የሞቀ ሳይሆን የተቃጠለ እሳትን ያውቀዋል፡፡ የኢትዮዽያ ህዝብ በቀደሙት ሥርዓት በተለያዩ አጋጣሚዎች ባደረጋቸው ጦርነቶች ምክንያት ከጦርነት ተጠቃሚ የሚሆን ወገን እንደሌለ ጠንቅቆ ያምናል።፡ ልጆቹ በግዳጅ ከጉያው እየተነጠቁ ለእሳት ይዳረጉ የነበሩበት ሁኔታ የማይድን አካላዊና ስነልቦናዊ ጠባሳ ጥሎ እንዳለፈ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ ሰላም ለኢትዮጵያዊያንም ሆነ ለሌሎች ህዝቦች በምንም ዓይነት ዋጋ ሊገመት የማይችል ፋይዳ እንዳለው እሙን ነው፡፡ ይህን ለኢትየጵያ ህዝብ መንገር ለቀባሪ የማርዳት ያህል ነው፡፡
ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በአገሪቱ ሰላም ሰፍኗል። በዚህ ምክንያትም ህዝቦች በየደረጃው የልማት ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡ የሰፈነውን ሰላምና መረጋጋት አጣጥሞ ሳይጠግብ አዲስ የሁከትና የብጥብጥ አጀንዳቸውን ዕውን ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች መከሰታቸውና የተለያዩ ሰላምን የሚያዉኩ ተግባራት እያከናወኑ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ እነዚህ ቡድኖች ህዝቦቻችን መቋጫ በሌለው ደም መፋሰስ እንዲገቡ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡
በአንዳንድ የኦሮሚያና የአማራ አካባቢዎች ስርዓቱን የሚያናጉ የህዝቦች አብሮነትን የሚሸረሽሩና ቀጣይነት ባለው የሁከትና የትርምስ ምህዋር የሚያሳፍሩ አጀንዳዎችን አንግበው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፈጦ የመጣው ማንነትን መሠረት ያደረገ ግዲያና ዝርፊያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይሻሻላል ተብሎ ሲገመት እየተባባሰ መምጣቱ ዋቢ ማደረግ ይቻላል፡፡
ይህ በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ቀላል የማይባል ጉዳት እያደረሰ ይገኛል፡፡ በአካባቢው የተከሰቱት ግጭቶች ብሄርን ማዕከል ያደረጉ መሆናቸው ደግሞ ነገሩን ያወሳስበዋል፡፡ ይህ ማንነትን ማዕከል ያደረገ ግዲያና ዝርፊያ ህዝቦች የፈጸመው እንዳልሆነ ምስክርነት መጥራት አያሻውም፡፡ ይህንን ድርጊት እየፈጸሙ ያሉ ወገኖች ፀረ ሰላም ኃይሎች ናቸው፡፡ በየወቅቱ ስለከከሸፋባቸው ሰላምን የማወክ ተግባራቸውን ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በተለያየ ርዕስ ቀደም ብሎም ሲነሱ የነበሩ እንደሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡
- ሰላም ለማደፈረስና ልማቷን ለማደናቀፍ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ሰበብ ቀላል የማይባል ጥረት መደረጉ ይታወቃል፡፡ ከከሸፉ አጀንዳዎች መካከል በሃይማኖት ስም ህዝብን ከህዝብ ለማፋጀት የተወጠኑ ሴራዎች እንደነበሩ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ በአገሪቱ የሃይማኖት መቻቻልና መተሳሰብ ለዘመናት የዘለቀ በመሆኑ ህዝቦች አንድነታቸውን ጠብቀው ኖረዋል፡፡
