ሰኔ 29/2016 (አዲስ ዋልታ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛ ሳምንት መርኃ ግብር የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮጵያ መድንን 2 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን አንስቷል።
64 ነጥብ በመያዝ አንደኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ላይ ይሳተፋል።
ሌላኛው የዋንጫ ተፎካካሪ መቻል ድሬዳዋ ከተማን 1 ለ 0 በማሸነፍ በ63 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ የውድድር ዓመቱን አጠናቋል።