አለበት ከሚለው አንቀጽ የሚመነጩ የድጋፍ ዓይነቶች ናቸው።

ልክ እንደ አሜሪካኖቹ (ቀደም ብዬ ጠቁሜያለሁ አሜሪካኖቹ ህፃናቱን የሚያስተምሩበት መንገድ በተለይም ከህገ መንግትና ዜግነት ጉዳይ ጋር በተያያዘ የመንግት ቀዳሚ ትኩረት ነው) የሚመለከታቸው መንግታዊ ተቋማት በህፃናቱ ላይ መስራት ግዴታቸው መሆኑን ተገንዝበው ተጨባጭ የሆነ እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ዳሩ ግን ይህ ሁሉ ሊሳካ የሚችለው ደራሲያን ራሳቸውን ከላይ ለተጠቅሱት ተግባራት ሁሉ ሲያዘጋጁ እና አገራችንን ካለችበት አዘቀት ለማውጣት አቅም አለን ብለው ማመን ሲጀምሩ እንደ ጀርመኖቹ የልማት ኃይሎች ግሩፕ 47 መሆን ሲቻላቸውና ያሉበትን እና ያለንበትን ወቅታዊ ሁኔታ ማገናዘብ ሲችሉና ሲረዱ ነው።