የኢሬቻ በአል በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ በየአመቱ በታላቅ ድምቀት የሚከበር፣ በናፍቆትም የሚጠበቅ ባህላዊና ሀይማኖታዊ በአል ነው፡፡ ይሀው በአል በባህላዊ ወግና ስርአት መሰረት ከጥንት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የኖረ፣ ህዝቡ በጋራ ተሰብስቦ ክረምቱ አለፈ እነሆ መስከረም ጠባ፤ ሀገራችንን፣ ቤታችንን፣ ሰብላችንን፣ ቤተሰባችንን፣ ከብቶቻችንን ሁሉ ሰላም አድርግልን፤ ባርክልን፤ ጠብቅልን ብሎ በአባ ገዳዎች መሪነትና መራቂነት በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ በአመት አንድ ግዜ በጋራ ተሰባስቦ ለፈጣሪ ምስጋናና ጸሎት የሚያቀርብበት ታላቅ መንፈሳዊ በአል ነው፡፡
እሬቻ ሙሉ በሙሉ የእኛና የእኛ ብቻ የሆነ፣ በሌላው አለም ዘንድ የሌለና ብርቅዬ የኢትዮጵያ አመታዊ መንፈሳዊ ክብረ በአል ሲሆን ዩኔስኮ በአለም ቅርስነት ሊመዘግበው ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡
እሬቻ ለዘመናት ሲከበር የኖረው በደብረዘይቱ ሆራ አርሰዲ ሀይቅ ነው፡፡ በአሉን ለማክበር ከመላው ኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ከዋዜማው ጀምሮ ወደ ስፍራው ይጎርፋል፤ በአካባቢውም ያድራል፡፡ ባህላዊ ልብሶቹን ለብሶ ያደምቀዋል፡፡ ይበላል፤ ይጠጣል፤ ይጨፈራል፡፡ “ለዘንድሮው እንዳበቃሀን ለመጪው አመት በሰላም አድርሰን” የሚል ጸሎቱን ያደርሳል፡፡ ባለፈው አመት ወደ ስፍራው ሲሄድ ለዘንድሮው አመት የተሳለውንና የተሳካለትን ይዞ ይመጣል፡፡ ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል፡፡ ይህ አመታዊ ክብረ በአል ባህላዊና መንፈሳዊ በመሆኑ ፍጹም ሰላማዊ የሆነ በአል ነው፡፡
ባለፈው እሁድ መስከረም 22 2009 አ.ም በአሉን ለማክበርና ለመታደም ወደ ደብረዘይት ሆራ አርሰዲ በሄደውና በተገኘው ሰላማዊ ህዝብ ላይ የተፈጠረው እጅግ ዘግኛኝና ሰቅጣጭ ሁኔታ የህዝብን ልብ ያደማ፣ ክፉኛ ያስለቀሰ፣ ያስነባና ለመገመትም የሚያዳግት ሁኔታ ነው የተከሰተው፡፡ ጉዳዩ እንዲህ ነው።
እንደሚታወቀው ሀይማኖታዊ በአሎች የፖለቲካ መድረኮች አይደሉም፡፡ ሀይማኖታዊ በአሎች ተጀምረው እስኪያበቁ ድረስ ፍጹም ሰላማዊ መንፈስና ድባብ በተመላበት ሁኔታ መካሄድና መቋጨት ነው የሚገባቸው፡፡ ሀይማኖታዊ-መንፈሳዊ በአሎችን ለእኩይ የፖለቲካ አላማ ሲባል መጥለፍ፣ ማሰናከልና ሁከት እንዲነሳ ማድረግ በባህላችን ውስጥ ያልተለመደ ከመሆኑም በላይ እጅግ የከፋ ጸረ ህዝብ ባህርይ ነው፡፡ የአክራሪ ሀይሎቹ አላማ ግጭት ቀስቅሶ ህዝብ እንዲጎዳና በመንግስት ላይ ያለው ተቃውሞ እየበረታ እንዲሄድ አመጽ እንዲቀጣጠል ማድረግ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በሰለጠኑ ፀረዲሞክራሲ ሀይሎች የሚሰራ ስራ ነው። የእንደዚህ አይነቱ ኢሰብአዊ ተግባር ኤክስፐርቶች በየሀገሩ ይሰለጥናሉ፤ ስምሪት ይሰጣቸዋል፡፡ በየተመደቡበት ሀገራትም የቀለም አብዮቶችን ይቀሰቅሳሉ፤ ህዝብ እርስ በርሱ ይጫረስ ዘንድም የሚችሉትን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ የህዝብ አመጽና ሁከት፣ ግርግርና ትርምስ እንዲፈጠር ያለመታከት ሲሰሩ የነበሩ የአውሮፓም ሆኑ የአረቡ ሀገራት እንዳሉ ይታወቃል፡፡ እነዚህ ደግሞ የየራሳቸው ብሄራዊ ጥቅምና ፍላጎት ያላቸው ወገኖች ናቸው። ጉዳዩን ከዚህ አንፃር ስንመለከተው እኛም ላይ እየተደረገ ያለው ይሄው ነው።
የግብጽ ደኅንነት በርካታ አክራሪ ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን እና የኦነግ አባላትን አሰልጥኖ በስውር ወደ ሀገር ውስጥ እንዳሰማራ ይታመናል፡፡ ግብፆችም ሆኑ ሌሎቹ በስውር አድፍጠው ለሚገኙት ወኪሎቻቸው የሶሻል ሚዲያ ስራዎች እንዲሰሩ አሰልጥነው (በፌስቡክ) ለአመጽ ማቀጣጠያና የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ ስራዎቻቸው ዘመናዊ አይፖድ ሞባይል ስልኮችን፣ ላፕቶፖችን በብዛት ወደ ሀገር ውስጥ አስገብተው አስታጥቀዋቸዋል፡፡ የስነልቦና ጦርነት በማወጅ እየተዋጉ፣ ህዝብን በማሸበርም የሀሰት ዘመቻ እያደረጉ ያሉትም በዚሁ ነው፡፡
በነዚህ የሰለጠኑ ሀይሎች በመጠቀም ነው ሽብር በመንዛት፣ ሁከት በማሰራጨት የፈጠራ ዜናዎችን በመፃፍ አመጽ እንዲቀጣጠል እየተረባረቡ ያሉት፡፡ ለጊዜው አብዛኛው ዜጋ ከጀርባ ያለውን ሀገር አፍራሽ የግብጽንና የሻእቢያን ረዥምና ስውር እጅ ለማስተዋል አልቻለም፡፡ መንግስት ይመጣል፣ ይሄዳልም፤ ሀገርና ትውልድ ይቀጥላሉ፡፡ ይሄን አርቆ በማየት ሀገርንም ህዝብንም ከጥፋት መጠበቅ ተገቢ ነው፡፡
በደብረዘይቱ/ቢሾፍቱ የእሬቻ በአል ላይ ሰላም ለማደፍረስና ሁከት ለመፍጠር አስቀድመው፣ አቅደው፣ ተደራጅተው የመጡ ወገኖች ይሄንኑ ሰላማዊና መንፈሳዊ ክብረ በአል የአክራሪ ተቃውሞ የፖለቲካ መድረክ ለማድረግ ባደረጉት እንቅስቃሴ በተነሳው ግርግርና ትርምስ የበርካታ ሰላማዊ ንጹሀን ዜጎች ሕይወት ጠፍቶአል፤ ቀደም ሲል እንዳልነው ድርጊቲ እጅግ ሰቅጣጭና ክፉኛ አሳዛኝ ነው፡፡ ይህን ድርጊት ለመፈጸም የተንቀሳቀሱት የሽብር ሀይሎች ከነጃዋር መሀመድ፣ ከግብጽ መንግስት፣ ከሻእቢያና ከመሳሰሉት የተሰጣቸውን ተልእኮ አንግበው ነው፡፡
እነዚህ የኦነግ ክንፎች በሰላም ከቤቱ የወጣው ህዝብ ሀገር አማን ብሎ፣ በቦታው ተገኝቶ እያለ ሀይማኖታዊና መንፈሳዊ በአሉን በመርገጥ፣ ከአባገዳዎቹም ማይክሮፎን በመቀማት ያልተገባ ሁከትና ትርምስ ፈጥረዋል፡፡ ፖሊስ ግርግሩን ለመበተንና ሽብርተኞቹ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ለማድረግ የጭስ ጋዝ ሲተኩስ (ከህዝቡ ብዛት የተነሳ በመረበሽ) ለማምለጥ በሚደረግ ሙከራ ብዙዎች ተረጋግጠው ህይወታቸው አለፈ፡፡ አካባቢው ገደላማና ሀይቅ ያለበት ስፍራም በመሆኑ ብዙዎቹም ሀይቅ ውስጥና ገደል ውስጥ በመግባት ህይወታቸው አለፈ፤ እድሜ ለጨካኙ ኦነግና ልጁ ጃዋር መሀመድ፡፡
የጥፋት ሴራውን ያቀነባበሩና የመሩት ሀይሎች በየትኛውም መስፈርት ቢሆን ጸረ ህዝብ አቋም፣ እምነትና አላማ ያላቸው፣ በምንም መልኩ ህዝብን ሊወክሉ የማይችሉ፣ ስለህዝብም የማያስቡ፣ የማይጨነቁ፣ ለህዝቡም ባህላዊና ሀይማኖታዊ እምነት እሴት ምንም አይነት ክብር የማይሰጡና በኦሮሞ ህዝብ ውስጥ ምንም አይነት ቦታ የሌላቸው መሆኑን በአደባባይ ያረጋገጡበት ኢሰብአዊ ተግባር ነው፡፡
ህዝብን አጠቃላይ ባህሉን እና እምነቱን የሚያከብር ማንኛውም ወገን፣ የፈለገው አይነት የፖለቲካ አመለካከት ቢኖረውም፣ ይህን አይነቱን አስከፊና ነውረኛ ድርጊት አይፈጽምም፤ በህዝብ እምነትም አይሳለቅም፤ መንፈሳዊ በአልን ወደ ፖለቲካ መድረክነት ለመለወጥ አይሄድም፡፡
እነኦነግ ለህዝብ ክብር ቢኖራቸው ኖሮ የኦሮሞ ህዝብ በአመት አንድ ግዜ ሀይማኖታዊ ምስጋና ለፈጣሪው በሚያቀርብበት፣ በአሉን በጋራ በሚያከብርበት የእምነት ቦታ ላይ ፖለቲካዊ አጀንዳቸውን ለማራመድ ባልሞከሩም ነበር፡፡ ይሄ የሚያሳየው ለባህላዊ አባገዳዎችም ሆነ ለመንፈሳዊ ስርአቱ ያላቸውን ወደር የሌለው ንቀት ነው፡፡ ፖለቲካና ሀይማኖት በፍጹም አይገናኙም፤ ይህ ደግሞ በወሬ ብቻ ሳይሆን ህገመንግስታዊም ነው፡፡ ይህ ማለት የትኛውም የፖለቲካ ሀይል ፖለቲካውን ይህን በመሰለ ህዝባዊ ሀይማኖታዊ በአል ላይ ጣልቃ በማስገባት ለመጠቀም መሞከር በፍጹም አይችልም ማለት ነው፡፡ በእሬቻ መንፈሳዊ ክብረ በአል ላይ የተቃውሞ ፖለቲካን ማራመድ ተቀባይነት የለውም፡፡ ፖለቲካና ሀይማኖት ሙሉ በሙሉ የተለያዩ ናቸው፤ ሊገናኙም አይችሉም፡፡
ጽንፈኞቹ አክራሪ የኦነግ ሀይሎች በእሬቻ መንፈሳዊና ሰላማዊ ክብረ በአል ላይ በቀሰቀሱት ሁከትና ትርምስ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ የብዙ ወገኖቻችን ህይወት አልፎአል፡፡ ህይወታቸው ያለፉትን ሳንጨምር፣ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ዛሬም በየሆስፒታሉ የሚገኙት ወገኖቻችን ብዙዎች ናቸው፡፡ ይሄ የሚያሳየው ኦነግም ሆነ አባላቱ ወይንም ደጋፊዎቹ ለኦሮሞ ህዝብ ባህላዊና መንፈሳዊ እምነት ምንም አይነት ክብር እንደሌላቸው ነው፡፡ ባህላዊ እሴቱን ሙሉ በሙሉ ረግጠውታል፤ አባገዳዎችን ንቀዋል፡፡
