የባህርዳር ከተማ አውሮፕላን ማርፊያ ስያሜ ተቀየረ

የባህርዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ኤርፖርት

ባለፉት ዓመታት “የባህርዳር ግንቦት 20 ኤርፖርት” ተብሎ ይጠራ የነበረው የባህርዳር አውሮፕላን ማርፊያ “የባህርዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ኤርፖርት” ተብሎ እንዲጠራ መወሰኑ ተገልጿል።

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ ስያሜው ከ1983 ዓ.ም በፊትም ይጠራበት እንደነበር በማስታወስ እንዲሁም የህዝቡን ፍላጎትና የከተማውን ወካይ ስያሜ በመምረጥ ስሙ እንዲቀየር በሙሉ ድምፅ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል።

ተቋርጦ የነበረውም የአውሮፕላን ትራንስፖርት ከነገ ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ አገልግሎት እንደሚጀምር ነው አስተባባሪ ኮሚቴው የገለፀው ሲል የከተማውን ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ጠቅሶ አብመድ ዘግቧል።