የኢትዮጵያ ህዳሴ ጉዞ

መሰረተ ኢትዮጵያ

  1.  

 

 

  • የብዝሃነት ተምሳሌት፣ የሰዉ ልጅ መሰረተ ምድር ከመሆኗም ባሻገር የስልጣኔ በር ከፋች የሆነች ቀዳማዊት ሃገር መሆኗ ይታወቃል፡፡ ቢሆንም ቅሉ በተለያዩ ጊዜያት በዘር ሀረግም ይሁን በአምባ ገነንነት ሲያስተዳድሯት የነበሩ መሪዎች ለረጅም ዘመናት በአብሮነት ተቻችሎና ተከባብሮ በትጋት ይሰራ የነበረዉን ህዝብ በጅምላ በመጨፍጨፍ በአንድ ጉድጓድ ውስጥ ሲቀብሩና የዕድገት ተምሳሌት የነበረችን ብርቅዬ ሀገር ኢትዮጵያ በድህነት አረንቋ ዉስጥ ከሚገኙ የአለም ሀገራት መካከል ቀዳሚዋ ኦክስፎርድ ዲክሽነሪ ላይ የተቀመጠች ምስራቅ አፍሪካዊት ሀገር ማድረጋቸዉ ታሪክ  የማይረሳዉ ተግባር ነዉ፡፡ የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የረጅም ዘመናት ግፍና ሰቆቃ ብሎም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ማሽቆልቆል እንቅልፍ የነሳቸዉ ጥቂት ሰላም ወዳድ ቁርጠኛ ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በመሰባሰብ የሀገራቸውን ህዝብ ከግፍና ሰቆቃ እንዴት መታደግ እንዳለባቸው ከተወያዩ በኋላ የኢትዮጵያ ሰላም ሊረጋገጥ የሚችለው አምባገነኑንና ዕብሪተኛዉን መንግስት በትግል ማስወገድ ሲቻል ብቻ እንደሆነ ስምምነት ላይ ደረሱ፡፡

 

  • ቆራጥና የሃገራቸው ዜጋ ግፍ ገፈት ቀማሽ መሆን ሰላም የነሳቸው ዜጎች የትግል ስልት በመንደፍ ለ17 ተከታታይ ዘመናት እልህ አስጨራሽ ትግል በማድረግ በአለም ሀያላን ሀገራት ሳይቀር የፈጣሪን ያህል ይፈራ የነበረውን፣ ጅምላ ጨራሹንና አምባገነኑን መንግስት ዳግም ላይመለስ ግንቦት 20/1983 ዓ.ም በድል ገረሰሱ፡፡ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ለረጅም ዘመናት ተነፍገው የነበሯቸውን መብቶችን ማጎናጸፍ የሚችል ህገመንግስት ህዝቦች ራሳቸው በመረጧቸው ተወካዮች ረቂቁ ተዘጋጅቶ ለህዝብ ይፋ ተደርጎና ተስማምተውበት ጸደቀ፡፡ በጸደቀውም ህገመንግስት መሰረት ህዝቦች መሪያቸውን መረጡ፤ ሀገሪቱን ለመምራት ከህዝብ ሀላፊነት የተሰጠው መንግስት የሀገሪቱን የቀደምት የእድገት ፊታውራሪነት ለመመለስና የብሄረሰቦችን የቃልኪዳን ሰነድ ህጉ በሚያዘው አግባብ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ለዜጎች እኩል ተጠቃሚነት፣ በትጋትና በቁርጠኝነት ሊሰራ ቃል በመግባት የመሪነት ስራውን በይፋ ተረከበ፡፡ የመሪነት ስራውን በህዝብ ይሁንታ የተረከበዉ የኢህአዴግ መንግስት የህዝቦችን ሉዓላዊነት ባከበረ መልኩ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት የበለጸጉ በርካታ የአለም ሀገራትን ተሞክሮ በመቀመር  ወደሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ በመለወጥ አጭር በሚባል ጊዜ ውስጥ ባለ ሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ ዕድገት ባለቤት እንድትሆን በማስቻል በድህነት አረንቋ ስር ካሉ ሀገራት ስሟን በማስወገድ ዳግም ታሪክ ሰሩ፡፡

 

  • እያስመዘገበች የመጣችው የኢኮኖሚ ዕድገትና የተረጋጋ ሰላም መኖር ዋና ከተማዋን የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንድትሆን ከማስቻሉም በላይ የአለም ሀገራት ኢንቨስተሮች መዋለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ የሚመርጧት ቀዳሚዋ አፍሪካዊት እመቤት ለመሆን በቅታለች፡፡  የህዝቦችን ደህንነትና የሀገሪቱን ሰላም ለማስጠበቅ የሚያወጣቸው የጸረ ሽብር ህጎች የተዋጣላቸው በመሆናቸው በአለም ተመራጪ የሰላም አስከባሪ ኃይል ባለቤት የሆነች ብርቅየ ሀገር ለመሆን ችላለች፡፡

 

  • ብሄረሰቦችና ህዝቦች የኢኮኖሚ ዕድገትና ፍላጎት የተመጣጠነ ይሆን ዘንድ በትጋት የሚሰራው መንግስት የሀገሪቱ የምንጊዜም ጠላት የሆነውን ድህነት ከምንጩ ለማድረቅ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ነድፎ እመርታዊ የሆነ ለውጥ በማስመዝገብ ላይ ነው፡፡

 