- መቻቻል፣ መረዳዳትና አብሮነት ኢትዮጵያዊያን ከሌሎች አገራት ህዝቦች ከምትለይባቸው ዋና ዋና ነገሮች አንዱ ነው፡፡ በአገሪቱ የሃይማኖት ነጻነት ባልተረጋገጠበት ወቅት ሳይቀር ኢተዮጵያውያን በሃይማኖት ልዩነት ምክንያት በጋራ ለመኖር ያስቸገራቸው ወቅት እንዳልነበር ይታወቃል፡፡ መቻቻልና መተሳሰብ ለዘመናት የዘለቀ አኩሪ ባህላቸው ነው፡፡ አንዱ የሌላውን ሃይማኖታዊ ዝግጅትና ስርዓት ላይ ይገኛል፡፡ በሃዘንም ሆነ በደስታ ይተጋገዛሉ ይደጋገፋሉ፡፡ ይህ ለዘመናት የዘለቀ የኢትዮጵያውያውያን መገለጫ ነው፡፡
- መሠረት ያደረገ ብጥብጥ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን በመጣበት በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ዓመታት በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች ታይቶ የነበረ ቢሆንም ያ ከስሞ ሁሉም ህዝቦች በአንድነት መኖርና የጋራ አገራቸውን መገንባት በተያያዙበት በአሁኑ ወቅት እንዳድስ እየተቀሰቀሰ መምጣቱ ከበስተጀርባው ሌላ አጀንዳ እንዳለው ለመገንዘብ አያዳግትም፡፡
- ግድብ ግንባታ ጋር ተያይዞ የአገሪቱን የልማት ጉዞ ለማደናቀፍ በተለያየ መልኩ የሚንቀሳቀሱ አገራት እንዳሉ ማወቅ አያዳግትም፡፡ ኢትዮጵያ ለዘመናት ተደፍሮ የማይታወቀውን የአባይ ወንዝ ላይ ልማት መገንባት መጀመሯ ግብጽ ውሃውን በበላይነት የመቆጣጠር ፍላጎቷና ቀደም ሲል ከሱዳን ጋር የገባችው ስምምነት መፍረሱን ስታይ የተለያዩ አጋጣሚዎች መጠቀም አትችልም ብሎ መገመት የዋህነት ነው፡፡
- ቀደም ሲል በአንዳንደ የኦሮሚያና የአማራ ክልሎች በአሁኑ ወቅትም በአንዳንድ የአማራ አካባቢዎች በቀጠለው ችግር ላይ የግንቦት ሰባትና እነሱን የመሰለ ዓላማ የሚያራምዱ ተዋኒያንና እጅ የለበትም ብሎ መደምደም የዋህነት ቢሆንም በዋናነት ግን የውስጥ ሥራ ባለመሠራቱና አመራሩ የሚጠበቅበትን ተግባር በተሰጠው ኃላፊነት መጠን ባለመወጣቱ እንደሆነ አያጠራጥርም፡፡
- እያጋጠመ ያለው ችግር ምንም ይሁን ምንም ሰላምን የሚያደፈርሱ ወገኖች ወግዱ ሊባሉ ይገባል፡፡ ኢትዮጵያ ለዓመታት የገነባችውን ልማት የማፍረስና ሰዎችን በማንነታቸው የመግደልና ንብረት የማውደም መንግሥትን ጥያቄ ማቅረብ ሳይሆን ሕግን መተላለፍና ወንጀል እንደሆነ እሙን ነው፡፡ የአገሪቱን ሕገ መንግሥት በሚፈቅደው መሠረት የማስከበር ኃላፊነቱን ባግባቡ ሊወጣ ይገባል፡፡ መንግሥት ሕገ-መንግሥቱን የሚያከብረውና የሚያስከብረው ኃላፊነቱን ለመወጣት ነው፡፡ ሕገ መንግሥቱን የማክበርና የማስከበር ሃላፊነት በህዝብ ተሰጥቶታል፡፡ ይህንን ሕግንና ደንብን የማስከበር አደራ መወጣት ይኖርበታል፡፡
