…በበለጠ ፍጥነት!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሰሞኑን ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎች ከሰጧቸው ምላሾች ውስጥ አንዱ ኢህአዴግን የተመለከተ ነው። በመግለጫቸው ኢህአዴግ እስካሁን የርዕዩተ ዓለም ለውጥ አለማድረጉን አስታውቀዋል። ድርጅቱ እስካሁን ባለው ቁመናው በጥልቅ ተሃድሶ መስመር ላይ የሚገኝ መሆኑንም እንዲሁ።

ኢህአዴግ በሂደት ራሱን እያሻሻለና ተሃድሶ እያደረገ አሁን ባለበት ደረጃ ላይ ደርሷል። በአሁኑ ሰዓት በአዳዲስ ሃሳቦች የሚስተዋለውን ፍላጎት ለመመለስ እየሰራ ነው። በቅርቡ ባካሄደው ጉባኤውም በተወያየባቸው አጀንዳዎች በመግባባት አጠናቅቋል። ይህም በኢህአዴግ ውስጥ ልዩነት አለ በሚል የሚናፈሰው ወሬ መሰረት የሌለው ተራ አሉባልታም መሆኑን የሚያመላክት ነው።

በጉባኤው ሁሉም የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች አሁን የመጣውን ለውጥ ሙሉ በሙሉ የተቀበሉና ያልተቀበሉ ግለሰቦች እንጅ እንደ ድርጅት ልዩነት የለም። ግለሰቦች ደግሞ አንድን ለውጥ መቀበላቸውም ይሁን አለመቀበላቸው ነባራዊ ክስተት ነው። እንደ ድርጅት ግን አራቱም አባላት (ህወሓት፣ ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደኢህዴን) ለውጡን ተቀብለው በጋራ በመስራት ላይ ይገኛሉ። ህብረተሰቡም ይህን ተገንዝቦ ከድርጅቱ ጎን በመቆም ለውጡን በበለጠ ፍጥነት ማስኬድ ይኖርበታል።

ድርጅቱ በጥልቅ ተሃድሶ ውስጥ ነው። በአገራችን ፈጥሮ የነበረውን ችግር ለመፍታት ባስቀመጣቸው አቅጣጫ እየተጓዘ ነው። በለውጡም በአንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠሩትን ሁከቶች በማርገብ ሰላምና መረጋጋትን ፈጥሯል።

ኢህአዴግ ምንም እንኳን በተለያዩ ማህበራዊ መስተጋብሮች ሊፈተን የሚችል ቢሆንም፤ ዋናው ነገር ችግሮቹን በተገቢው ሁኔታ ከህዝብ ጋር ሆኖ እያለፋቸው ነው። በአሁኑ ወቅት የሚገኝበት የለውጥ መስመር የጥልቅ ተሃድሶ ሂደት ያስቀመጣቸውን ተግባሮች የአመራር ፈጠራ ታክሎበት እየተፈፀመ ነው። በዚህም አገሪቱ ከፊቷ ተጋርጦባት የነበረውን የፀጥታ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን እጅግ በተፋጠነ ሁኔታ መፍታት ችሏል። እነዚህን ድሎች ማስመዝገብ የቻለው በለውጥ ሂደቱ ነው። ለውጡ ብዙ ለውጦችን አምጥቷል።

ዛሬ በመንግስት ስራ ላይ የሚገኝ አመራር የህዝቦችን መብት በሚሸርፍበት ወቅት የሚያስተካክለው ራሱ ህዝቡ ነው። በተለያዩ አካባቢዎች የተካሄዱት ህዝባዊ መድረኮች ይህን የሚያረጋግጡ ናቸው።

በየመድረኮቹ ህዝቡ ፍላጎቱን ይገልፃል፤ የተፈፀሙበትን የመልካም አስተዳደር ጉድለቶች በማቅረብ የሚመለከተው አካል ከቦታው እንዲነሳ ያደርጋል። ይህም ለውጡ የህዝብና በህዝብ የሚመራ እንደሆነ ያሳያል። የለውጡ መነሻም ይሁን መድረሻ ህዝቦች በመሆናቸው የህዝብ ንቅናቄ እሳት በሆነ ቁጥር የአመራሩ መቀጠል ጥያቄ ምልክት ውስጥ እንደሚገባም የሚገልፅ ነው።

እርግጥ በህገ መንግስቱ የተለያዩ አንቀፆች ላይ የተቀመጡት ሁሉም መብቶች የአገራችን ህዝቦች በትግላቸው የተጎናፀፏቸው ትሩፋቶች ናቸው። እነዚህን ህገ መንግስቱ ያረጋገጠላቸውን መብቶች ተጠቅመውም የበርካታ ውጤቶች ባለቤት ሆነዋል።

