የህገመንግስቱ ቱርፋቶች የህዝቦች አንድነት መገለጫ

ወ/ሪት ሁሉንአየሁ በላይ

                   (ከየቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት)

ሀገራችን ኢትዮጵያ የራሳቸው መገለጫ ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋና ዘዬ ያላቸዉ ከ80 በላይ የሚሆኑ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መኖሪያ ሀገር ናት፡፡ እነዚህ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ራሳቸዉንና አገራቸውን ከውጪ ወረራ በመከላከል ማንነታቸውን አስጠብቀው ለዘመናት የኖሩ ኩሩ ህዝቦች ናቸዉ፡፡ ይሁንና አብሮነታቸዉ ላይ ያጠሉ የታሪክ ጠባሳዎች ነበሩ፡፡

ቀደም ባሉት ዘመናት መንግስታትና ገዢዎች ህዝቡ ላይ የጭቆና ቀንበር በመጫን የሀገራችን ህዝቦች የእኩልነት መብታቸዉ ተገፎ በገዛ አገራቸዉ እንደሁለተኛ ዜጋ ሲቆጠሩ ኖረዋል፡፡ ግን ዛሬ የሀገራችን ብሔር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ህገ መንግስታዊ መብታቸዉ ተከብሮ ቋንቋቸዉ፣ ባህላቸዉ እና ታሪካቸዉን የማዳበርና የመጠቀም መብታቸዉ እዉን ሆኗል:: በተጨማሪም ራስን በራስ የማስተዳደር፣ በቋንቋቸዉ የመስራት፣ በቋንቋቸዉ የመማር፣ የራሳቸዉን ባህልና ወግ የማሳድግና የመግለጽ፣ ታሪካቸዉን የመንከባከብ መብት በህገመንግስቱ ተረጋግጦላቸዋል፡፡ በዚህ ህገ መንግስት አማካይነት፣ በህዝቡ ሲነሳ የነበረውን የረጅም ጊዜ ራስን የማስተዳደር ጥያቄ ለመጀመሪያ ጊዜ በመመለስ በሌላ በኩል የህዝቦቿን የጋራ እድል በጋራ በመፈቃቀድ እንዲወስኑ በር የከፈተ፣ ለዘላቂ ስላም፣ ለቀጣይ ልማት፣ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና ለህግ የበላይነት መሰረት የጣለ ህገ መንግስት ነው፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞም የሀገራችን ህዝቦች መብታቸዉና እኩልነታቸዉ ያለምንም ገደብ ሙሉ እዉቅና በማግኘት በብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ቀን ታስቦ እንዲዉል ተደርጓል፡፡ የበአሉ መከበር ሁሉም ብሄሮች የማንነት መገለጫዎቻቸውን በማውጣትና በአንድ ቦታ ላይ በመታደም አንዱ ሌላውን እንዲያውቅ፣ በመካከላቸው ያለውን መከባበርና መቻቻል እዲገልጹ ማድረግ የሚያስችል ዝግጅት ይፈጥራል፡፡ ይህ ዝግጅት ደግሞ በልዩነት ውስጥ ያለውን አንድነታቸውን ሊታይ በሚችል ደረጃ ተጨባጭ አድርጎ አቅርቦታል፡፡ ይህም ህገ መንግስቱ ለብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ካተረፈላቸው ቱሩፋቶች ዉስጥ አንዱ ብቻ ሳይሆን ዋናው ነዉ፡፡ ይህ የህዝቦች አንድነትና አብሮነታቸዉም ሀገራችን እያስመዘገበች ላለችው ፈጣን የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እድገት  የበኩሉን አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡

በሀገሪቱ ዉስጥ እየተመዘገበ ያለዉ ቀጣይነት ያለዉ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት መንገዶች፣ ድልድዮች እንዲሁም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሽፋን መጨመር፣ የቴሌኮሙኒኬሽን ዝርጋታ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች መስፋፋት እና ሌሎች የልማት ዘርፎች መስፋፋታቸዉ ህዝቦች በአንድነታቸዉ ጠንክረዉ በመስራት ያመጡት የሀገሪቱ እድገት መገለጫዎች ናቸዉ፡፡

ለኢትዮጵያ ለህዝቦች አንድነት የጋራ ርብርብ እየተሰራ ያለዉ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ እንደ ዋና ማሳያ ይሆናል፡፡ የህዳሴዉ ግድብ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ሁሉም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ከጫፍ እስከ ጫፍ የኔ ነዉ በማለት በራሳቸዉ ወጪ ግድቡን እየገነቡ መሆናቸዉ በህዝቦች መካከል የተፈጠረዉ አንድነት መገላጫ ነዉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም ሀገራችን ከነበረችበት ግብርና መር የእድገት ስትራቴጂ ወጥታ ወደ ኢንዱስትሪ መር ስትራቴጂ ለመሸጋገር እያደረገች ያለችዉ እንቅስቃሴ አሁን ካለችበት የኢኮኖሚ ደረጃ በፍጥነት ለመሸጋገር የህዝቦች አንድነት በጥምረት ተሰባስቦ መስራት ዋነኛ ቁልፍ ተግባር መሆኑን እና ይህም የሀገሪቱ የኢንዱስትሪ እድገት ካለፉት ዓመታት የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ማስቻሉ ነው፡፡

