ጎግል የመረጃ ማፈላለጊያ ፕሮግራሙን በአውስትራሊያ ሊያቋርጥ እንደሚችል አስጠነቀቀ

 

 

ጎግል የመረጃ ማፈላለጊያ ፕሮግራሙን በአውስትራሊያ ሊያቋርጥ እንደሚችል ማስጠንቀቁ ተሰምቷል፡፡

ኩባንያው ማስጠንቀቂያውን የሰጠው በአውስትራሊያ ከመረጃ እና ዜና ጋር በተያያዘ አዲስ ህግ ሊተዋወቅ መሆኑን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

በአውስትራሊያ ጎግልን ጨምሮ ፌስቡክ እና መሰል ኩባንያዎች የሚዲያ አውታሮች ለሚያጋሩት ዜና ገንዘብ እንዲከፍሉ የሚጠይቅ አዲስ ህግ እየወጣ ነው፡፡

አዲሱ ህግ የዜናው ባለቤት ነው ለተባለው ተቋም ወይም ግለሰብ ላጋራበት ኩባንያዎቹ ገንዘብ እንዲከፍሉ ያስገድዳል፡፡

ይህ መሆኑ ደግሞ እንደ ጎግል ያሉ ኩባንያዎችን አስቆጥቷል፡፡

ህጎቹ ጠንከር ያሉ እና በማህበረሰቡ የአገልግሎት ተደራሽነት ላይ ችግር ይፈጥራሉ በሚልም ተቃውሞታል፡፡

በአውስትራሊያ የጎግል ሥራ አስኪያጅ ሜል ሲልቫ ህጎቹ የማይሰሩ ናቸው ሲሉም ነው የገለጹት፡፡

ይተገበራል በተባለው አዲስ የክፍያ ህግ ላይ ስምምነት ካልደረሱም የጎግል መፈለጊያ በአውስትራሊያ ከማቆም ውጭ ምንም አማራጭ የለንም ነው ያሉት ስራ አስኪያጅ፡፡

(ምንጭ፡- ቢቢሲ)