ዛሬ የአገራችን ህዝቦች በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ለውጥ ባለቤቶች ከመሆናቸው በላይ ለሌሎች አፍሪካውያን አርአያ የሚሆን ዕድገት በሁሉም መስኮች በአጭር ጊዜ ውስጥ እያስመዘገቡ ነው። በዚህም የህዳሴያቸውን ጉዞ ቅርብ ለማድረግ ግስጋሴያቸውን ተያይዘውታል።

በአሁኑ ሰዓት መንግስት በአሰራሮቹ ላይ ግልፅነትንና ተጠያቂነትን በማስፈን የህዝቦችን ህገ መንግስታዊ ፍላጎት እውን እያደረገ ነው። ይህም በመሆኑ በየጊዜው ለህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት የየወራት ስራዎቹን ያቀርባል። ያስገመግማል።

እንዲሁም መጠንከርና መሻሻል በሚገባቸው ጉዳዩች ላይ የሚሰጡትን አስተያየቶችንም ይቀበላል። እንዲያውም በ2011 ዓ.ም የፌዴራል መንግስት አስፈፃሚ አካላት የስራ ኮምትራት ከህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት ጋር ተዋውለዋል። ስለሆነም ተግባራቸውን ቆጥረው ተቀብለው ቆጥረው እንዲያስረክቡ ይደረጋል።

እርግጥ በዴሞክራሲ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤት የሆነው ህዝብ አስተሳሰብ፣ በጊዜ ሂደት ለምርጫ የሚሰጠው ትርጉም የሚያድግና የሀገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር እንዲሁም እየሰፋ የሚመጣ ብሎም ተወዳዳሪ ፓርቲዎች በምርጫ የሚኖራቸው ተሳትፎ እየጎለበተ የሚሄድበት አውድ ነው።

አሁን የምንገኝበት ደረጃ የህዝብ አስተሳሰብ እያደገ፣ ለለውጥ ያለውም ስሜት እየጨመረና የአገሪቱ የፖለቲካ ምህዳርም እየሰፋ ይገኛል። ህዝቡም በተወካዩቹ አማካኝነት እያደረጋቸው ያሉት ተግባሮች የአገራችን መፃዒ ዕድል ብሩህና ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው።

በመሆኑም አገሪቱን በመምራት ላይ የሚገኘው ኢህአዴግ የህዝቦች የትግል ውጤት የሆነውን ለውጥ በጥልቀት ማስፋትና ማጎልበት ይጠበቅበታል። የአሰራሩን ተጠያቂነትና ግልፅነት በዚያኑ ልክ ለህዝቡ ማረጋገጥም ይኖርበታል። በእነዚህ ጉዳዩች ዙሪያ እስካሁን የተኬደው መንገድ እጅግ አኩሪ ቢሆንም አሁንም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።

ገዥው ፓርቲና መንግስት እያካሄዱ ባሉት የጥልቅ ተሃድሶ እንቅስቃሴ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ከህዝቡ ጋር በመሆን ተረባርበዋል። ወደፊትም ህዝቡ በባለቤትነት መንፈስ ይንቀሳቀሳሉ። ይህም በአሁኑ ሰዓት በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ እየሰሩ ነው። በተለይም ህግና የበላይነቱን ለማስከበር ጠንክረው በመስራት ላይ ይገኛሉ።

ኢህአዴግ እንደ ገዥ ፓርቲነቱ ሌሎች በውጭ የሚገኙ ድርጅቶች በአገራቸው ፖለቲካ እንዲሳተፉ ጥሪ እያደረገ ነው። ይህም የህዝብን ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነት ከማክበር የመነጨ ነው።

እንደሚታወቀው ሁሉ በህገ መንግሥቱ አንቀፅ 8 ላይ የአገራችን ህዝቦች ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤት መሆናቸውንና ተገልጿል። ይህም በህገ መንግስቱ መሰረት በሚመርጧቸው ተወካዮቻቸውና በቀጥታ በሚያደርጉት ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ አማካኝነት የሚያስረዳ ነው።

አሁን ባለንበት የለው ሂደት ኢትዮጵያ ውስጥ ህዝብ ትብብሩና ፋና ወጊነቱ ወሳኝ ሆኗል። ሁሉም ነገር በህዝቡ ስምምነትና በጋራ አመራርነት ተፈፃሚ እንዲሆን እየተሰራ ነው። ምስጋና ለለውጡ ይግባውና ህዝብ አሊያም ወኪሎቹ ሳያውቁትና ሳይመክሩበት የሚከናወን አንዳችም ነገር የለም። ይህም ድርጅቱ ለህዝብ ፍላጎት ካላው ከበሬታ የመነጨ በመሆኑ ነገም ብሆን ተጠናክሮ ይቀጥላል። ስለሆነም ይህን ሁሉ የተለየ አሰራር ያመጣውን ለውጥ በበለጠ ፍጥነት ማፍጠን ያስፈልጋል።