ሀገሪቱ ከኢንዱስትሪዉ ዘርፍ የምታገኘዉን ጥቅም ከየትኛዉም ጊዜ በተሻለ ከፍ ለማድረግም የህዝቦች ጠንካራ የሆነ የመተሳሰብና የአብሮነት ባህል ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ ይህ ሀገሪቱ የኢንዱስትሪዉን ዘርፍ ለማሳደግ እያደረገች ያለዉን የተጠናከረ ርብርብ ቀጣይነት እንዲኖረዉ ያስችላል፡፡ እንዲሁም ከሀገር ዉጪ የሚመጡ ባለሀብቶች ቁጥርና የሀገር ዉስጥ ባለሀብቶች ተሳትፎ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡

የባለሀብቱ ተሳትፎ እና የኢንዱስትሪዉ እድገት ከጨመረ ደግሞ በሀገሪቱ ዉስጥ በሚገኙ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች እኩል የሆነ ተጠቃሚነት ይኖራቸዋል፡፡ አንዱን ከአንዱ ያላበላለጠ የኢኮኖሚ እድገት ይመዘገባል፣ የሁሉም ህዝቦች የስራ ባህል ይጠናከራል፡፡ የተሻለ እድገት የተሻለ ለዉጥ በሀገሪቱ ዉስጥ ይመዘገባል፡፡ ለዚህ እድገት መስፋፋት ደግሞ ህገ መንግስቱ ካመጣቸዉ ቱሩፋቶች ዉስጥ የብሔሮች ብሔረሰቦች አንድነት፣ እኩልነት እና በሀገሪቱ ዉስጥ ብዙ ሆነዉ ግን እንደ አንድ ተከባብሮና ተስማምቶ የመኖር ባህላቸዉ ለአንድነታቸዉ መገለጫ መሆኑ ነው፡፡

በተጨማሪም ለአንዲት ሀገር እድገት ህልውና በዛች ሀገር የሚኖሩ ሁሉም ዜጎች የተለያየ እምነት፣ ቋንቋ፣ ብሄር መኖሩ ሳይገድባቸው ሁሉም በአንድነት እና በመተሳሰብ በሰላም ስርተው ለማደግ እና ለሀገሪቱም ፈጣን የእድገት ግስጋሴ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት፣ ህገ መንግስቱ ያጎናጸፋቸውን ህገ መንግስታዊ መብት ተጠቅመው መንቀሳቀሳቸው እንደ ዋና ቁልፍ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ይህም ሀገራችን ከአደጉት ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ እያደረገች ያለችውን እንቅስቃሴ ከግብ ለማድርስ ያግዛል፡፡

ለዚህም ሁሉም ብሄሮች በያሉበት እና በተሰማሩበት ስራ እንዲሁም በየትኛውም አካባቢ እንደፈለጋቸው ተንቀሳቅሰው በመተሳሰብ እና በመከባበር አንዳቸው ከአንዳቸው ሳይለያዩ በፍቅር እና በሰላም ሰርተው፣ ውለው እንዲገቡ አስችሎቸዋል፡፡ ይህም ህገ መንግስቱ ካጎናጸፋቸው መብቶች በመነሳት ሁሉም ሰው በየትኛውም ቦታ ተንቀሳቅሶ የመስራት ሙሉ የዜግነት መብቱን ተጠቅሞ መስራት እንዲችል አድርጎታል፡፡

በአጠቃላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች መኖሪያ እንደ መሆኗ መጠን ሁሉም በመተባበርና በአንድነት ለሀገራችን እድገት መፋጠን የየራሳቸውን ድርሻ በመወጣት ሀገሪቱን በአጭር ጊዜ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ለማሰለፍ የሁሉም ሰው ተሳትፎ የጎላ ሚና ስላለው ሁሉም በተሰማራበት ስራ ብሄር፣ ሀይማኖት፣ ቋንቋ ሳይል የራሱን አስተዋጽኦ በማበርከት ለዘመናት ተጠብቆ የኖረውን፣ በብዙ ብሄሮች ውስጥ ግን እንደ አንድ ሆኖ የቆየውን ማንነታችንን ማስቀጠል እና የሀገሪቱን ሰላም አስጠብቆ መኖር የሁሉም ሰው ሀላፊነት መሆን ይገባዋል፡፡  