የአገራችንን ምርቶች ለዓለም ገበያ በማቅረብና መልካም አፈጻጸም በማስመዝገብ ለልማታችን ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለውን የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኙ እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡
እነዚሁም የወጪ ንግድ ላኪዎች፣ የገንዘብ አስተላፊዎችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ይገኙበታል ፤ማበረታታት ይገባል ፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቅርቡ ለነዚህ የማበረታቻ ሽልማት ሰጥቷል ፡፡በሸራተን አዲስ በተካሄደው ሽልማት መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ 127 ተቋሞችና ድርጅቶች ከ1 ሚሊየን ዶላር እስከ 300 ሚሊየን ዶላር በባንኩ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘታቸው ነበር የተሸለሙት ፡፡ ባንኩ በየዓመቱ በሚያደርገው የደንበኞች ቀን ሽልማት ከምስክር ወረቀት ጀምሮ እስከ የወርቅ፣የብርናና የነሐስ ሜዳሊያዎችና ፕላተኔሞች ሸልሟል ፡፡
ባንኩ በየዓመቱ የላቀ የኤክስፖርት አፈጻጸም ላሳዩ ተቋማትና ግለሰቦች እውቅና በሚሰጥበት ተሸላሚ የሆኑ ነባርና አዳዲስ ኤክስፖርተሮችም ለዚህ ስኬት በመብቃታቸው ደስ ሊላለቸው ይገባል ነው ያለው፡፡
መንግስት ሀገራችን ከድህነት ተላቃ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ እንድትሰለፍ ሁሉንም አገራዊ የልማት ዓቅሞች ለማንቀሳቀስና ለውጤት ለማብቃት የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ነው ፡፡
ይህ ጥረት ከጊዜ ወደ ግዜ ተሳክቶ መንግስት የግሉ ሴክተርና መላ የሀገራችን ህዝቦች ባካሄዱት የተቀናጀ ልማት ሀገራችን ከዘመናት የማሽቆልቆል ሂደት ወጥታ ለሩብ ምዕተ ዓመት ያህል በዕድገት ጎዳና እንድትራመድ ለማድረግ ተችሏል ፡፡
መንግስት ባለፈው ትግልና ጥረት ብቻ ሳይወሰን ከንግዲህም አገራችን ለሌላ ተመሳሳይ ከፍተኛ ዕድገት እንድትበቃ ለማድረግ እንዲቻል 2ኛው ዕትዕ ከግብርና መር ወደ እንዱስትሪ መር ለማሸጋገር በሚያስችል ቅኝት አዘጋጅቶ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረም እነሆ ሁለተኛ ዓመት እያስቆጠረ ነው ፡፡
በሀገራችን በመካሄድ ላይ ያለው ለውጥ ከግብረና መር ወደ እንዳስትሪ መር እንዲሸጋገር ባንድ በኩል ዘመናዊ እንዲስትሪ ለሚሸከም መሰረተ ልማት የማስፋፋት በሌላ በኩል ደግሞ መጠነ ሰፊ እንዳስትሪያዊ ግንባታ ማካሄድ እንደሚገባ ይታመናል ፡፡
እነዚህ ተግባራት በተሳካ መንገድ ይፈጸም ዘንድ ደግሞ ፋይናንስ የሚጫወተው ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው ፡፡
በዚሁ የደንበኞች ቀን በዓል ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዳይሬክቶሬት ቦርድ ሰብሳቢ አቶ በረኽት ስምዖን “አገራዊ የፋይናንስ በተለይም ደግሞ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ከግብርና ወደ ኢንዳስትሪ መር በሚካሄደው በዚህ ሽግግር ቁልፍ ሚና ይጫወታል ፡፡
