ባለ ጥልቁ አዕምሮ ሮቦት


#ቴክኖ_ቅምሻ

ጎግል ውስብስብና ፈታኝ የሆኑ ሒሳቦችን መስራት የሚችል ባለ ጥልቅ አዕምሮ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) ሮቦት ይፋ አድርጓል፡፡

በሰው ሰራሽ አስተውሎት ስርዓት የሚሰራው ይህ ሮቦት አልፋ ፕሩፍ (Alpha Proof) እና አልፋ ጂኦሜትሪ 2 (Alpha Geometry 2) በመጠቀም ፈታኝ የሆኑ ሒሳቦችን ይሰራል። ሮቦቱ በዓለም ከባድና ውስብስብ ከሚባሉት ስድስት ችግሮች ውስጥ አራቱን በመፍታት በዓለም አቀፍ የሒሳብ ኦሊምፒያድ የብር ሜዳሊያ አግኝቷል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እጅግ በጣም ውስብስብና ፈታኝ የሆኑ ችግሮችን በመፍታት ጥሩ ውጤት እያስመዘገቡ ነው።

ሮቦቱ አልፋ ፕሩፍን እንደ መደበኛ የሒሳብ ማጠናከሪያ ትምህርት እና ለአልጀብራ ቁጥራዊ ቲዎሪ ሲጠቀም፣ አልፋ ጂኦሜትሪ 2 በመጠቀም ደግሞ የጂኦሜትሪ ጥያቄዎችን በ16 ሰከንድ ብቻ መፍታት ይችላል።

ሮቦቱ ምንም እንኳን ከሰዎች ጋር ለመፎካከር ጊዜ ቢያስፈልገውም ይህ ወሳኝ ምዕራፍ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በሒሳብ አመክንዮ ላይ ያለው አቅም ያጎላ መሆኑን ፎሲቢትስ ዘግቧል።

በየኔወርቅ መኮንን