  • ሀገር የማሳደግ ቁርጠኝነት የሚያመለክቱ በርካታ አይደፈሬ የተባሉ ለእድገት መሰረት የተጣለባቸው ፕሮጀክቶችን በመንደፍና ወደተግባር በመለወጥ በ2017 መካከለኛ የዕድገት ደረጃ ላይ ከደረሱ ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ ሌት ተቀን እየታተረ ይገኛል፡፡ ማሳያ ከሆኑት ፕሮጀክቶች መካከል በአምላክ ተአምራዊ ሀይል ካልሆነ በስተቀር በኢትዮጵያ አቅም የማይደፈር ሲባል የኖረውን አባይን የመገደብ ስራ ይፋ ሲያደርግ የዓለም ሀገራት ምን አይነት ዕብደት ነው በማለት ተሳለቁ፤ ይሁን እንጅ የድህነትን አከርካሪ በመስበር የእማማ ኢትዮጵያን መጥፎ ታሪክ በመቀየር ዳግም በአርዓያነት የምትጠቀስ ሀገር ለማድረግ በቆራጥነት የተነሳው የህዝቡን የልማት ጥማት የተረዳው ልማታዊው መንግስት ተግባራዊ ሥራውን በሀገሪቱ ህዝብ የነቃ የገንዘብ ድጋፍ ሲጀምር የመንግስትን የልማት ቁርጠኝነት የተረዱት፣ የኢትዮጵያ እድገት የእግር እሾህ የሆነባቸዉ ሀገራትና ግለሰቦች ምንም ዓይነት የዉጭ እርዳታ እንዳናገኝ ሌት ተቀን በትጋት ተንቀሳቀሱ፡፡

 

ይሁን እንጂ፣ መንግስትና ህዝብ ይችን ቀደምት የስልጣኔ ተምሳሌት የነበረች ሃገር ታሪክ ዳግም ለመመለስ ቆርጠው የተነሱ በመሆናቸው እነሆ የኢትዮጵ ያ የዕድገት ብርሃን ፈንጣቂ፣ ለጠላቶቻችን የእግር እሾህ የሆነዉ ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የግንባታ ሥራ ከግማሽ በላይ ደርሷል፡፡ የግድቡ ስራ እውን እየሆነ መምጣቱ እንቅልፍ የነሳቸው የምንጊዜም የውስጥና የውጭ ጠላቶች የሀገሪቱ የህዳሴ ጉዞ የሚቋረጠዉ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በብዝሃነት ላይ የተመሰረተ የእንልማ ፍላጎት ሲለያይና በጋራ ለመበልጸግ በጋራ ማሰብ፣ በጋራ ለልማት መቆም . . . የሚሉ አስተሳሰቦችን በመስበር ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው መንግስት ለዚህኛዉ ብሄር አዳልቷል፤ የእንልማ ጥያቄህን በአግባቡ አልመለሰም፤ የነደፈው የህዳሴ መስመር ሆን ብሎ ይህን ክልል የሚጎዳ ነዉ፤ እከሌ የሚባል ቦታን እከሌ ለተባለ ሀገር ሸጧል ወዘተ. የሚሉ መሰረተ ቢስ አሉቧልታዎችን በማህበራዊ ድረ ገፆች እየለጠፉ በመንዛት እኩልነቱ ተረጋግጦ ሰላሙ ተከብሮ መቻቻልንና በጋራ ሰርቶ መበልፀግን፣ እንዲሁም ብዝሃነትን መርሁ በማድረግ ድህነትን ታሪክ ለማድረግ ቆርጦ የተነሳውን ህዝብ ተቆርቋሪ መስሎ አጉል በመፈትፈት፣ ሰላሙን በማወክና የሀገሪቱ መሰረተ ልማቶች እንዲወድሙ እና ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች እርስ በርሳቸዉ ጦርነት እንዲከፍቱና ሀገሪቱ የጦር አውድማ በመሆን እንደ ሶሪያ ምድር እንድትሆን በመስራት ላይ ናቸዉ፡፡ በመሆኑም መላው የሀገራችን ህዝቦች ኢትዮጵያን የጦር ቀጠና በማድረግ የተያያዘችውን የህዳሴ ጉዞ ለማደናቀፍ ቆርጠው የተነሱ የውስጥና የዉጭ አሸባሪዎች እኩይ ተልዕኮ አስፈጻሚዎች መሆናችንን በመተው፣ የእነኚህን አሸባሪዎች አላማ በጥልቀት በማጤን እየፈጠሩት ያለውን የሽብር ተልዕኮ በማውገዝ በጥቂት ቆራጥ የሀገራችን የቁርጥ ቀን ልጆች ተዓምራዊ ተጋድሎ ያገኘነውን ሰላም፣ እኩልነት፣ የሰከነ መልካም አስተዳደርና የማይቀለበስ የህዳሴ ጉዞ  በማስቀጠል ሽብርተኝነትን አምርረን የምንጠላና የሀገራችንን የተረጋጋ ሰላምና የተፋፋመ የህዳሴ ጉዞ ለማደፍረስና ለማደናቀፍ እኩይ ተልዕኮ አንግበው ለሚንቀሳቀሱ ፀረሰላም ኃይሎች የማንበረከክ መሆናችንን የአለም ህዝብ የሚያውቀው እውነታ መሆኑን መዘንጋት እንደሌለባቸዉ ለማሳየት ሁሉም ኢትዮጵያዊ የዜግነት ግዴታዉን መወጣት ይኖርበታል፡፡