ቲክ ቶክን ያገዱ የአሜሪካ ግዛቶች 19 ደረሱ

ቲክ ቶክ

ታኅሣሥ 11/2015 (ዋልታ) የማህበራዊ ትስስር ገጽ የሆነውን ቲክ ቶክ ያገዱ የአሜሪካ ግዛቶች 19 መድረሳቸው ተገለጸ፡፡

ቲክ ቶክን የደህንነት ስጋት ነው ያሉት የአገሪቱ ግዛቶች ቲክቶክ በመንግስትን ኮምፒውተሮች ጥቅም ላይ እንይውል ማገዳቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡ የሉዚያና እና ዌስት ቨርጂኒያ እገዳውን የጣሉ ተጨማሪ ግዛቶች መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡

የአሜሪካ ግዛቶች በዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት ተቋሙ አሜሪካዊያንን ይሰልላል በሚል እና በዜጎች ነፃ ሀሳብ ላይ እቀባ ያደርጋል በሚል ነው ተብሏል፡፡

ቲክ ቶክ በአሜሪካ ብቻ ከ100 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚ እንዳለው ሲገለፅ አንዳንድ የአገሪቱ የኮንግረስ አባላት የማህበራዊ ትስስር ገጹ ሙሉ ለሙ መታገድ አለበት የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል፡፡

መሰረቱን ቤጂንግ ያደረገው ተቋሙ በአሜሪካ እና በሌሎች አገራት የሚቀርበው ውንጀላ መሰረተ ቢስ ነው ሲል የማህበራዊ ትስስር ገጹ ምንም አይነት የደህንነት ስጋት የለውም ብሏል፡፡

ህንድ በፈረንጆቹ 2020 ቲክቶክን ያገደች ሀገር መሆኗ ይታወሳል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth