ጥፋት ጥፋት እንጂ ልማት አይሆንም

በኢትዮጵያ አክራሪ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ዘንድ ባህላቸው ሁኖ የኖረው የጽንፈኝነት ፖለቲካ ዘመን ተሻግሮ ዛሬም ለሀገር ውድመትና ጥፋት ተግቶ እየሰራ ይገኛል>> አክራሪው ኦነግና አቻው ግንቦት 7 በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች በግብጽና ሻእቢያ አሽከርነትና ተላላኪነት ስር ተሰልፈው በአረብ ሀገራት ምንዳ እየተሰፈረላቸው የገዛ ሀገራቸውን እያቆሰሉ፣ ወገናቸውን እየገደሉኛ አንጠራ ሃብታችንን እያወደሙ ይገኛሉ>>

በጥፋትና ውድመት ሀገርን ከመግደልና ህዝብን ለከፋ መከራና ችግር ከመዳረግ ውጪ የሚመጣ ለውጥም ሆነ የሚገኝ ጥቅም እንደሌለ አለመገንዘባቸው ነው ለዚህ የዳረጋቸው>> እነዚህ ወገኖች፣ ምናልባትም በሀገሪቱ ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ውድመት እንዲከሰት ሀገሪቱም ወደ መበታተን አፋፍ እንድትደርስ እየተጣደፉ ይገኛሉ>> አክራሪውና ጽንፈኛው ሀይል ምጽዋት እየለመነ የሚሰበስበውን ዶላር ወደ ሀገር ቤት እየላከ ሀገር እንዲበጠበጥ አውሮፓና አሜሪካ ተቀምጦ ሰፊ የሚዲያና የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ከፍቶአል>> ለአንድ አፍታ ቆም ብሎ የማን ሀገር ነው እየወደመ ያለው ብሎ ለማሰብ እንኳን አልታደለም>> አክራሪውና ጽንፈኛው ሀይል እንደ ሰው፣ እንደ ዜጋ ሀገሬ ወገኔ ሳይጎዳ የተፈጠረው የውስጥ ችግር እንዴት መፍትሄ ያግኝ በሚል አይደለም እየሰራ ያለው>>

ቂም በቀል አግቶና የበቀል ጥርሱን ነክሶ በተገኘው አጋጣሚ ሀገሪቱ በደም አበላ እንድትታጠብ የጸና ምኞቱ ነው፤ ሀገር በመቻቻል፣ በይቅርታና በምህረት፣ በመደማመጥ፣ በሰላምና በመግባባት እንጂ በበቀል እንደማትመራ አለማወቁ ግን እጅግ አስገራሚ ነው>> አክራሪው ሀይል ውስጥ በነገሰው የስልጣን ጥምና የከፋ ጥላቻ አገር ሰላማዊ ሁና ልትራመድ አትችልም>> ይሄንን አደገኛ ለሀገር፣ ለህዝብ ለአብሮነት ጠንቅ የሆነ አስተሳሰብ ከውስጣቸው አውጥተው በመጣል በፍቅር፣ በመቻቻል፣ በአብሮነትና በመደማመጥ ችግርን ለመፍታት ሀገርንም ከውጭ ሀይሎች ከፋፋይ ሴራና ደባ በአንድነት ጸንቶ ለመጠበቅ እስካልተቻለ ድረስ የሀገሪቱ ህልውና አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳይደርስምያሰጋል>> ኦነግ ኦሮሚያን፣ ኦብነግ ኦጋዴንን፣ የሲዳማ አርነት ሲዳማን፣ የጋምቤላ ነጻ አውጪ ጋምቤላን ለመገንጠል አክራሪውና አሸባሪው እስላማዊ ሀይል የሆኑት ወሀቢና ሰለፊዎች ደግሞ በሸሪአ ህግ የምትመራና የምትተዳደር እስላማዊት ኢትዮጵያን በረዥም ግዜ ትግል እናሳካለን ብለው በሚንቀሳቀሱበት ግንቦት ሰባት በሻእቢያ አሽከርነት ስር