ባምላክ ተሰማ ሁለት አኅጉራዊ ጨዋታዎችን በመሃል ዳኝነት እንደሚመራ ተገለጸ

ባምላክ ተሰማ

የካቲት 30/2014 (ዋልታ) ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ሁለት አኅጉራዊ ጨዋታዎችን በመሃል ዳኝነት እንደሚመራ ተገለጸ፡፡

የፊታችን ቅዳሜ በደቡብ አፍሪካ የሚደረገው የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ማሜሎዲ ሰንዳውንስ እና አል አህሊ ወሳኝ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ይህንን ወሳኝ ጨዋታ ለመምራት ዛሬ ወደ ስፍራው ያቀናል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በኳታሩ ዓለም ዋንጫ አፍሪካን የሚወክሉ አምስት አገራት ከሚለዩበት ጨዋታዎች መካካል አንዱ የሆነውን የማሊ እና የቱኒዚያ መጋቢት 16 ባማኮ የሚካሄደውን ጨዋታ እንደሚመራ ተጠቁሟል፡፡

የ41 ዓመቱ ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ በ33ኛው አፍሪካ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታን ጨምሮ በመሀል ዋና ዳኝነት የመራ ሲሆን በአስደናቂ ዳኝነት አድናቆትን ማግኘቱ የሚታወስ ነው፡፡

በሀብታሙ ገደቤ

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!