አትሌት ሰምበሬ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር አሸነፈች

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሰምበሬ ተፈሪ በአሜሪካ አትላንታ የተደረገ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር አሸነፈች፡፡

አትሌቷ ርቀቱን 30 ደቂቃ ከ49 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ ሆና የጨረሰችው፡፡

በውድድሩ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ጀማል ይመር በወንዶች ምድብ በተመሳሳይ ርቀት 3ኛ በመሆን ማጠናቀቁን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