ጉዳዩ መንግስትን የመቃወም/ያለመቃወም ብቻም አይደለም፡፡ ኦነጎች የተቃወሙት ዘመናትን ተሻግሮ ከትውልድ ትውልድ፣ ከዘመን ዘመን በመሸጋገር ሲከበር የኖረውን የኦሮሞ ህዝብንና የአባገዳዎችን ጥንታዊ ባህላዊ እሴት፣ መንፈሳዊ ስርአትና በአልም ጭምር ነው፡፡
ጽንፈኛዎቹ አክራሪ ሀይሎች ተቃውሞአቸውን በዚህ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ፣ ሰላምም በሚለመንበት ታላቅ መንፈሳዊ ስነስርአት በሚካሄድበት ቦታ ላይ ቅጥ ያጣ ተቃውሞን በማሰማት ክብረበአሉ እንዲስተጓጎል ከማድረግም አልፈው በሰላም ጸሎት አድርገን ወደቤታችን እንመለሳለን ብሎ የወጣውን ህዝብ ባልተጠበቀ ሁኔታ ለከፋ አደጋ ዳርገውታል፡፡ የበርካታ ዜጎች ህይወትም እንዲጠፋ ምክንያት መሆናቸው የሚያሳየው የኦነግንና የነጃዋር መሀመድን ፍጹም ጸረ ህዝብነትና የሚከተሉትን አክራሪና ጽንፈኛ አሸባሪ እስላማዊ መስመር መሆኑን ነው፡፡ አክራሪ እስላማዊ ሀይሎች ዋሀቢስቶችም ሆኑ ሰለፊዎች ሀይማኖታዊና መንፈሳዊ ክብረበአሎች እንዲከበሩ አይፈቅዱም፤ ለማጥፋትም ብዙ ሰርተዋል፡፡ በውጭ ሀገራት ቲምቡክቱን የመሳሰሉ ብዙ ዘመናትን ያስቆጠሩ በቅርስነት የተመዘገቡ ጥንታዊ የእምነት ስፍራዎችን ጭምር አቃጥለዋል፤ በፈንጂም አጋይተዋል፤ ከእነሱ እምነት ውጪ ያሉ ዜጎችንም አጥፍተዋል፡፡
ባጠቃላይ፣ ኦነግ ውስጥ አክራሪና ጽንፈኛ እስላማዊ ሀይሎች እንደነበሩና እንዳሉም ይታወቃል፡፡ ጃዋር መሀመድ በአክራሪ ጽንፈኛ እስላማዊ የሀይማኖት መስመር ውስጥ በዋና አቀንቃኝነት ተሰልፎ የሚገኝ ለመሆኑ ማረጋገጫው በአንድ ወቅት ከእኛ ውጭ ያሉትን አንገታቸውን በሜንጫ እንላቸዋለን ሲል የተናገረው ተመዝግቦ የሚገኝ አባባል ከበቂ በላይ ማረጋገጫ ነው፡፡ ከእነዚሁ ሀይሎች ጀርባ በብዙ መልኩ በግብጽ፣ በኳታር፣ በኩዌት፣ በሳኡዲ አረቢያ የእነሱም ተላላኪና ቅጥረኛ በሆነው ሻእቢያ እንደሚታገዙ ይታወቃል፡፡ አንዱም ግባቸው በአክራሪ የእስልምና ሀይማኖትና በሸሪአ የምትመራ ሀገር መፍጠር ነው፡፡ ሌላው ግባቸው ደግሞ ኢትዮጵያ የአባይን ግድብ ግንባታ እንድታቆም በሁከትና በትርምስ በወኪሎቻቸውና በቅጥረኞቻቸው አማካኝነት በህዝቡ ውስጥ አለመረጋጋት እንዲሰፍን መስራት፤ የእርስ በእርስ ግጭት እንዲነሳ፤ እንዲስፋፋ በማድረግ የግብጽንና የአክራሪ እስላማዊ ሀይሎችን አጀንዳ በሚፈልጉት መሰረት ማሳካት ነው፡፡ ይህ ደግሞ በውል ተለይቶ የታወቀ፣ መቼም የማይሰንፉበት መስመራቸውና አቋማቸው ነው፡፡ ከዚህ የከፋ ሁኔታ ለመፍጠር ከመሞከርም ወደኋላ የሚሉ አይሉም፡፡ ምንም ባላሰቡበት ሁኔታ ህይወታቸውን በሞት ለተነጠቁት ወገኖቻችን ጥልቅና መራራ ሀዘን በውስጣችን ዘልቆ ገብቶአል፡፡ ወደፊት የከፋ ሁኔታ እንዳይከሰት ህዝብ ሀገሩን ነቅቶ ሊጠብቅ ይገባል፡፡ ከጥፋት ተልእኮው ጀርባ ብዙ ጸረ ኢትዮጵያ ሀይሎች እንዳሉም ለአፍታም ቢሆን ልንጠራጠር አይገባም፡፡