ተሰልፎ እየተራወጠ ባለበትና ሁሉም በግብጽ መንግስት ገንዘብ በመረዳት ኢትዮጵያን ለመቀራመትና ለማጥፋት በአሁን ሰአት የተሰለፉበት ሁኔታ ሲታይ ይሄ ነው ወይኢትዮጵያዊነት? ይሄ ነው ወይ የሀገርና የህዝብ ፍቅር? እንደዚህ ነበሩ ወይ የእኛ ቀደምት አባቶች? ያሰኛል>> በእጅጉም ልብ ይሰብራል>> መንግስት ለሀገርና ለትውልድ የሚበጁ ተሻጋሪ የልማት ስራዎችን ሰርቶአል፤ እየሰራም ይገኛል>> የዛኑም ያህል ህዝብን ያስከፉና ያስመረሩ፣ የመልካም አስተዳደር፣ የፍትህ፣ የሙስናና የኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮች በመንግስታዊ መዋቅሩና በፓርቲው አመራሮች ዘንድ መከሰቱን በማመን ለጥልቀታዊ የተሀድሶ ለውጥ እንደሚሰራ ገልጾአል>> የውስጥና የውጭ አክራሪና ጽንፈኛ ሀይሎች በህዝቡ ውስጥ የተከሰተውን ተቃውሞ አቅጣጫ በማስቀየር ለራሳቸው አጀንዳ ማሳኪያነት ለመጠቀም በግንባር ቀደምትነት በግብጽ አመራር ሰጪነት ስር ሁነው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ>> ግብጽ መቼም ቢሆን ለአንዲትም ሰከንድ በታሪክዋ ለኢትዮጵያ ቅን አሳቢና ተቆርቋሪ ስትሆን ታይታ አትታወቅም፤ እንደዚያ አይነት ታሪክም የላትም>> ከግብጽ ጋር የተሰለፈ በግብጽ የሚረዳ የትኛውም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት ለኢትዮጵያ ሰላም፣ ደህንነት፣ ልማትና ብልጽግና ሊያስብም ሆነ ሊጨነቅም አይችልም>> ተልእኮው ሀገሪቱን የማጥፋት፣ የእርስ በእርስ
ጦርነት ውስጥ እንድትገባ የማድረግ፣ የኢኮኖሚና የልማት እድገት ግስጋሴዋን የመግታትና ዝንተ አለም ከተረጂነትና ከተመጽዋችነት እንዳትወጣ የማድረግ ነው>> ግብጾች ጥንትም ዛሬም እየሰሩ ያሉት ይሄንኑ ነው>> እኛ ላይ የለኮሱትና ያነደዱት እሳት ብዙም ሳይርቅ ወደነሱው ተመልሶ የግብጽ ህልውናና መንግስትነት ታላቅ ፈተናና ቀውስ ውስጥ እንደሚገባ የምናይበት ግዜ ሩቅ አይሆንም>> ኢትዮጵያ በታላቅ መንፈሳዊ ምስጢር የተፈጠረች የተሞላችም ሀገር ነች፤ ይህን የማያውቅ ካለ የውቀው ዘንድ የግድ ነው>> ከሰሞኑ በተለያዩ በኦሮሚያ ክልሎች የተካሄዱት የንብረት ማውደም ስራዎች የሚመሩት በኦነግና በነጃዋር መሀመድ በግብጽና በሻእቢያም የበላይነት ጭምር ነው>> ሀገሬን ወገኔን እወዳለሁ፣ ለሀገሬ ሰላምና ሉአላዊነት እቆማለሁ የሚል ማንኛውም ዜጋ ነቅቶ ሊከላከለውና ሊዋጋው የሚገባውም ይሄንኑ የህዝብን ተቃውሞ ሽፋን ባደረገ መልኩ በውስጡ በጸረ ኢትዮጵያ ሀይሎች መሪነትና አቀናባሪነት በሀገሪቱ ላይ የተከፈተውን የጥፋት ዘመቻ ነው>> በየትኛውም መስፈርት ቢመዘን ህዝብ የሚገለገልበትን፣ የሚሰራበትን፣ ለራሱ ጥቅምና አገልግሎት የሚውለውን መኖሪያውና መተዳደሪያው የሆነውን ንብረት አያወድምም>> ስራ ቢቆም ተጎጂው ቤተሰቡ፣ ልጆቹና እራሱ መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል>> ሀገሪቱን ለማልማትና ከድህነት ለማውጣት የተዘረጉትን መሰረተ ልማቶች ንብረቶች ማውደም መቼውኑም በህዝብ አይፈጸምም>> እንደዚህ አይነቱ እኩይ ዘመቻና ድርጊት የሚመራው በጸረ ኢትዮጵያ ሀይሎች ብቻ ነው>> ንብረቱ የማንም ይሁን የማን የሚሰራበት የስራ እድል አግኝቶ የሚኖርበት የሚጠቀምበት ህዝብ ነው>> እንደታየው ብዙ ፋብሪካዎች፣ ከባድ ተሸከርካሪዎች፣ የግለሰብ ዜጎች፣ ሀብቶችና ንብረቶች፣ አምቡላንስ፣ የውሀ ማጠራቀሚያና ማከፋፌያ ዴፖዎች፣ ጋኖች በእሳት ተለኩሰው ነደዱ፤ ወደሙ>> በዚህ ድርጊት ከባለሀብቶቹ በላይ የተጎዳው ስራው፣ እንጀራው ህይወቱ የነበረው ህዝብ ነው>> እንዲህ ነበር እነሶርያን እነሊቢያን ቀስ በቀስ በኋላም ሙሉ በሙሉ የማውደሙ ስራ የተጀመረው>> ጥንታዊ የነበሩት ታዋቂ ከተሞች ብዙ ታሪክ ቅርስና ልማት የነበራቸው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህዝቦች የሚኖሩባቸው ስንትና ስንት ዘመን ተለፍቶ ትውልድ በየፈረቃው ገንብቶ ያስተላለፋቸው መሰረተ ልማቶች ከተሞች መንገዶች ህንጻዎች ተቋማት እንዳልነበሩ ሆነው ወደሙ>> ዛሬ ባዶ አውድማ ካልሆነ በስተቀር ምንም የለም>> ህዝቡም በጦርነት አለቀ>> የተሰደደውም ተሰደደ>> እነዛ በአለም ፊት ተከብረው ይኖሩ የነበሩ ህዝቦች መንግስት አልባ፣ ሀገር አልባ ሁነው የሚበሉት፣ የሚጠጡት፣ የሚለብሱት የሚጠለሉበት አጥተው ታሪካቸውም ሀገራቸውም ወድሞ ጥገኝነትና ተረጂነትን ፍለጋ በአለም ዙሪያ ተበተኑ>> ጸረ ኢትዮጵያ ሀይሎች ለኢትዮጵያ የሚመኙላትና የደገሱላት እንዲህ ሁና ማየትን ሲሆን የከፋው የወንጀላቸውም ሴራ ሀገሪቱን እንዳልነበረች አድርጎ ማፈራረስና መበታተን ነው>> የጀመሩት የጥፋትና የውድመት እርምጃም የሚነግረን የሚጠቁመን ወደዚሁ አዘቅት እንድንገባ የተቆፈረውን ጥልቅ ጉድጓድ ነው>> ግን አይሆንም፤ አይሞከርምም>> ያለጥርጥር ይህንን የጥፋት ሴራ ህዝቡ ተረባርቦ ይቀለብሰዋል>> ኢትዮጵያ አትጠፋም>> አትወድምም>> እነሱ ግን በየትኛውም መልኩ ቢሆን ይጠፋሉ>> አሁን ያለው ወጣት ትውልድ የነገው ሀገር ተረካቢ ስለሆነ የሀገሪቱን ጠላቶች መሰሪ ሴራ ጠንቅቆ ማወቅና ሀገሩንና ወገኑን ከጥፋትና ከውድቀት የመታደግ ታሪካዊ ሀላፊነት አለበት>> ከሀገርና ከህዝብ ሀብት ጥፋትና ውድመት የሚገኝ ደስታ ትሩፋት የሚመጣም ለውጥ የለም>> ይህ አሁን በሽብር ሀይሎች እየተሰራ ያለው ስራ፣ የሀገርን ሀብትና ንብረት የማውደሙ ሴራ ሀገሪቱን በኢኮኖሚ እድገትና በመሰረተ ልማት ጭራሽ የኋሊት እንድትሄድ ወደነበረችበት ኋላቀርነትና ድህነት እንድትመለስ የሚያደርግ፣ ህዝብንም ልጆቹንም ለከፋ ችግር አሳልፎ የሚሰጥ እኩይና አረመኔዊ ድርጊት ነው>> የዚህን ድርጊት