ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን ከናይጄሪያ ጋር ያደርጋል

ግንቦት 12/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን ከናይጄሪያ ጋር ያደርጋል፡፡
በ2022 በህንድ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው ከ17 ዓመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ የማጣሪያ ጨዋታውን እያደረገ የሚገኘው ብሔራዊ ቡድኑ የናይጄሪያ አቻውን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ ይገጥማል፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ በትላንትናው ዕለት የመጨረሻ ልምምዱን አከናውኗል፡፡
የቡድኑ አሰልጣኝ እንዳካቸው ጫካ ትላንት በሰጡት መግለጫ ከደቡብ አፍሪካ እና ከዩጋንዳ ጋር በነበሩ ጨዋታዎች የታዩ ክፍተቶችን ለማረም የሚረዳ ዝግጅ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጅራ በካፍ የልህቀት ማዕከል ተገኝተው ብሔራዊ ቡድኑን በማበረታታት ለሴቶች እግር ኳስ እድገት የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡
በመሰረት ተስፋዬ