መንግስት አገራዊ የካፒታል ክምችትን ለማጎልበትና ለኢንዱስትሪ ልማት የሚሆን ፋይናንስ በተለይ ደግሞ የውጭ ምንዛሪ ለሟሟላት በልዩ ትኩረት ሲንቀሳቀስ ቆይቷል ፡፡
በአነስተኛ አርሶ አደር ማሳ ላይ በመመስረት ለሩብ ምዕተ ዓመታት ያክል በተካሄደው ፈጣን ልማት አገራችን ወደ ኢንዳስትሪ ልማት ሊሰማራ የሚችል ፋይናንስ በሰፊው ለማቅረብም የምትችልበት ምቹ ሁኔታ በመፈጠር ላይ ነው ፡፡ባለፉት በርካታ ዓመታት ታላቁ የህዳሴ ግድብን ጨምሮ ልዩ ልዩ የመንግስትና የግል ትልልቅ ኢንቨስትመንቶችን ከራሳችን ውስጣዊ ምንጭ ለመሸፈን የሚያስችል ብቃት ማዳበራችን ለዚህ ዓይነተኛ ማረጋጫ ነው ፡፡በተጨማሪም አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋይናንስንና ልማትን እንደሚያገናኝ አንድ ድልድይ ቁጠባን የማሳደግ ስትራቴጂ ቀርጾ ይህንኑ ተግባረዊ የማድረግ ከመላው የሀገራችን ህዝቦች ያሰባሰበው ተቀማጭ ገንዘብ 320 ቢልየን መድረሱ ይህንኑ እንደገና በጉልህ የሚያሳይ ነው ፡፡ከዓመት ወደ ዓመት በመጨመር ላይ ያለው የውጭ ምንዛሪ ግኝትም የልማታችን ፍሬና አገራዊ ልማታችን ጥረታችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያግዝ ባንካችን በሀገራዊ ፋይናስም ሆነ በውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ለደንኞች ፍላጎት ለማርካት የሚያደርገው ጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ መጥቷል፡፡
ይሁንና የውጭ ምንዛሬ አቅርቦቱ እጅግ እያሻቀበ ከመጣው ፍላጎት ጋር ሊጣጣም ባለመቻሉ የደንበኞችን ታዳጊ ፍላጎት የሟሟላት ጉዳይ ራሱ የቻለ ተግዳሮት እንደሆነ ይታወቃል ፡፡
ባለፉት ዓመታት የአገራችን የውጭ ንግድ አፈጻጸም እንደሚያሳየው ለገበያ የምናቀርባቸው ምርቶች መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ቢሆንም ከነዚህ ጥሬ ምርቶች ሽያጭ የምናገኘው የውጭ ምንዛሬ መሆን የሚገባውን ያህል ጭማሪ አላሳየም ፡፡ይህም እሴት ያልተጨመረባቸውን ምርቶች ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ በተነጻጻሪ እያነሰ ከመሄዱ ጋር የተቆራኘ ነው ፡፡
በመሆኑም የውጭ ምንዛሪ ግኝታቸውን ለማሳደግ በፋብሪካ እሴት የተጨመረባቸው ለገበያ ለማቅረብ መሸጋገር አጣዳፊ ሆኖ ይገኛል ፡፡
አገራችን ያላት ተዳጊ የውጭ መንዛሪ ፍላጎት ሊሟላ የሚችለው ኢኮኖሚያችን በኤክስፖርት ዘርፉ እየተመራ ከግብርና ወደ ኢንዳስትሪ መር ሲሸጋገርና ኢንዱስትሪውም በኤክሰፖርት ዘርፍ ሲመራ ነው ፡፡” ሲሉ ነበር ያስገነዘቡት ፡፡
ስለሆነም አገራችን ወደ ውጪ ለምትልካቸው ምርቶች ላይ እሴት በመጨመር ይህንኑ በዓይነትና በመጠን በማጎልበት የውጭም ምንዛሬ አቅርቦትን አስተማማኝ ማድረግ ይገባል ፡፡
አገራችን በዓለም ገበያ ተፈላጊ የሆኑ በርካታ የምርት ዓይነቶች ያሏት በመሆኑ እነዚህም በከፊልም ይሁን በሙሉ ባለቀላቸው ደረጃ ወደ ማዘጋጀት ማምራት ይገባል ፡፡ከዚህ በመነሳት መንግስትም ሆነ ንግድ ባንኩ የአገሪቱ ባለሃብቶች በጥሬ እቃዎቻቸው ላይ እሴት በመጨመር ወደ ዓለም ገበያ ለማቅረብ የሚያደርጉትን ጥረት አስፈላጊ ሆኖ በተገኘው መንገድ ለመደገፍ ዝግጁ ናቸው ፡፡