ተዋናዮች ፈልፍሎ ማውጣትና በህግ እንዲጠየቁ ማድረግ የህብረተሰቡ ሀላፊነት ነው የሚሆነው>> በድርጊቱ ከማንም በላይ የሚጎዳው ህብረተሰቡ ነውና>> ድርጊታቸው በየትኛውም መስፈርት ሲለካ ፍጹም ጸረ ህዝብና ጸረ ሀገር ነው>> ከጀርባ ያለችው ግብፅ በገንዘብ እየደገፈች ያሰለፈቻቸው ኦነግና ሌሎችንም በመርዳት ለሀገራችን ጥፋት እየደገሰች ነው፤ ውድመቱን የደገሰው የግብጽ መንግስት ሻእቢያና
ተላላኪዎቹ መሆናቸውን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያውቀውና ሊጠነቀቅ የተቃዋሚዎችንም አሰላለፍ ሊረዳው ይገባል>> መንግስትን መቃወምና ጭርሱንም ሀገርን ለማፍረስ መሰለፍ የማይገናኙም የማይታረቁም ጉዳዮች ናቸው>> መንግስት ቢቀየር ሌላ መንግስት ቢመጣ የሚመራት ሀገር የግድ መኖር አለባት>> በማነህ ማነህ በእርስ በእርስ መባላትና መናቆር የሀገርን ህልውናና ደህንነት ብሄራዊ ጥቅሟን አሳልፎ ለውጭ ሀይሎች የሚሰጥ ባንዳ የመኖር ህልውናዋን አደጋ ላይ የሚጥል ስለሆነ ይህን ለመመከትና በጋራ ለመንቀሳቀስ በብስለትና በእርጋታ ማሰብ የሁሉም ወገን ሀላፊነት መሆን አለበት>> መንግስት የተጀመረውንም ልማትና እድገት ማስቀጠል፣ መምራትና ማስተዳደር፣ የህዝብንም ጥያቄ በአግባቡ መመለስ ካልቻለ ፍጹም ሰላማዊ በሆነና በሰለጠነ መንገድ በምርጫ ካርድ መልስ መስጠት ይቻላል>> ከዚህ ውጪ በሁከት፣ በትርምስ፣ በአመጽ፣ ንብረት በማውደም የሚኬድበት መንገድ ለጠላቶቻችን ሰፊ በር ከመክፈት ባለፈ የተሻለ ለውጥና ሰላም እንደማያመጣ ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ መማሩ ብልህነት ነው>> ከጥፋትና ውድመት የሚገኝ ለውጥ የለም>> የገነባነውን እያፈረስን አዲስ ሀገር እንገነባለን ማለት የህልም ቅዠት ነው>> አክራሪውና ጽንፈኛው ሀይል በማህበራዊ ድረገጾቻቸው አማካኝነት ለጥፋትና ለውድመት አላማቸው ሳያሰልሱ ለአመጽ ቀስቅሰዋል>> የእነሱ ሀሳብና እቅድ ስርአተአልበኝነት እንዲሰፍን በማድረግ ሁከቱን በመላው የሀገሪቱ ክልሎች ለማዛመት ነበር፤ ህዝቡ ታግሎ አስቁሞአቸዋል እንጂ>> በርእሳችን እንዳልነው ጥፋት ጥፋት እንጂ ልማት አይሆን፤ ከሰላም መደፍረስና መታጣት የሚገኝ ጥቅም እንደሌለም ይታወቃል>> የሰላሙም ሆነ የልማቱ ተጠቃሚና የሀገሪቱም ዋነኛ ባለቤት ደግሞ ህዝቡ ነው>> በሀገር ላይ ትርምስና ሁከት እንዲነሳ ሰላም ጠፍቶ ብጥብጥ እንዲነግስ አቅዶ የሚንቀሳቀስ የትኛውም ተቃዋሚ ቢሆን በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት የለውም>> ከጥፋትና ከውድመት የሚገኝ ትርፍ፣ የሚመጣ ለውጥ የለም>> በመሆኑም፣ በደረሰው ጥፋት እየተፀፀትንና ሌላ ጥፋት ላለማድረስ ቃል እየገባን አገራችንን እንጠብቅ፤ እድገታችንን እናስቀጥል። እነግብፅም ይህንን ይወቁት።