ሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ

 

                                                

ዴሞክራሲ በአገራችን ውሰጥ እውን ከሆነ ጥቂት ዓመታት ቢሆንም፣ እየተከናወነ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ግን ከእድሜውን አጭርነት ከፍ ያለ ነው። በተለይም በሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አከባበር ሁኔታ አኳያ ረጅም ርቀት መጓዝ ችላለች። ሰብዓዊ መብቶች ሰብዓዊ የሰው ሰው ልጅ መብቶች ናቸው። ሰው በሰውነቱ የሚጎናፀፋቸው መብቶችም ናቸው። የትኛውም አካል ሊሰጣቸውና ሊነፍጋቸው የሚገቡ መብቶች አይደሉም።

የሀገራችን ህዝቦች ባለፉት ስርዓቶች ለእነዚህ መብቶች ባይተዋር ነበሩ። ሰብዓዊ መብቶች በሀገራችን ይከበር የነበረው ለገዥዎች እንጂ ለህዝቡ አይደለም። ህዝቡ በገዛ ሀገሩ ሰብዓዊ መብቶቹ ተጥሶበት፣ ሰው መሆኑም ሳታወቅ እጅግ ዘግናኝ ሁኔታዎችን አሳልፏል። ይህ ሁኔታም ህዝቦች አንገታቸውን ቀና አድርገው እንዲጓዘ ያስችላቸው ዘንድ ለትግል ያነሳሳቸው ጉዳይ ሆኗል። በዚህም ህዝቡ ይህንንና ሌሎች መብቶቹን ለማስከበር ከፍተኛ ትግል አድርጓል። ባካሄዱት መራርና እልህ አስጨራሽ ትግል ይህን መብቶቻቸውን ማስመለስ ችለዋል።

በዚህም ባለፉት 25 ዓመታት ራሳቸው ተስማምተው ባፀደቁት ህገ መንግስት ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን መጎናፀፍ ችለዋል። የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር አለመኖር በመሆኑና ይህ የሀገራችን ህዝቦች የዘመናት ጥያቄ በአሁኑ ወቅት በቂ ምላሽ በማግኘቱ ነው። እነዚህ መብቶች የራሳቸው ተግዳሮቶች ቢኖሩባቸውም፣ ችግሮች በሂደት የተፈቱ ሰብዓዊ መብቶች በተሻለ ሁኔታ እንዲተገበሩ ማድረግ ተችሏል።

እርግጥ የኢፌዴሪ ህገ -መንግስት ለዜጎች ካጎናፀፋቸው ዴሞክራሲያዊ መብቶች መካከል የቡድንና የግለሰብ መብቶችን መጥቀስ ይገባል። መብቶቹ በዋነኛነት የአመለካከትና ሃሳብን በነጻ የመያዝና የመግለጽ፣ የመሰብሰብና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነት እንዲሁም አቤቱታን ማቅረብን የሚያጠቃልሉ ናቸው፡፡ እነዚህ መብቶች ሀገራችን ውስጥ ጥበቃ እየተካሄደላቸው ያሉ ብቻ ሳይሆኑ፣ በፖለቲካው ምህዳር ውስጥ በተጨባጭ ገቢራዊ እየሆኑ የመጡም ጭምር ናቸው።

ይህን ሁኔታ ለመግለፅ የታዘብኳቸውን ጥቂት ምሳሌዎች ማንሳት ያስፈልጋል። በተለያዩ ወቅቶች ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሚያካሂዱት ሰላማዊ ሰልፎች፤ “መንግስት የታሰሩ ሰዎችን እንዲፈታ፣ ስራ አጥነትን እንዲቀንስ፣ በሃይማኖት ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ እንዳይገባ…ወዘተ.” ጥሪዎችን ሲያካሂዱ ተመልክተናል።

  በተለያዩ ወቅቶች በተደጋጋሚ ይካሄዱ የነበሩት ሰላማዊ ሰልፈኞችና ባለቤቶቹ ህግን እስካልጣሱ ድረስ ከፖሊስ ምንም ዓይነት ትንኮሳ ሲደርስባቸው አልተመለከትኩም። እናም ለእኔ ይህ ተጨባጭ ሁኔታ በሀገራችን ውስጥ የሚታየው ተደራጅቶ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን የሚያመላክትና ለፖለቲካ ሂደቱ አዲስ መንገድ በሂደት እየታየ መሆኑን የሚያንፀባርቅ ይመስለኛል። እርግጥ ምንም እንኳን እነዚህ መብቶች ከጀማሪነት አኳያ በተሰላፊዎቹ ላይ ችግሮች ቢኖሩም ረጅም ርቀት ግን መሄድ ሠ

 ያም ሆነ ይህ ከላይ የጠቀስኩት ማሳያ መንግስት ለዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር ያለውን ቁርጠኛ አቋም የሚያሳይ ይመስለኛል፡፡ ማናቸውም የቡድንና የግለሰብ ፖለቲካዊ መብቶች ያለ አንዳች ጣልቃ ገብነት የሚከናወኑና ከበሬታ የሚቸራቸው ብሎም በፖሊስ ሃይል ጉልህ ጥበቃ የሚደረግላቸው መሆናቸውንም ጭምር፡፡

እርግጥ በተለያዩ ወቅቶች በሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች በፓርቲዎች የዕውቀትና የግንዛቤ ችግር ሳቢያ ሁከትን የሚቀሰቅሱ ቃላቶች ሊሰነዘሩ፣ የሌሎችን መብት የሚነኩ አጸያፊ ሰድቦች ሊሰሙ እንዲሁም ‘አትነሳም ወይ!’ የሚሉ ጠብ-ጫሪ ዝማሬዎችም ሊደመጡ ይችላሉ፡፡ ስንሰማም የኖርነው እንዲህ ዓይነት ዝማሜዎችን ነው።