ያለፈው ዓመት በተለይ ለውጭ ንግድ የተሰማሩ ባለሃብቶች አዳጋች እንደነበረ መንግስት በጥብቅ ይገነዘባል ፡፡
በዓለማችን ብሎም በአገራችን የተከሰተው የአየር መዛባት ተከትሎ ሰፋ ያለው አከባቢ የሸፈነው ድርቅ በኤክስፖርት ምርት አቅርቦት ላይ የራሱ ተጽእኖ አስከትሎ ነበር ፡፡
በአንዳንድ የአገራችን ክፍሎች ተከስቶ የነበረው አለመረጋትም በኢኮኖሚው ላይ በተለይ በውጭ ንግድ ላይ የራሱ ተጽእኖ ማሳረፉ አይዘነጋም ፡፡
ይህ በመሰለ አስቸጓሪ ሁኔታ ወቅት በመንቀሳቀስ ምርትና አገልግሎቶችን ለዓለም ገበያ በማቅረብ የአገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ይዞታ ለማዳበር ባለሃብቶች ያደረጉት ጥረት በእጅጉ የሚያስመሰግን ነው ፡፡
ልዩ ልዩ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች ባጋጠመበት ባለፈው ዓመት በተለመደው አገራችን የ8በመቶ ዓመታዊ የዕድገት ምጣኔ ማስመስገቧ የተከተልነው ልማታዊ አቅጣጫ ምን ያህል ትክክለኛ እንደሆነ ያመለክታል ፡፡
ዛሬም መንግስት እንደትናንቱ በልማት ለተሰማሩና ለሚሰማሩ ወገኖች ከፍተኛ ድጋፍ በሚሆን የመሰረተ ልማትና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ ላይ መረባረቡ በኢንዱስትሪ እሴት በመጨመርና በምርቶቻቸው ከፍ ያለ የውጭ ምንዛሪ ለማስገኘት ቆርጦ ለተነሱ ሁሉ መልካም አጋጣሚ ነው ፡፡
ባሳለፍነው ዓመት በነበረው መልካም ዝናብና በአርሶ አደሩ ጥረት ግብርናው የተሻለ ዕድገትና ምርታማነት ያስመዘገበ በመሆኑ 319 ሚሊየን ኩንታል መገኘቱን የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ሚኒስትር የተገኘው የቅድመ ትንበያ መረጃ ያመለክታል ፡፡ይህም ዘንድሮ ከበልግ ከመታፈሰው 93 ሚሊየን ኩንታል ሰብል እና ከመስኖ ልማት ምርት ሳይጨምር ማለት ነው ፡፡
በምርት ሰንሰለት ውስጥ እሴት ለመጨመር ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ነው ፡፡ በዚህ ላይ በኢትዮጵያ በፈጣን ልማት አሻራው ያኖረውን ንግድ ባንኩ በካፒታል ዓቅሙ 43 ቢሊየን ብር አሳድጓል ፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግማሽ ዓመቱ 28 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ተመላሽ ብድር ሰብስቤያለሁ ብሏል፡፡
በተያዘው ዓመት ውስጥ 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር የውጨ ምንዛሬ መሰብሰቡንም ባንኩ ጠቁሟል፡፡ ከዚህ ውስጥ 1 ነጥብ 9 ዶላሩ ከውጭ አገር በሀዋላ የተገኘ ነው ተብሏል፡፡
ስለሆነም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ልማታዊ ባለሃብቶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ለማገልገል መዘጋጀቱ ለስራቸው መቃናት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ በመጠቀም የወጪ ምርቶችን በዓይነትና በመጠን ሊያበራክቱ ይገባል ፡፡ ሰላም!