ብሄራዊ ቡድኑ ከሌሴቶ አቻ በመለያየት ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ

የኢትዮጵያ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ከሌሴቶ አቻው ጋር ለ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን በሌሴቶ ሜዳ አካሂዶ 1 ለ 1 በመለያየት ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል፡፡

የመጀመሪያውን አስደንጋጭ ሙከራ ኢትዮጵያ 15ኛው ደቂቃ ላይ አድርጋ ፤የግቡ ቋሚ መልሶታል፡፡

ጫና ፈጥሮ የተጫወተው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከእረፍት መልስ 49ኛው ደቂቃ ላይ ቀዳሚ ሆኗል፡፡

35ኛው ደቂቃ ላይ ሌሴቶዎች ጥሩ ቦታ ላይ የቅጣት ምት አግኝተው ሳይጠቀሙበት ቢቀሩም፤ በድጋሚ

54ኛው ደቂቃ  ላይ  በግምት ከ20 ሜትር ርቀት ላይ ያገኙትን ቅጣት ምት ወደግብ ቀይረው አንድ አቻ ሆነዋል ፡፡

የሌሴቶ ብሄራዊ ቡድን የአቻነቷን ግብ ካስቆጠሩ በኋላ በተሻለ ጫና ፈጥረው ለመጫወት ቢሞክሩም ኳስና መረብ ማዋሃድ አልቻሉም፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከሌሴቶ አቻው ጋር በባህርዳር ስታዲየም ያደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ ያለ ምንም ግብ መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

ብሄራዊ ቡድኑ ከሜዳ ውጪ ግብ በማስቆጠሩ ምክንያት ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችሏል፡፡