- ወቅት መንግሥት አደራውን ለመወጣትና ሕግንና ደንብን ለማስጠበቅ የተለያዩ ጥረቶች እያደረገ ቢሆንም የዘላቂ ሰላም ጉዳይ በመንግሥት ጥበቃ ብቻ የሚፈጸም አይደለም፡፡ የሰላም ባለቤት ህዝቡ ነው፡፡ የአገራችን ህዝብ ሰላም ወዳድ ህዝብ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ አሁንም ሰላሙን በዘላቂነት ለመጠበቅ ከመንግሥት ጋር ተባብሮ ሊሠራ ይገባል፡፡ "እሳትን የሚያውቀው የሞቀ ሳይሆን ተቃጠለ ነው" እንደሚባለው የሁከትና ግጭት አሉታዊ ፋይዳ ለኢትዮያዊያን አዲስ ነገር አይደለም፡፡ እልቂትና እርስ በርስ መተራረዱ ለአስርት ዓመታት አይተውታል፡፡ በዚህም ምክንያት ኢኮኖሚያቸው ደቆ ህዝቦች ለስደት ተዳርገዋል፤ በረሃብ አለንጋ ተገርፈዋል፡፡ ያንን ችግር ከሥር መሠረቱ ለመቅረፍ ሲሉ በርካታ ዜጎች ተሰውተዋል፡፡ ተሰውተው አልቀሩም ዕውን አድርገውታል፡፡
- ማንነትን መሠረት ያደረገ ትንኮሳ ዓላማው ሌላ መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ቀደም ሲል ሃይማኖትን ሰበብ አድርጎ የሀገሪቱን ልማት ለማደናቀፍና ሰላሟን ለማወክ የተኬደበት ሴራ በከሸፈ ማግስት መልኩን ቀይሮ የመጣው ማንነትን እየለዩ ሰዎችን መግደል አሁንም የውጭ ጠላቶችና አገር ውስጥም ያሉ የውስጥ አርበኞች ተግባር እንደሆነ መገመት አያዳግትም፡፡ ለዚህም ነው መንግሥት ውስጡን ማየት ያለበት፡፡ እስካሁን የተደረጉ ግምገማዎች ተስፋ ሰጪ እንደሆኑ ቢታወቅም ፀረ ሰላም ኃይሎች ይህ የተሃድሶ ግምገማ ተጠናክሮ እንዳይቀጥልና የውስጥ አርበኞቻቸው እንዳይመነጠሩ ሁከትንና ብጥብጥን በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ቀጥለውበታል፡፡
- 75 በላይ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ህዝች በጋራ በሚኖሩባት አገር በቀደሙት ስርዓታት እኩልነታቸው ማረጋገጥ የሚያስችል ሁኔታ ባለመኖሩ አንዱ በሌላው የበላይነቱን ያወጀበት የሁሉም ዜጎች ተጠቃሚነት ያልተረጋገጠበት ሁኔታ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነው፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ ያለው ኋይማኖታዊ ቁርኝንት የጠበቀ በመሆኑና የአንድ ሃይማኖት አማኞች ከሁሉም ብሔር፤ ብሔረሰብና ህዝቦች የተውጣጡ በመሆናቸው በብሔር ቢለያዩ በሃይማኖት በሃይማኖት ቢለያዩ በብሄር የተዛመዱ ስለሆኑ ጠላቶች የጠነሰሱትና ለረጅም ጊዜ የደከሙበት ኢትዮጵያን በሃይማኖትና በብሔር ከፋፍሎ የማፋጀት ጉዳይ የማይታለም ሆኖባቸዋል፡፡
- ሰላም ባለቤት የሆኑት ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ለሰላም እያደረጉ ያለውን ትጋት አጠናክረው ሊቀጥሉበት ይገባል፡፡ ባለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት የተመዘገበው የኢኮኖሚ ለውጥና በየደረጃው የታየው ተጠቃሚነት ሰላም በመስፈኑ የመጣ ነው፡፡ በመሆኑም ቅድሚያ ሰላምና መረጋጋትን ማስፈን ለሁሉም እንቅስቃሲያችን ወሳኝ በመሆኑ እጅና ጓንት ሆነን ፀረ ሰላም ኃይሎችን መዋጋት ይጠበቅብናል፡፡
ኋ