 ያም ሆኖ ግን ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ሃሳባቸውን በነጻ የመግለጽ ተቃውሟቸውን የማስማት መብታቸውን የነፈገ አንዳችም ኃይል የነበረ አይመስለኝም። ይህ መሆኑም እዚህ ሀገር ውስጥ እየተገነባ ያለው ያለ ዴሞክራሲ ለመቻቻል ቅድሚያ የሚሰጥ ስለሆነ ነው። የሃይማኖት ነጻነትን በተመለከተም የሚነሳው ክርክር ከነባራዊ ሁኔታው ጋር የሚጣጣም አይመስለኝም። ምክንያቱም የኢፌዴሪ ህገ- መንግስት የመንግስትና የሃይማኖት መለያየትን በግልፅ መደንገግ ብቻ ሳይሆን ድንጋጌውም ካለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በላይ ወደ መሬት ወርዶ ተግባራዊ በመሆኑ ነው።

 እስካሁን ድረስ መንግስት ከድንጋጌው በማንኛውም ሃይማኖት ጣልቃ ገብቶ ‘ይህን አድርግ ያንኛውን ደግሞ ተው’ ያለበትን ሁኔታ ለማስታወስ ይከብደኛል። የሃይማኖት መሪዎችን ሲሾምና ሲሽርም የታዘብኩበት አግባብ የለም፡፡ እርግጥ በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄዱ የሽብር ተግባራትን የማውገዝ፣ የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅና ወንጀለኞችን ለፍርድ ማቅረብ የመንግስት ግዴታ መሆኑ ማንም የሚክደው ሃቅ አይደለም። ሆኖም እነዚህ ተግባራት ከሃይማኖት አክራሪነት እንጂ፤ ከሃይማኖት ነጻነት ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም።

 መንግስትና ሃይማኖት በተለያዩበት ሀገር ውስጥ ሃይማኖታዊ መንግስትን መመስረት አይቻልም። እናም ይህን ችግር ለመፍታት መንግስት በሃይማኖት ስም በሚነግዱ ፖለቲከኞች ላይ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ አድርጓል።

 እናም የሃይማኖት አክራሪነት ሀገራችን ከምትከተለው ከዴሞክራሲ መርሆዎች አንፃር የሚጋጭ ከመሆኑም በላይ፤ መንግስት የሁሉንም ዜጎች የእምነት ነፃነትና የሃይማኖት እኩልነት ህገ-መንግስታዊ መርሆዎችን ለማስጠበቅ የሚያደርጋቸው ጥረቶች ከሃይማኖት ነፃነት ጋር የሚቆራኙበት ምክንያት ለማንም ግልፅ የሚሆን አይመስለኝም። 

 በአጠቃላይ ቀደም ሲል ያነሷኋቸው ክርክሮችና እኔም ከራሴ እይታ በመነሳት መልስ ለመስጠት የሞከርኳቸው ጉዳዩች ሙሉ ለሙሉ ምንም ዓይነት ችግሮች የላቸውም የሚል እምነት የለኝም። በሂደት የሚፈቱ ተግዳሮቶች መኖራቸው እሙን ነው። ይሁንና በደፈናው ‘ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እዚህ ሀገር ውስጥ የሉም’ የሚያስብሉ አይደሉም።

 ከ25 ዓመታት በፊት ምንም ካልነበረ ነገር ተነስቶ፣ ዛሬ ሊፈቱ ተግዳሮቶች ቢኖም የዜጎችን ሁለንተናዊ መብት ማክበርና ማስከበር ትልቅ እመርታ ይመስለኛል። እርግጥ ዛሬ እዚህ ሀገር ውስጥ የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚከበረው የሌሎችን ፍላጎትን ለማሟላት ወይም የውጭ መንግስታትን ለማስደሰት አይመስለኝም።

 እንደ እውነቱ ከሆነ ሀገራችን ውስጥ በውጭ ሃይሎች አማካኝነት የሚዘወሩ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሊኖሩ አይችሉም፤ አይገባምም። ምክንያቱም መብቶቹ የሚከበሩት የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የዘመናት ትግል ውጤት እንዲሁም የሀገሪቱ የህልውና ጉዳይ ስለሆኑ ብቻ ነው። እናም ባለፉት 25 ዓመታት የተናወኑትንና ዕመርታ ያሳዩትን የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ማጣጣል የሚቻል አይመስለኝም። የተገኙት ውጤቶች ማንም ሳይጠይቃቸው ራሳቸው የሚናገሩ በመሆናቸው ነው። እነዚህ ውጤቶች የተገኙት መንግስት ባደረጋቸው ቁርጠኛ ውሳኔዎች ነው።

 እርግጥም ባለፉት ስርዓቶች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ይፈፀምበት የነበረው የሀገራችን ህዝብ፤ በራሱ ትግል ባገኘው በምት ሰብዓዊ መብቶቹን ሊያረጋግጥ ችሏል። በስም ብቻ ወይም ሲነገሩ የመጡ ሰብዓዊ መብቶችን ይሰማ የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ዛሬ ላይ የመብቶቹ ተጠቃሚ ሆኑ ለልማቱ እየተጋ ነው። ሰብዓዊ መብቶቹ ያልተከበሩለት ህዝብ ልማትን ሊያረጋግጥ አይችልም። በዚህም ሳቢያ የሀገራችን ህዝቦች ሰብዓዊ መብቶቻቸው ስለተከበሩ ባለፉት 15 ዓመታት ተጨባጭ ውጤቶችን እያመጡ ነው። ይህ የልማት ውጤታቸውም በሰብዓዊ መብቶቻቸው እየተጋዘ ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል እምነት አለኝ።